Saturday, August 10, 2013

ተሸንፈን እንዳንቀር

(ሉሉ ከበደ)
አንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውን እየገመገሙና ራሳቸውን እያረሙ፤ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ
ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርም እድል ይሰጣቸዋል ።
ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን ብሎ ድንገት እየተጯጯኽ ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት።
ይህ አባይን የመሰለ ብሄራዊ ጉዳይ ባልታሰብ ሁኔታና ጊዜ ድንገት ያነሳው ቡድን፤ ኢትዮጵያን እንደሀገር ሊያቆዩአት የሚችሉ ልዩ ልዩ
ብሄራዊ ጥቅሞችን ለባእዳን አሳልፎ የሰጠ፤ ብሄራዊ እሴት ከኢትዮጵያዊ ብሄራዊ ስሜት ጋር እንዲጠፋ የሚታገል፤ በኢትዮጵያ ህዝብ
ምኞት ቁማር ተጫውቶ ወደ ኢትዮጵያ ትመጣ ይሆናል ያላትን የአረብ አብዮት ሊያሳልፍ እንጂ የሚጠላውን የኢትዮጵያ ህዝብ
ሊጠቅም አባይን እንደማይገነባልን እናውቀዋለን።
የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሾመው፤ የሚሽረው፤ የኔ የሚለው መንግስት ሲኖረው፤ በብሄራዊ ኢትዮጵያዊ ስሜትና አንድነት፤ በሀገር ፍቅር
ስሜት ተገንብቶ የተደራጀ ብሄራዊ ጦር ሲኖረው፤ በሙያው የተካኑ የሀገር ልጆች ተሰብስበው፤ ከመንግስታቸው፤ ከህዝባቸው ጋር
መክረው፤ የግንባታውን አይነትና መጠን ሰፊ ጥናት አካሂደው፤ በየትኛው ቦታ፤ መቼ፤ እንዴትና ለምን አላማ በምን መጠን ብንገነባው
በህዝቡ ኑሮ ላይ ቀጥተኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ትርፍ ያስገኛል ብለው መክረው፡ በውትድርናውም በህጉም አቅጣጫ ሊከተል
የሚችለውን ሁሉ አጥንተው፤ ገምተው፤ ሁሉም ዝግጅት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተደርጎ አባይ ለኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ሊገንባ
ይችላል። የኢትዮጵያ ህዝብ በማናቸውም መልኩ፤ የሚከፈለውን መስዋእትነት ከፍሎ ሊያስወግደው የሚገባ ጠላት፤ አባይን
ከኢትዮጵያ ህዝብ በሰረቀው ገንዘብ ለመገንባት ፍቃደኛ ቢሆን እንኳ ህዝቡ ባንድ እጁ ወንዙን እየገደበ ባንድ እጁ እየታገለ ሀገሪቱንና
ራሱን ነጻ ማውጣት አለበት። ወያኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገው ነገር በሙሉ በራሱ ጥቅም ዙሪያ የተሰላ እንጂ ለህዝብና ለሀገር
ይጠቅማል ተብሎ አይደለም።
አለቃቸው ከሞተ በኋላም የተረፉት የወያኔ መሪዎች፤ ሌጋሲው እያሉ ህዝቡን ማደናቆርና የዘረፋና የስርቆት እስትራቴጂአቸውን
ማጠናከሩን ቀጥለዋል። ሌጋሲ ጥሎ አለፈ የሚባለው መሪ፤ እንደ ኒልሰን ማንዴላ፤ ህይወቱን ሙሉ ለሰው ልጆች አንድነትና እኩልነት
ሲታገል፤ ጥቅሙንና ህይወቱን ለመስዋእትነት አቅርቦ፤ ሀገር ለበቀሉባት ዜጎቿ ሁሉ እኩል መኖሪያ እንድትሆን፤ እኩል ሀብት
እንድትሆን፤ ዜጎች በዘርና በቀለማቸው አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ሳይል እኩል አይን ለአይን እየተያዩ እንዲኖሩ የሚያስችል ስርአት
እንዲሰፍን አድርጎ የሚያልፍ መሪ ነው። እንደመለስ ዜናዊ አይነት በዘረኝነት የቆሸሸ፤ ያንኑ ካንሰሩን ህዝብ ላይ አራግፎ በሰላም የኖረን
ህዝብ እንዲበጣበጥ አድርጎ የሞተ ሰው ጥሩ ሌጋሲ ሳይሆን ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ በህዝብ መካከል ቀብሮ አለፈ ነው የሚባለው።
መሰረትና ምክንያት ከሌለው በቀልና ጥላቻ ጋር ተወልዶ፤ አማራ የሚባል ዘር ጨፍጭፎ ሳይጨርስ እግዚአብሄር ፍርዱን የሰጠውን
ሰው፤ በተጨባጭ ሲጨፈጭፉት፤ ሲያስሩት፤ ሲያግዙት፤ ለኖሩት ነጮች ምህረት አድርጎ፤ ትውልድን አስታርቆ፤ ሰላም አውርዶ፤
የአምላክን ሚና ለተጫወተ ታላቅ ሰው ማንዴላ የሚገባውን ክብር ለወያኔ ቆሻሾች መዘከር በህዝብ ማላገጥ ነው።
እንደ ወያኔ አይነት የህዝባቸውንና የሀገራቸውን ጥቅም ለሌላ አገር ህዝብና መንግስት አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጁ ወገኖች ባሉበት ሀገር
እነዚህ ገዢዎች የተወዳጇቸው መንግስታት የጥቅም ቁርኝታቸውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ በስልጣን ላይ እንዲዘልቁ የበኩላቸውን ምክር
መለገሳቸው የማይቀርና የተለመደ ነገር ነው። ባእዳኑ ማናቸውንም የረቀቀ የአፈናና የጭቆና ዘዴ ስለሚመክሯቸው
ስለሚያስተምሯቸው፤ ስልጣን ላይ እየቆዩ በሄዱ ቁጥር የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ነጻ ለማውጣት የተወሳሰበ ችግር ሊገጥመው ይችላል።
በሀያ ሁለት አመታት ጉዞአችን እያየነው ያለ ነገር ወያኔ የነደፈው እቅድ ያለ አንዳች ሳንካ እየተሳካ እየተሳካ በመሄድ ላይ ሲገኝ የኛ
የተገዢዎቹ ኢትዮጵያውያን እቅድ ጩኸት ብቻ ሆኖ እሱም ሰሚ የሌለው የምድረበዳ ጩኸት እየሆነ መምጣቱን ነው። መላውን
የሀገሪቱ ጦር ሰራዊት በራሱ የአማጽያን ቡድን ለውጦ፤ ወያኔ ፖለቲካውንም ኢኮኖሚውንም መቶ በመቶ በበላይነት ተቆጣጥሮ፤
በፈለገው አይነትና ሁኔታ ህዝቡን በዘር አጥሮ፤ ከፋፍሎ፤ ተቆጣጥሮ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ መተሳሰሪያ ያንድነቱን እትብት በጣጥሶ
እየጨረሰ ነው። ህዝቡ አንድ ቋንቋ እንዳይናገር የአማርኛን ብሄራዊ ቋንቋነት ሰርዞ፤ የህዝቡን ህጋዊና ታሪካዊ የባለቤትነት መብት
በሀይል አግዶ የባህር በር እንዳይኖር አሰብን ለጠላት ሰቶ፤ ምእራቡን የኢትዮጵያ ክፍል አንድሺህ ስድስት መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት
ከሰላሳ እስክ ስልሳ ኪሎሜትር ስፋት ለሱዳን ሰቶ፤ መላውን ህዝብ ከየቀየው እያፈናቀለ፤ እያሳደደ፤ እየገደለ፤ ወህኒ እያጎረ የሀገሪቱን
ለም የርሻ መሬት ለባእዳን በርካሽ እየቸበቸበ፤ ገንዘቡን እንደፈለገው እያደረገ መኖሩን ቀጥሏል። መላውን የሀገሪቱን ሀብት በህውሀት
ቡድን መዳፍ ውስጥ አስገብቶ፤ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መለያ የሆኑ ባህላዊ፤ ታሪካዊ፤ ሀይማኖታዊ ውርስና ቅርሶችን ሁሉ
አውድሞ፤ ገዳማትን አፍርሶ፤ ሀውልቶችን ነቅሎ፤ ታሪካዊና መታሰቢያ ስሞችን ሁሉ ለውጦ፤ ሀይማኖታትን አርክሶ ክልሶ፤ ከፋፍሎበጣብጦ፤ አበጣብጦ፤ የነበረውን ሊያጠፋ ያልነበረውን ሀይማኖት ከየትም ፈልጎ እያመጣ፤ ህዝብ ላይ እያጣበቀ እየጫነ፤ ሌላም ሌላ
....የጥፋት ጎዞውን ያለ እንቅፋት ቀጥሏል።
እርግጥ ነው ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለወያኔ እጅግ የሚያስፈራውና የሚያሳስበው የማይናወጥ አንድ አቋም እንዳለው በተደጋጋሚ
አጋጣሚውን ሲያገኝ አሳይቷል። ወያኔ እንደማናቸውም ቅኝ ገዢዎች ሁሉ ማናቸውንም ዋጋ ከፍሎ እየሰራበት ያለው ከፋፍሎ
የመግዛት ዘይቤ፤ ይህ ቡድን በገመተው ልክ የኢትዮጵያን ህዝብ አልከፋፈለለትም። ከስምንት አመት አገዳ በሁዋላ በቅርቡ ለሙከራ
የተጀመሩት ሰላማዊ ሰልፎች፤ ያዲስ አበባውም የወሎውም የጎንደሩም ሁሉም ያረጋገጠው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ከሀያ ሁለት
አመታት በፊት የነበረ አብሮነቱን፤ እንድነቱን ምንጊዜም ከልቡ እንደማያወጣው ነው።
አዎ የኢትዮጵያ ህዝብ ለየብቻው እንዲሆን፤ ለየብቻው እንዲያስብ፤ ለየብቻው እንዲናገር፤ በሀይል ተከልሎ ታጥሯል። ከስድስት መቶ
አመታት በላይ የጋራ መግባቢያ የነበረውን የአማርኛ ቋንቋ ሁሉም ክልል እናዳይናገር ተከልክሏል። ህጻናት የራሳቸውን ቋንቋ ብቻ
እየተናገሩ እንዲያድጉና እንዲማሩ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚያገናኛቸው ሌላ ቋንቋ እንዳይማሩ ተደርገዋል። የወያኔ ትልሙ
ከኢትዮጵያ ህዝብ በብዛቱ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘውን ወጣት በሀምሳ አመት ውስጥ እንደጋሪ ፈረስ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚያይ
አድርጎ ከፈጠረው፤ የሚያስተሳስረው ቋንቋ፤ ባህል፤ ታሪክ፤ የጋራ ሀገር ካሳጣው በቀላሉ ይበተናል፤ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አትኖርም
ነው። ኢትዮጵያ ግን በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ አንድነቷን ጠብቃ ለዘለአለም ትኖራለች። በወያኔ ፋሺሽቶች ከርሰ መቃብር ላይም
በልጆቿ አንድነት አንዲት ሀያል ኢትዮጵያ ዳግም ትነሳለች።
ወያኔ የያዘውን ስልጣን ተቆጣጥሮ እስከመጨረሻው ለመዝለቅ የሚያስችለው እርግጠኛ የሆነበት ሌላው በተግባር ያዋለው ዘዴ፤ ጦር
ሀይሉን ደህንነቱና ፖሊሱን በራሱ ሰዎች ማስይዙ እንዳለ ሆኖ፤ የህውሀት የጦር አለቆች ቀጥተኛ የሀገሪቱ ሀብት ባለድርሻ መሆናቸው
ነው። በዛሬዋ ዓለም ምንም አይነት የተለየ ሞያ ሳይኖረው፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጣ ለግሉ ህንጻ መገንባት የቻለ፤
በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በኢንቨስትመንት የሚያንቀሳቅ ጀነራል፤ ኮሎኔል፤ ሻለቃ ወዘተ....የሚባል፤ ስራ ላይ ያለ ወታደር ያላት
ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች። እነዚህ ባለሀብት መኮንኖች የኛ ነው የሚሉት መንግስት እንኳ ለለውጥ ቢነሳና ያ ለውጥ ይህን ያለ አግባብ
በጃቸው ያከማቹትን ሀብት ያሳጣናል ብለው ከሰጉ ፤ የወያኔ ጀነራሎች ከላይ ያለውን የወያኔ አካል በሀይል አስወግድው ራሳቸው
ስልጣኑን እንደሚይዙት ልንጠራጠር አይገባም። ስለዚህ ሁሉም የህውሀት አመራር በየፈርጁ ለራሱ ህልውና ሲል በስነስርአት የሀገሪቱን
ሀብት እየዘረፈና እየተከፋፈለ በመኖር ላይ ይገኛል። ህዝብ ለለውጥ ልነሳ ካለ እስካሁን እያደረገ እንዳለው ማናቸውንም ወታደራዊና
አስተዳደራዊ እርምጃ እየወሰደ ይቀጥላል። እነዚህን በሀገር ሀብት ዘረፋ የደለቡ ደናቁርት የወያኔ ነፍሰገዳይ የጦር አለቆች፤ ከታች ያለው
የሰፊው ህዝብ ልጅ የሆነው መለዮ ለባሽ ካላመጸና እግር ተወርች እያሰረ ለፍርድ ካላቀረባቸው፤ ግደል ባሉት ቁጥር የራሱን ቤተሰብ
እየገደለ፤ የወገኖቹን ደም እያፈሰሰ እነሱ እየበለጸጉ መኖር እንዲቀጥሉ፤ ስርአቱም በጥቂት የአንድ ጎሳ አባላት የበላይነት ተገንብቶ
እንዲቀጥል ከፈቀደላቸው ይህች ሀገርና ይህ ህዝብ ፍዳቸው ይቀጥላል።
የጦር አዛዦቹ የሀብት ምንጭ ማእከላዊ መንግስቱ ብቻ አይደለም። የየክልል አሻንጉሊቶቻቸው ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ። አሰራሩ
እንዲህ ነው። በአራቱም የሀገሪቱ ማእዘናት የጦር እዝ ማእክሎች ይገኛሉ ። የዚያን አካባቢ እዝ የሚያዙት የህውሀት ጀነራሎች
ስራቸው፤ ጦሩን ማንቀሳቀስና መምራት ማዘዝ ብቻ አይደለም። ባካባቢያቸው ያሉ ክልሎችን ለምልክት ካስቀመጧቸው የክልል
ፕሬዚደንቶች ጀርባ ሁነው፤ ክልሉን ያስተዳድራሉ። ይመራሉ። ሹማምንቱን ይቆጣጠራሉ። ያዛሉ። ከማእከላዊ መንግስት የሚለቀቀውን
በጀት ያውቃሉ፤ ይቆጣጠራሉ።
ምሳሌ.... ሀረር ከተማ መቀመጫውን ያደረገው የምስራቅ እዝ አዛዥ ጀነራል፤ የሀረሪ ክልላዊ መንግስትና የሱማሌ ክልላዊ መንግስት
ባለስልጣናትን ያዛል፤ ይቆጣጠራል። በየአመቱ የክልሎች በጀት እንደተለቀቀ የህውሀት ኩባንያዎች በያቅጣጫው አብረው ይለቀቃሉ።
በየክልሉ በበጀት አመቱ ይሰራሉ የተባሉትን አንዳንድ ነገሮች ተሻምተው ይከፋፈላሉ። ከባጀቱ የተወሰነውን ይወስዳሉ። ከዚያ የተወሰነ
መጠን የክልልሉ ሹማምንት እንዲበሉ ይደረጋል። ይህም የሚደረገው በኮረብሽን እንዲነካኩና የሚታዘዙትን አንፈጽም ካሉ በቀላሉ
እስር ቤት ተወርውረው ሌላ ማስቀመጥ እንዲቻል ነው። ይህን ሁሉ በንቃት ይሚያስፈጽመው የወያኔ ጀነራል፡ ኮሎኔል፡ ወይም
ሻለቃም ሊሆን ይችላል። በክልሉ ለምልክት የሚሆኑ ጥቂት ስራዎች እንዲሰሩ ያ የወያኔ አዛዥ ከተከታተለ በኋላ የተጋነኑና የውሸት
ሪፖርቶች እንዲዘጋጁ ይደረጋል። የዚያ ክልል ፕሬዚዳንት የተረፈውን ገንዘብ ይዞ ወደ ጀነራሉ ቢሮ እንዲመጣ ይታዘዛል። ያንን
ገንዘብ የተረከበው ጀነራል የሚበቃውንና የሚፈልገውን ያህል ወደ ግል ባንኩ ካስገባ በኋላ፤ ለሌሎቹ ማካፈል ካለበትም የሚያደርገውን
ራሱ ይወስናል።
ለዚህም ነው ኢትዮጵያን የወረሯት አዛዥ የትግራይ ታጋዮች በሙሉ በኢንቨስትመንትና በግንባታ ላይ የተሰማሩት፡፡ ለዚህም ነው
እስከመጨረሻው እየገደሉ ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ እንጂ ሰላማዊ ትግል በሚል ጨዋታ እጃቸው የገባውን ስልጣን አሳልፈው
የማይሰጡት።ምንድነው መደረግ ያለበት?
ይህን በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ ተዳፍኖ ያለውን የአንድነትና የትግል ስሜት ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ ከንግዲህ በኋላ ጊዜ
የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። አብረው ሲጋፈጡት ሞትም አይከብድም። አንዱ አደባባይ ወቶ የተቃውሞ ጩኸቱን ሲያስማ ሌላው
በፍርሀት ቤቱ ተሸሽጎ አጨንቁሮ በመስኮትና በበሩ ቀዳዳ የሚያይበት ሁኔታ ዛሬ ላይ መቆም አለበት።
ከዚህ መንግስት ጋር በሙሉ ልብ ለስርአቱ እድሜ መራዘም እየሰራችሁ ያላቸሁ ምሁራን፤ በኢትዮጵያ ህዝብና በሀገሪቱ ላይ እየደረሰ
ያለው አፈና፤ ሰብአዊ መብት ረገጣና ግፍ፤ ትክክል አለመሆኑ ሳይገባችሁ ቀርቶ ሳይሆን ህሊናን ለጥቅም አሳልፎ የመሸጥ ጉዳይ ነው
ችግራችሁ። ግልጽ ነው። እርግጥ ተፈጥሮን ተመክሮ ላያድነው ይችላል። አንድ ሰው በተፈጥሮው ራስ ወዳድ፤ ውሸታም፤ ሌባ፤ መስሎ
አዳሪ፤ ጥቅም እንጂ ሰብአዊ ርህራሄ የማያውቅ ከሆነ፤ ለራሱ የሚጠቅመውን ነገር ካተረፈ፤ ህዝብ ያስፈጃል፤ ግፍም ይፈጽማል።
ስለዚህ እናንት ከወያኔ ጋር የተለጠፋችሁ ቅጥረኛ ምሁራን፤ አማራ፤ ኦሮሞ፤ ደቡብ ወዘተ....ወያኔ ባላሰባችሁት ሁኔታ እያንዳንዳችሁን
በልቶ እንደሚጨርሳችሁ ከወዲሁ ተገንዝባችሁ፤ የተጠቀማችሁትን ተጠቅማችኋል፤ የያዛችሁትን ይዛችሁ እራሳችሁን ከወያኔ መንግስት
አግልሉ። የነጻነቱን ትግል ተቀላቀሉ። የበደላችሁትን ህዝብ ካሱ።
ሌሎቻችሁ በተቃዋሚውም ወገን በደጋፊውም ወገን ሳትሆኑ፤ መሀል ላይ ተደላድላችሁ፤ ድምጣችሁን አጥፍታችሁ፤ አድፍጣችሁ፤
በቀጥታ እናንተ ላይ ስላልደረስ ብቻ በሀገር በወገን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንዳላየ እንዳልሰማ ሁናችሁ፤ በራሳችሁ ህይወትና ምቾት
ዙሪያ እየተሽከረከራችሁ ይህችን ቀውጢ ቀን ለማሳለፍ የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ይህ መሀል ሰፋሪነት ያስገኘላችሁ ሰላም ነገ ጠዋት
ይደፈርሳል። ህዝብን እየጨፈጨፍኩ መግዛቴን እቀጥላለሁ ብሎ የቆረጠ ነፍሰ ገዳይ መንግስት ባለበት ሀገር ውስጥ የናንተ ሰላም
አይዘልቅም። በህዝባዊ ትግል የቆሰለ መንግስት እንዳበደ ውሻ ባጠገቡ ያየውን ሁሉ ነው የሚቦጭቀው። አካሉንም ሳይቀር ስለዚህ....
ስለዚህ ከመሀል ውጡና ህዝቡ እንደሚሆነው ሁኑ። የህዝቡን የተቃውሞ ድምጽ አበራክቱ።
በተራ ወታደርነትና የበታች መኮንንነት ደረጃ ያላችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ ይህ እንደከብት እየነዳ የሚያዛችሁ የወያኔ ታጋይ
አዛዥ ከናንተ የበለጠ አዋቂ፤ ከናንተ የበለጠ ጀግና አይደለም። ቀን ያነሳው የመሀይም ሽፍታ ጥርቅም ነው። የአንድ መንደር ምልምል
ነው። እናንተ ግን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ናችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ቤተሰባችሁን የኑሮ ውድነት እየጠበሰው፤ የወያኔ
አመራሮችና ታጋይ ጀነራሎች እንዲሁም ቅጥረኞቻቸው በሚሊዮን ዶላር ንግድ ተሰማርተው የአለም ሀብታም ሰዎች እንደሚኖሩት
ይኖራሉ። በናንተ ደምም ይነግዳሉ። ለምሆኑ እናንተ ለሰላም ማስከበር ተልኮ ሩዋንዳ፤ ሶማሌ፤ ሱዳን፤ እየሄዳችሁ ስትሞቱ የተባበሩት
መንግስታት ለያንዳንዱ ወታደር የሚከፍለውን ወፍራም አበል ተቀብላችሁ ወደ ቤተሰብ ልካችሁ ታውቃላችሁ? ስንቶቻችሁስ ናችሁ
የተባበሩት መንግስታት ለናንተ አበል እንደሚከፍል የምታውቁ? የወያኔ ታጋይ አዛዦች ተቀብለው ወዴት እንደሚያደርሱትስ
የምታውቁት ነገር አለ?
አንድ ወታደር በህዝብ ላይ አደጋ እንዲያደርስ ቢታዘዝ ያለቃውን ትዛዝ አልቀበልም የማለት የሞራልና የህግ መሰረት እንዳለው
ይታወቃል። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ እያስገደለ፤ እስከመቼ ድረስ ነው ረግጦ የሚገዛውና የሀገሪቱን ሀብት
የሚያጋብሰው? ወጣቱ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት እንደ ግብጽ፤ እንደቱኒዚያ ሰራዊት ከሀገርና ከህዝብ ጎን መቆም ይጠበቅበታል። የአንባ
ገነኖች ደህንነት ሳይሆን የሀገርና የህዝብ ደህንነት ነው የሀገር ፍቅር ላለው ሰራዊት ቅድሚያ የሚኖረው። ሀይል በጁ ነው። የህውሀትን
ታጋይ አዛዦች ሰብስቦ ወደ እስር ቤት ማጎርና ስልጣኑ ላይ ያሉትን አሽመድምዶ፤ ለህዝቡ የምርጫ ነጻነት መስጠት ያስፈልጋል። ህዝቡ
በቶሎ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት አቋቁሞ፤ ለመደበኛ ምርጫ ሰላማዊ ስራ እንዲሰራ ማድረግና ከውስጥም ከውጭም ለሚነሱ የሀገር
ጠላቶች ምላሽ ለመስጠት መሰማራት ያስፈልጋል።
ተቃዋሚ ነን የምትሉ ድርጅቶም አንዱ ያንዱን ጥረትና ትግል እያንኳሰሰ፤ ራሱን እያወደሰ ፤ እርስ በርስ መናቆር ከቀጠለ አተካራችሁ
የኢትዮጵያን ህዝብ ጥርጣሬና ውዥንብር ውስጥ ስለሚከተው አንዳችሁንም አያምን። አንዳችሁንም አይከተል። መጀመሪያ ለራሳችሁ
ተከባበሩ። ተባበሩ። አንዲት ጎጆ ለመገንባት አብረው የተሰማሩ ሰዎች ሳር አይሻማሙም ይባላል። የሁላችሁም አላማና ግብ ወያኔን
አስወግዶ አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት እስከሆነ ድረስ፤ የተለማችሁት ዘዴና አካሄድ መለያየቱ የሚጠበቅና
መሆንም፤ መኖርም ያለበት አማራጭ ነው እንጂ፤ አንዳችሁን ካንዳችሁ የሚያባላ የማይታረቅ ልዩነት አይደለም። በማይረባ ጥቃቅን
ልዩነት በህዝብ ፊት ስትናቆሩ፤ ህዝቡ ሁላችሁንም አንቅሮ ተፍቶ፤ ከራሱ ውስጥ የሚያታግሉትን ሰዎች አውጥቶ ትግሉን ይቀጥላል።
ያከመሆኑ በፊት ግን ተከባብራችሁ፤ ተባብራችሁ ህዝቡን በማስተባበር የለውጥ እንቅስቃሴውን አፋጥኑ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ወያኔ ሀገር እያሳጣችሁ፤ ተስፋ እያሳጣችሁ በመጓዝ ላይ መኖሩን ሳትዘነጉ፤ ራሳችሁንና ሀገራችሁን ህዝባችሁን
ለማዳን ተነሱ።
በጫትና በሀሺሽ፤ በአልኮል ናላችሁን የምታዞሩ፤ ገሚሶቻችሁም የሀገር ፍቅርን ስሜትና የትግልን ስሜት በሚያኮላሹ ሀይማኖቶች
ተተብትባችሁ፤ በእውን ለምትኖሩበት የምድር ፈተና መፍትሄ እንደመፈለግ ከሞት በኋላ ስለምታገኙት ህይወትና ሞቾት ስትቃዡ፤ ጌታጌታ እያላችሁ በየ አጥቢያው ስታላዝኑ ወያኔ ምድሪቱን በላያችሁ ላይ እየሸጣት ነው። ከጴንጤውም ከጆቫውም ከሌላውም የቅዥት
አለም ውስጥ ውጡና እናት ሀገራችሁ ኢትዮጵያን ከአርባ ጊዜ በላይ የሚጠራት መጽሀፍ ቅዱሳችንን ይዛችሁ፤ ለትግል የቆረጡ
ወጣቶችን ተቀላቀሉ።
ኢትዮጵያ ዳግም ትነሳለች!
ሞት ለወያኔ!
lkebede10@gmail.com
ኢትዮሚድያ - August 8, 2013
Ethiomedia.com

No comments:

Post a Comment