Sunday, August 11, 2013

“የሽመልስ ከማል እና የዳንኤል ብርሃነ መመሳሰል”

“እዉነት አርነት ያወጣችኋል”
አብዲሳ አጋ(ገሞራዉ)
ትናነት ማታ በኢቲቪ ህትመት ዳሰሳ የቀረበዉ የኢህአዴግ ቀንደኛ ደጋፊ የሳይበሩ ሰላይ ዳንኤል ብርሃነ፡፡
ስለ ሙስሊሞች ጥያቄ አንስቶ በሰፊዉ ፈር ባልያዘ ነገር ሲለፈልፍ ነበር አሁን እሱ ባነሳዉ ነገር ላይ ለመናገር ፈልጌ ነዉ፡፡
ስለ ሙስሊሞች እንቅስቀሴ ተጠይቆ እነዲህ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 1ሚሊዮን ፌስቡክ የሚጠቀም ሲሆን ከእዚህ ዉስጥ ግን 5ሺ ነዉ በንቃት ፖለቲካ የሚከታተለዉ፡፡
የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ እየመራዉ ያለዉ ድምጻችን ይሰማ ነዉ፡፡ በፌስቡክ ከ40ሺ በላይ ተከታይ የላቸዉም፡፡ ግን የኢህአዴግ መሪዎች እና ደጋፊዎች እርስ በርስ የሚጣረስ ነገር ካልተናገሩ ያወሩ አይመስላቸዉም እንዴ፡፡ይህ ምንን ያመለክታል ብለህ ታስባለህ፡፡ በጣም ጥቂት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ይህም የሙስሊም መንግስት ለመመስረት እየተንቀሳቁ ያሉት፡፡ ከቻሉ ለምን ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ዉህደት አይፈጥሩም የሚል ስላቅም ተናግሯል፡፡ ዳንኤል “ምሳሌ ሁሉ ሽባ ነዉ”
እዉነት ዳንኤል ሙስሊሞች ጥቂት እንዳልሆኑ በረከት ስምዖንም፣ ሽመልስ ከማልን አንተም እራስ የምታዉቁ ነገር ነዉ፡፡
“ከሃቅ ፍቅር እንጂ ዉርደት አይገኝም”
የሙስሊሞች ፍላጎት በራሳቸዉ በሙስሊሞች ብቻ ሊፈታ የሚችሉ ለዚህ ሁኔታ የተመቻቸና የተሟላ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እና የሃይማኖት ነፃነት ሲኖር ነዉ፡፡ የዲሞክራሲ አገዛዝ የመርህ፣ የፍትህና የነፃነት አገዛዝ ነዉ፡፡ የዜጎች እኩልነት መከበሩ ለሀገር አንድነት መሰረት ነዉ፡፡ከሃይማኖታቸዉ ማንነት በመነሳት ከአክራሪነት ኋይሎች ጋር እና ከፖለቲካ ድርጀቶች አቋሞች ጋር በማላከክ በጸረ-ህዝብነት ፈርጆች ዉስጥ ማቅረብ አደገኛ አዝማሚያ ነዉ፡፡የሁሉም የሃይማኖት እምነት አቋም መከበር ይኖርበታል፡፡የተከተሉት መንገድ እና ጥያቄ የተሳሳተ እንኳን ቢሆን ስህተተኝነቱን ግልጽ ከማድረግ ዉጭ አዋራጅ ስድብና ወታደራዊ እርምጃ አስፈላጊ አይደለም፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ የራሱን ጥያቄ፣ አቋምና እምነት ይዘዉ በሰላማዊ መንገድ ከአንድ ዓመት በላይ መንግስት እየተቃወሙ ያሉት ለዚህ ነዉ፡፡ በኢትዮጰያ ዉስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እና የሃይማኖት ነፃነት አለ እየተባለ በሌላ በኩል ጠብመንጃ ይዞ ላይና ታች ዞር ዞር ማለት እርስ በርሱ የሚቃረርን አሰራር ነዉ፡፡ በጣም የሚገርመዉ በተለይ ኢህአዴግ የሙስሊሞችን ጥያቄዎች ላይ የወደሰዉ አቋም ለእነርሱ እጅግ አክራሪና የስልጣን ጥያቄ የሚያነሳ ነዉ በሚል ነዉ፡፡ በህዝቡ የተደነገገ ህገ-መንግስት አለ ይላሉ፡፡ የሐይማኖት ነፃነት ሲነሳ ግን ጨዋታ እና ቀልድ ያረጉታል፡፡ ያለእዉነተኛና ተግባራዊ ዲሞክራሲያዊና የሐይማኖት ነፃነት ዕድል በራስ መወሰን መብት ባዶና ትርጉም የለሽ ነዉ፡፡ በህገ-መንግስቱ የተደነገገዉ መብት የወረቀት ላይ ጌጥ የሚያደርግና የሕዝቦች መብት የተከበረ የሚያስመስል ስልት ነዉ፡፡
አንዳንዶቹ ሶሻል ሚዳያዉን እና ኤሌክትሮኒክስ ሜዳያዉን ለማይገባ አገልግሎት ሲያዉሉት እያስተዋልናቸዉ ነዉ፡፡ ለአንዳንዶቹ የፕሬስ ነፃነት በርካሽ ባህሎችና በሕዝብ ስነ ልቦና በሚረብሹ የመነገድ ተራ የጥቅም እንቅስቃሴ ነዉ፡፡ መንግስት በራሱ ሚዲያ በመጠቀም ዲሞክራሲን ገድሏል፡፡
ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የመገናኛ ብዙሐንን(ሬድዮ፣ ጋዜጣና ቴሌቪዥን) ከመንግስት ይዞታና ቁጥጥር ነፃ መዉጣት አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይህ ወሳኝ እርምጃ ነዉ፡፡ዛሬ በግልጽ እንደሚታየዉ የኢህአዴግ መንግስት እንደቀደምት መንግስታት የመገናኛ ብዙሐንን በግል ይዞአቸዋል፡፡ የሚገለገልባቸዉ ለራሱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ነዉ፡፡ መንግስት ጋዜጠኞችን ቀጥ እያሰራ ነዉ፡፡ ጋዜጠኞች ታዛዥ፣ ተቀጣሪ ነዉና የመንግስትን ኢ-ሰብአዊና አ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድ አይተችም፡፡ የባለስልጣናት ጥፋት ይፋ አያደርግም፡፡ በሚሰጠዉ መመሪያ መሰረት መስራት ግዴታዉ ነዉ፡፡ የሚሰጠዉን ሙያዊ ግዴታዉን ዘንግቶታል አጥፍቶታል፡፡
በዚህ ሁኔታስ እንዴት ዲሞክራሲ ስርዓት እንዴት ሊያብብ ይችላል?
ማበብ ይችል ዘንድ መሰረቱ መቼ ተጣለ ?
ለዲሞክራሲ ላንቃቸዉ እስኪሰነጠቅ ይጮሃሉ፡፡ በሌላ በኩል የማፈኛ መዋቅራቸዉን ያስፋፋሉ፡፡
ከላይ የሁሉም ችግሮች ምንጭ የዲሞክራሲ አለመኖር ነዉ፡፡
“ቀበሮ የበግ ቆዳ ስለለበሰች በግ አትሆንም”
የዛሬን በዚህ አበቃዉ!!!
Bitania Alemayehu

No comments:

Post a Comment