Sunday, August 4, 2013

ኮፈሌ በ ንጹሃን ደም ታጠበች! ቁጥሩ የበዛ ሰው ተገሏል

የ ኮፈሌ ወንድሞቻችን በ ወያኔ ቡችሎች ሲገደሉ ሲደበደቡና ሲታፈሱ ውለዋል፦ ምንም ላልታጠቁ ንጹሃን በ ታንክ የታገዘ 40 ኦራል ሰራዊት ቃታውን ሳበ። የሟቾች ቁጥርም 25ደርሷል :: 1500 ሰዎች ታስረዋል :: ሆስፒታሎች በ ቁስለኞች ሞልተዋል የ ሟቾች አስከሬን ከ መስጊዶች እንዳይወጣ ተከልክሏል ። ፌደራሎች ያገኙትን መኪና መስተዋት ይሰብራሉ። ETVም የተለመደ ድራማውን ሲሰራ ዋለ።
በኢትዮጵያዊው ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በርትቷል:: እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በወገኑ ላይ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና ሰቆቃ ወከባ ግድያ ሊያሳስበው እና ሊያወግዘው ይገባል ::አንድነት ሃይል ነው:: ከሙስሊም ወገኖቻችን ጎን መቆም የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብት እና ግዴታ ነው:: ነግ በኔ ነውና:: ምስሉ ላይ የምትመለከቱት ፖሊሶች እና የአግኣዚ ወታደሮች ሙስሊሙን ወገን ሲደበድቡ ሲያፍሱ እና ሲያዋክቡ ነው::

No comments:

Post a Comment