Monday, August 19, 2013

ከሦስት ጊዜ በላይ የሞተ ብቸኛው የሀገር መሪ

ይሄይስ አእምሮ
ወቅቱ በኦርቶዶክሳውያንና በኢትዮጵያውያን ካቶሊኮች ዘንድ የፍልሰታ ለማርያም የፆምና የሱባኤ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ለየት ባለ የሱባኤ ወቅት ለምንገኝ ወገኖች ፈጣሪ የልባችንን መሻት ተረድቶ የዘመናት ህልማችንን በቅርብ እውን ያድርግልን፤ የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ ጸሎት ምህላችንን ሰምቶ ከነዚህ ሽል መንጣሪዎች፣ ከነዚህ የሰው ግርድ እና አመሳሶ አውጪዎች ይገላግለን፡፡ የእስላም የክርስቲያኑን ዕንባ ተመልክቶ ከነዚህ ሰው በላዎች ነጻ የምንወጣበትን መንገድ ያሳየን፡፡ በመካከላችን የቆመ የሚመስለውን ጽልመተ መንጦላዕት ይበጣጥስልንና ወያኔ የዘራውን የልዩነት አዝርዕት ሁሉ ይመነቃቅርልን፡፡
ሰው ስንት ጊዜ ይሞታል? ብለን ብንጠይቅ እንደየአመለካከታችን የተለያዩ መልሶችን የምናገኝ ይመስለኛል፡፡ የመልሶቻችን መለያየት መሠረትም ለሞት ያለን ግምትና የምንሰጠው ፍቺ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ‹መለስ ዜናዊ ስንት ጊዜ ሞተ?› ለሚለው ጥያቄ መልስ እኔን ጨምሮ ብዙዎች የሚቃወሙት ሰዎች ከሦስት ጊዜ በላይ እንደሆነ ቢናገሩ እንደአካሄድ ትክክል ናቸው፡፡ እመለስበታለሁ፡፡
አንዲት ማሳሰቢያ ቢጤ ጣል ባደርግ ደስ ይለኛል፡፡ ይህን ጽሑፍ ሃይማኖት የሌለው ሰው፣ በ‹paranormal and/or parapsychology› ኅልውና የማያምን ሰው፣ እምቦቀቅላው ሣይንስ አምስቱን የስሜት ሕዋሳት ብቻ ተመርኩዞ ከሚሰጠው መረጃ ውጪ ሌላ ሃሳብ የማይቀበል ዝግ ሰው እንዳያነብ እመክራለሁ፡፡ (የቅንፍ ሰበር ሃሳብ! በሞስኮ ኦሎምክ የ1500ኪ.ሜ ሩጫ አሁን እየተካሄደ ነው – ልክ አሁን፡፡ መጻፌን ቆም አድርጌ ይህችን አጭር ሩጫ ጨረስኳት፡፡ በውጤቱ ግን አዘንኩ – ወልዶ ለሰው መገበር የማይሰለቻት ሀገራችንም አሳዘነችኝ፡፡ ይህን ሩጫ በአንደኛነት ያሸነፈችው ‹ስዊድናዊት› አበባ አረጋዊም አሳዘነችኝ፡፡ በዚህ ውድድር 8ኛ ሆና የጨረሰችው ተወዳዳሪ ገንዘቤ ዲባባም በሀገሯ ልጅ በ‹ስዊድናዊቷ› አበባ አረጋዊ በሰፊ ልዩነት መሸነፏም አስተከዘኝ፡፡ አበባ ድሏን ለ‹ዜጎቿ› ለመግለጽ ባንዲራየ ብላ የያዘችውን የስዊድን ሰንደቅ ዓላማ ስታውለበልብ የተሰማኝ ስሜትም የተለዬ ነው – የሰው ወርቅ ላያደምቅ ዘመን በፈጠረው የኢትዮጵያውያን ተከፍሎ ሊያልቅ ያልቻለ የትውልድ ዕዳ ምክንያት ዜጎቻችን ከችግርና ከፍትህ አልባ መንግሥታዊ አሠራር ለማምለጥ ሲሉ የገቡበትን የሥነ ልቦናና የፖለቲካ ቀውስ በዚህ አጋጣሚ ሳስበውና ከስድስት ወራት ገደማ በፊት በተሰጣት የሁለትዮሽ ጠቀሜታ ባለው ዜግነት ምክንያት አበባ ሌላ ባንዲራ ስታውለበልብ ሳያት በእውነቱ ጥልቅ የሀዘን ስሜት ተሰማኝ፡፡ መቼ ይሆን ሀገራችን የወላድ መካንነቷ የሚያቆመው? በነገራችን ላይ የአበባ ችግር በሀገራችን ከነገሠው የዘረኝነት ልክፍት ጋር እንደማይገናኝ የታወቀ ነው – ምክንያቱም ልጂቷ ትግሬ በመሆኗ በዚያ በኩል የትግሬው መንግሥት ሊታማ እንደማይችል እረዳለሁ፡፡ ችግሩ ሌላ መሆኑ ሲወራ ሰምቻለሁ፡፡ ለነገሩ በስፖርቱ መንደርም የጎሣው ተዋፅዖ ትልቁ የድቀታችን መንስኤ መሆኑን አንረሳም፡፡)
ወደቀደመው ነገራችን እንግባ፡፡ ፍቼ አካባቢ የተፈጸመ እውነተኛ ታሪክ ላስታውሳችሁ፡፡ ጊዜው ራቅ ይላል – ግን በደርግ ዘመን ነው፡፡ አንዲት ተማሪ በጠና ትታመማለች፡፡ ያን ተከትሎም ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ትወሰዳለች፡፡ በህክምና ብዙ ብትረዳም ሕይወቷ ሊተርፍ አልቻለም፡፡ አስከሬን ለቀብር ወደፍቼ ይመለሳል፡፡ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ቤተሰብና የአካባቢው ሕዝብ በተገኙበት የቀብር ሥነ ሥርዓቷ ሊፈጸም ሲል አንድ አስደናቂ ነገር ይከሰታል፡፡ ካህኑ ጸሎታቸውን ጨርሰው ሣጥኑ ወደተዘጋጀው ጉድጓድ ሊገባ ተሸካሚ ሰዎች ሲጠጉ ሬሣው ከውስጥ መንቀሳቀስ ይጀምራል፡፡ ከሞተች ከሦስት ቀናት በላይ የሆናት፣ በፎርማሊንና በልዩ ልዩ ሕክምናዊ መነካካት ከሬሣነት ተራ የወጣው የዚያች ተማሪ አስከሬን ሲከፈት ተማሪዋ ቁጭ ትላለች፡፡ ቀባሪዎች ይደነግጣሉ፡፡ ሁሉም በሽብርና በጭንቀት ይዋጣል፡፡ የደፈሩ ሰዎች ልብስ ያለብሷታል፤ ካህናትም ያናግሯታል፡፡ ተመልሳ ጤናማ ትሆንና ንግግርም ትጀምራለች፤ የተናገረችው ግን ‹ንስሃ ግቡ! ኃጢኣት አትስሩ› የሚል ብቻ ይሆናል፡፡ ‹ሌላ ነገር እንድናገር አልተፈቀደልኝም›በማለትም ቁርጡን ታሳውቃለች – ይጎርፉላት የጀመሩትን በርካታ ጥያቄዎች ለማስቆም፡፡
እንደተረጋጋች – ባለፉ ቀናት ያስተናገደቻቸውን የተዘበራረቁ የሥጋ፣ የነፍስና የመንፈሳዊ ሕይወቶች መስመር ከያዙላት በኋላ ወደ ትምህርት ቤቷ ተመልሳ በህመሟና በሞቷ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርቷን ለመቀጠል ወደ ክፍል ትገባለች፡፡ ነገር ግን እርሷ ክፍል ገብታ ከመቀመጧ የክፍል ተማሪው ከክፍል ውልቅ ይልና ብቻዋን ትቀራለች፤ ምክንያቱም ተማሪዎች ያን ያልተለመደና አስደንጋጭ የ‹ከሞት በኋላ ሕይወት› አያውቁም ነበርና፡፡ በዚያም ሳቢያ ከክስተቱ ጋር በቀላሉ መለማመድ ስላቃታቸው የነበረው ብቸኛ አማራጭ ‹ሟች›ን ወደሌላ አካባቢ ወስዶ ማስተማር ነበርና እንዲያ ተደረገና ሕይወት ቀጠለች፡፡… እንዲህ ዓይነት ነገር በኢትዮጵያም በሌሎች ሀገሮችም በብዛት ባይሆንም እጅግ አልፎ አልፎ ይከሰታል፡፡ ማመን አለማመን የየራስ ድርሻ ነው፡፡
ካልሰለቻችሁ አንድ ልጨምር መሰለኝ፡፡ አንድ ሰው ለመስክ ሥራ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ይሄዳል፡፡ በሄደበት አካባቢ በቢጫ ወባ ይነደፋል፡፡ ወባዋ ለህክምናም ለታማሚም አስቸጋሪ እንደመሆኗ – በተለይ የተወሰነ ጊዜ ካለፈና በሰውነት ውስጥ ከተራባች  በኋላ – ጭንቅላቱ ውስጥ እንደገባችና እንደማይተርፍ ቤተሰቦቹ ሲነገራቸው ከክፍለ ሀገር ሆስፒታል ወደ አዲስ አበባ ያመጡታል፡፡ የሕክምና ዶክተር ጓደኛው ወደሚሠራበት አንድ የመንግሥት ሆስፒታልም ያስገቡታል፡፡ ያ ጓደኛው ከረዳቶቹ ጋር ጓደኛዊና ሙያዊ ልዩ ክብካቤውን ሲያደርግለት ውሎ ለተረኛው ዶክተርም ‹አደራህን፣ ዘመዴ ነው፤ በተቻለህ ሁሉ ርዳው፣ አንድ ነገር ቢከሰትም ቢሆንም እንኳን እኔ ሳልመጣ ወደሬሣ ክፍል እንዳትልከው እባክህን› በማለት የመዳን ተስፋ የሌለው መሆኑን ግን በልቦናው ተገንዝቦ ወደቤቱ ይሄዳል፡፡
ያ ጓደኛ የጠረጠረው አልቀረም፡፡ ጓደኛ ዶክተር ልብሱን ለውጦ ምናልባትም የሆስፒታሉን ዋና በር ብዙም ከመራቁ ሰውዬው ይሞታል፡፡ እስትንፋሱ ስለመቆሙና ስለመሞቱም የህክምና ሙያዊ ፍተሻ  ከተደረገ በኋላ የጓደኛውን ቃል ለማክበር ያልቻለው ተረኛ ዶክተር የሟችን ሬሣ ወደአስከሬን ክፍል ለክፈና ይልከዋል፡፡ በዚያም ከመሰል አስከሬኖች ጋር እንዲያድር አንዱ ፍርጎ ይሰጠዋል፡፡
በማግሥቱ የሬሣ ክፍል ሠራተኛው ሲገባ ግን ያ በቢጫ ወባ ሞተ የተባለ ሰውዬ መግነዙን ፈትቶ፣ የተተበተበበትን እሥራት ለመፍታት ባደረገው ጥረትም ፊቱን ቦጫጭሮ  ቁጭ ብሎ ይገኛል፡፡ ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ በእነማንና በምን ሁኔታ የት ደርሶም ለምን እንደተመለሰ ዝርዝሩ ብዙ ነውና ለአሁኑ አስፈላጊያችን ባለመሆኑ ይቅር፡፡ ግን ሰው በሥጋው ከሞተ በኋላም ሊመለስ እንደሚችልና ሌላ የመሞቻ ቀኑን የሚጠብቅ መሆኑን መረዳት የሚገባ መሆኑን አስምሬበት ልለፍ፡፡ ዓለማችን ብዙ ከአእምሮ በላይ የሆኑ ክንውኖችና ተዓምራት ቤተሙከራ ናት፡፡ ሣይንስ ደግሞ በዳዴ ደረጃ የሚገኝ ሕጻን ነው፡፡
በእማሬያዊ ትርጉም ሞት ማለት የነፍስና የሥጋ መለያየትና አንድ ሰው ከምድራዊ ሕይወት የሚሰናበትበት ሂደት ነው፡፡ በፍካሬያዊ ትርጉም ደግሞ አንድ ሰው በሕይወት እያለም ሆነ ከሞተ በኋላ በክፉ ሥራው ዘወትር ስሙ የሚወሳና ወደዚህች ምድር የመምጣቱ ምሥጢር ለዜጎች መሰቃየትና መበደል ከሆነ የሞት ሞት የሞተ ያህል ተቆጥሮ በታሪክና በትውልድ የሚኮነን ሆኖ በክፉ እየተዘከረ ይኖራል – ያም ከዋና አካላዊ ሞት በበለጠ እንደትልቅ ሞት ይታሰባልና ብዙዎች ሲሸሹት ይስተዋላል፡፡ አንዳንዶች ግን የክፋት ዕቅድና ትልማቸው እስከሰመረላቸው ድረስ ለዚህ ዓይነቱ ሞት ደንታ የላቸውም፡፡ ከዚህ አንጻር ዓለማችን የብዙ ባለመጥፎ ታሪክ ሰዎች ሥፍራ ስለሆነች ምሳሌ ለመጥቀስ የማንቸገርበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው በዘመናችን ጥሩ ሰው የማጣት ችግር እንጂ በጥባጭ የማጣት ችግር የለብንም፡፡ ዛሬ ዛሬማ ስሙን በክፋት መዝገብ ለማስከተብ የሚሯሯጠው የዓለም ዜጋ በጣም እየበዛ ነው፡፡
መለስ ዜናዊ በአካላዊ ሞት በትንሹ ሁለት ጊዜ ሞቷል፡፡ አንደኛው በኢሳት ቴሌቪዥን ቀድሞ የተገለጠው የሐምሌ 7 ቀን 2004 ዓ.ም በውስጥ ዐዋቂዎች ዘንድ እውነተኛ የሚባለው ሞቱ ሲሆን ሁለተኛው በኢቲቪ የተገለጠው የነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ሞቱ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሁለት ሞቶችን የተጎናጸፈ ብቸኛው የሀገርና የአንድ ብሔር መሪ ቢኖር መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ሁለቴ መሞት የሚቀናበት ከሆነ በርግጥም ያስቀናል፡፡ የሁለቱ ሞቶቹ የጊዜ ልዩነት ደግሞ ቀላል አይደለም – የአንድ ድፍን ወርና የስምንት ወይ የሰባት ቀናት ልዩነት ማለት በመካከሉ የሚሊዮኖች ዜጎች ሞት ወይ ልደትና ሠርግ የሚከናወንበት ረጂም ጊዜ ነው፡፡ የዚህ ልዩነት መፈጠር ምክንያት በወቅቱ በወያኔዎቹ በራሳቸውና ሪፖርተርንና አዲስ አድማስን በመሰሉ በወያኔያውያንና አሽቃባጭ ሚዲያዎች እንደተገለጠው  መለስ ዜናዊ ከበሽታው አገግሞ ወደቢሮው ለመግባት ሰውነቱን እያሟሟቀ ወይም በቤተ መንግሥት እልፍኝ ውስጥ ተቀምጦ ሱዳናውያኑን እያስታረቀ ሳይሆን ሞቱ ዱብ ዕዳ ስለነበር ቤታቸውን ለሀዘን አስተካክለው እስኪገኙ ድረስ ጊዜ ለመግዛት እንደነበረ ተረድተናል – አለበለዚያ ሌሊት ሞቶ ጧት ተነግሮ ወዲያውኑ ያ ሁሉ በብዙ ሺዎች የሚገመት ከናቴራና ኮፍያ ተሠርቶ ሊሠራጭና ቀድሞ በአባላት የተዘጋጀው ሀዘን ከመቅጽበት ተግባራዊ ሊሆን ባልቻለ ነበር (‹ጧት ተመርቶ ከሰዓት መርካቶ› ለ‹ላቭሊ› በስኩት የተሠራ ማስታወቂያ እንጂ ከዚህ በመኮረጅ ‹ሌሊት መለስ ሞቶ ጧት በምስሉ ከናቴራ ተሰፍቶ› ቢባል ግነቱ የዚያኛውን ያህል አይጥምም ብቻ ሣይሆን ማስታወቂያውን የሠሩትን እነበረከትንና ሽመልስ ከማልን ትዝብት ውስጥ ይጥላል – ትዝብት እሚባል ነገር አያውቁም እንጂ ደግነቱ) ፡፡ ያን ዓይነት ብልግና የተሞላበትና ከባህልም ከሃይማኖትም ከሞራልም ማዕቀፎች የወጣ  የሞተን ሰው ‹ሥራ ላይ ነው፤ ሽርሽር ላይ ነው፤ ኢሳት የፈጠራ ወሬ ነው ያወራው…› በማለት በእግዜር እጅ የተያዘ ሙት ሰው ላይ የማሾፍና የመቀለድ የቦዘኔ ሥራ መሥራትን የመረጡት እውነቱ መውጣቱ የሚቀር መስሏቸው ሣይሆን መራሩ መፃኢ ዕድላቸው አስጨንቋቸው ነው፡፡ ሰው መቼም ወዶ አንድን ሰው ሁለቴ አይገድልም፡፡ ወያኔዎች የሚያደርጉትን አያውቁም ነበር – አሁንም አያውቁም፡፡ የሸሹት እውነት ሮጦ ያዛቸውና የዛሬ ዓመት በዚህ ወቅት ገደማ የአናኮንዳውና ኮብራው ወያኔ መርዛማ ጭንቅላት ከእናት የዘንዶ ሰውነት መበጠሱን ሳይወዱ በግዳቸው ዐወጁ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላም ቆሌ ርቋቸው ይሄውና የፈጣሪ ፍርድ እውን እስክትሆን በስቃይና በጣር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍርዱ ትክክል የሆነው እግዚአብሔር ደግሞ ሰዓቷን ጠብቆ ሁሉንም የሥራቸውን እንደሚሰጣቸው የታመነ ነው፡፡ የውሻን ደም በከንቱ የማያስቀረው የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡
ይህችን የ2005ዓ.ም ፍልሰታ ብዙዎቻችን ተስፋ ጥለንባታል፡፡ በድረ ገፆች በቅርቡ ባነበብነውና ከበፊትም አንዳንዶቻችን ከአባቶች በሰማነው የትንቢት ቃል መሠረት  የኢትዮጵያ የዕዳ ደብዳቤ የሚቀደድበትና ሰላም በሀገራችን የሚሠፍንበት ዘመን እየመጣ እንደሆነ አምነን ጸሎታችንን እያቀረብን እንገኛለን፡፡ እግዚአብሔር ዐመፀኞችን እንደሚቀጣ ደግሞ ከጥንትም የታወቀ ነውና ብዙ ወደተገፋነው ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ ፊቱን እንደሚመልስልን በሙሉ ልብ እናምናለን፡፡ ይሆንልናል ብለን ካመንን ይሆንልናልና ተስፋችንን በርሱው እናድርግ ወገኖቼ፡፡ የእርሱ ፍርድ ደግሞ ይዘገያል እንጂ አይቀርም፡፡ ፍርዱ የሚዘገይ ወይም የሚቀር የሚመስላቸው ግን በሞኝነት ላይ ሞኝነትን እየደረቡ ለከፋ መለኮታዊ ቅጣት ይዳረጋሉ፡፡ ማንም ቢሆን የእጁን እንደማያጣ በመዘንጋትም አምላክን ይፈታተናሉ፡፡
ባጭሩ ለመከለስ ያህል ወያኔዎች የሚጠፉበትና ከነሰንኮፋቸው ተነቅለው የሚጣሉበት ምክንያት ብዙ ቢሆንም የተወሰኑትን ቀጥለን እናስታውሳለን፡፡
እስከዚህን ዘመን ባልታወቀ አዲስ አስተሳሰብ ተመርተው ሀገሪቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለዋል፤ ይህም ነገር ዜጎችን በተወሰነ ደረጃ አናቁሯል፤ ትዳርን እስከመበተንና ፖለቲካን አልጋ ውስጥ አምጥቶ እስከመነታክና እስከመጋደልም አድርሷል፡፡
ኢትዮጵያን ያለወደብ አስቀርተዋል፤ ለተባበሩት መንግሥታትም ደብዳቤ በመጻፍ በየትም የዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እናስተዳድረዋለን ከሚሉት ሀገር አንድን ግዛት ገንጥለው ራሳቸው ዕውቅና ከመስጠትና መተዳደሪያ የሚሆናትን የጎጆ መውጫ በጀት ከመመደብ ባለፈ በአፋጣኝ ዕውቅና እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም እነኚህ ኢትዮጵያን የያዙ የወያኔ ሰዎች ቅኝ ገዢዎች እንጂ የሀገሪቱ እውነተኛ ዜጎች አለመሆናቸውን በገሃድ አሳይተዋል፡፡ ኢትዮጵያን በዜግነት ሣይሆን ለጥቅም የያዘ አካል ደግሞ የጥፋት እንጂ የልማት ተልእኮ ሊኖረው አይችልምና እስካሁን ያደረጉት ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ ጭብጥ የተለዬ አይደለም፡፡ የሚታዩት አንዳንድ የልማት ውጥኖችና የመሠረ ልማት ዝርጋታዎችም ቢሆኑ የዕርዳታና ብድር ማወራረጃና የድጎማ ባጀትን ማስቀጠያ እንጂ እውነተኛና ሁሉን አቀፍ እንዳልሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በዚያ ላይ ለ23 ዓመታት ሥልጣን ላይ ለነበረ አካል እነዚህ በጎ ጅምሮች የእንፉቅቅ ያህል እንጂ አታሞ ሊደለቅላቸው የሚገቡ አይደሉም፡፡ በነዚህ ዓመታት ውስጥ በሙስና በሮች በባለሥልጣናት የተመዘበረው፣ ለመከላከያና ለደኅንነት የወጣው፣ ወያኔንና ቁንጮ ባለሥልጣናቱን ለመጠበቅ የተከሰከሰው፣ አለዕቅድ በየቦታው የባከነውና በወያኔ የንግድ ድርጅቶች የተመዘበረው የሀገር ሀብት በአንድነት ተደምሮ ሥራ ላይ ቢውል ይሄኔ ሀገራችን የት ልትደርስ እንደምትችል ስናስበው ትርፋችን ጸጸት ብቻ ነው፡፡
የከፋ ዘረኝነትና አፓርታይድ የሚያካሂዱ ናቸው፡፡ የነጭ በጥቁር ላይ አፓርይድ ከደቡብ አፍሪካ ሲባረር በቀጥታ የመጣው ወደኢትዮጵያ ነው፡፡ እዚህም መጥቶ ጥቁር በጥቁር ላይ፣ ወንድም በወንድም ላይ – ትግሬ በአማራና መሰል ምዝብር ሕዝብ ላይ የተጫነ በዓይነቱ አዲስ የሆነ አፓርታይድ በታሪክ ሊመዘገብ ችሏል፡፡ ይህ በኅቡዓን የዓለም ገዢ ኃይላት አማካይነት እየተጃገነና ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተሰጠው ሥልጣን ላይ የወጣ የኅቡዓን ኃይላት የኢትዮጵያ ክንፍ  (representative in Ethiopia of the secret lodges such as the Skull and Bones or the Order of Death) እንደነሱው ሁሉ ብዙኃንን በኃይል እየደቆሰ ወረደ መቃብራቸውን የሚያፋጥንና በምትኩም የጥቂቶችን የተንደላቀቀ ሕይወት የሚያረጋግጥ መሠሪ ቡድን ነው፡፡ ዋና ተልእኮው ብሔራዊ ስሜትን ማጥፋትና ሞራለቢስነትን ማስፋፋት በመጨረሻም የሉሲፈርን የጨለማ መንግሥት በምድር ላይ በግልጥ ማወጅ በመሆኑ ይህ ቡድን በሃይማኖቷና በባህሏ የታወቀችን አንዲት ታሪካዊት ሀገር በማጥፋቱ ረገድ በሙሉ ፈቃደኝነት በመተባበሩ እስካሁን ከየትኛውም ተፅዕኖ አሳዳሪ የውጭ መንግሥት አንዳችም ግልምጫ አልደረሰበትም፡፡ የወያኔ አፓርታዳዊ ሥራ ከደቡብ አፍሪካም እጅግ የከፋ ሆኖ ሳለ አንድም የውጭ አካል ሃይ ያለው የለም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በማንነት ጥያቄ ቀድሞውን ይንገላወድ የነበረው ይህ የወያኔ ቡድንና አመራሩ ምድራዊ የመብልና መጠጥ ፍላጎቶቹ እስከተሟሉለት ድረስ ለሰብኣዊና ኅሊናዊ ጤናማ ዕሤቶች ደንታቢስ በመሆኑና ለታሪካዊ የሰው ልጆች ጠላቶች ምቹ ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ነው፡፡ ለነሱ ባይመች ኖሮ እስካሁን ስንቴ ተቀያይሮ ነበር፡፡ ለማንኛውም ወያኔ የአፓርታይድ ታሪክ አስቀጣይ የዘመናችን ባንዳ ነው፡፡ የአመራሮቹ ጥንተ ታሪክ ሲፈተሸም ሀገር ክህደትንና ባንዳነትን በደም ከአያት ቅድመ አያቻቸው የወረሱት ስለመሆናቸው ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡
በትግሬዎችና በሌሎች ዜጎች ቁርጥ ያለና ለማንም ቁልጭ ብሎ የሚታይ የዜግነት ልዩነት አለ (ትግሬዎች ሲባል እንደ አጠቃላይ እንጂ በዝርዝር አተያይ የሚስተዋሉ ፈርጣዊ ቀለማትን እንደማይጨምር ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡) በመሠረቱ የዚህ ልዩነት መኖር ለኅቡዓን ድርጅቶች ዓላማዎችና ዒላማዎች ስኬት ወሳኝ ነው፡፡ በሀገሮች ውስጥ ሰላምና ፍቅር ካለ ሰይጣናዊ መንግሥትን ለመመሥረት አይቻልምና ያ ዓይነቱ ሰላማዊ መደላድል በኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን በተቀረው ዓለምም ሁሉ መጥፋት ይኖርበታል፡፡ ያን ለማጥፋት ደግሞ ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም መንግሥትና የመንግሥት አመራር ሳይሆን ሕዝብና ሀገር የሚጠላው ክፉ መንግሥት መተከል አለበት፡፡ የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ ስናይ ሕዝብ የወደደው መሪ በመፈንቅለ መንግሥት ሲወገድና በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች አረር አናቱ ሲበረቆስ በምትኩም ሆዳምና የሚጫነውን የምዕራብ ግሳንግስ ሁላ አለአንዳች ቅዋሜ የሚሸከም ማይም አጋሰስ በልዩ ዘዴ – የዴሞክራሲን ጭምብል በመጠቀም ጭምር – ሥልጣን ላይ ሲወጣ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እያየነው ያለነውም ይህንኑ ነው፡፡ ትግሬው ተጠቃሚ ሆኖ ወይም ቢያንስ መስሎ የምናየው በመሠረተ ሃሳቡ ለትግሬው ታስቦ ሣይሆን የእርስ በርስ መናከስንና ጠብንና ዕልቂትን ለማነሳሳት በዚያውም የዚያን የዲያብሎስ የሰው ደም ግብር ለማቅረብ ተፈልጎ ነው፡፡ እናስ? እኛስ በመርበባቸው አልገባንም? ከመነሻው አሣፍረን ልንመልሳቸው ሲገባን የመጣብን መርገምት በረከት መስሎን አንዳችን በአንዳችን ላይ አለቅጥ ስንፏልል ይሄውና የእግዚአብሔር ቅጣት በኛና በልጆቻችን ላይ ሊወርድ የቀረው ጊዜ እጅግ አጭር ሆነ፡፡ በወያኔ የዱባ ጥጋብ የተዘናጋው ትግሬ፣ በተለይ በአማራው ላይ በመነሳቱ ምን ጥቅም አተረፈ? ሁላችንም ረጋ ብለን እናስበው፡፡ በአንዱ ሞትና ስደት ሌላው መጥገቡና ሰማይ ጠቀስ ሀብትና ንብረት ማከማቸቱ እየቆዬ ለኅሊና ፀፀት የሚዳርገው ከሆነ፣ እየቆዬ የ‹ወይኔ›ን እግር እሳት በመላ ሰውነቱ የሚለቅበት ከሆነ፣ እየቆዬ ጥጋቡ ወደርሀብ የሚነዳው ከሆነ ከፀሐይ በታች ምን አዲስ ነገር አመጣለት ሊባል ይሆን?  የቀንን ጎደሎ ያልተረዳ ትግሬ ሥልጣን ላይ ያለውን ገዢ ኃይል ተጠቅሞ የአማራውን ሕዝብ ሀብትና ንብረት በመቀማቱ እስከመቼ እንደተደሰተ ይኖራል? አዙሮ ማየት ማንን ገደለ? ሆድንና ስሜትን ሳይሆን አእምሮንና ኅሊናን መጠቀም ማንን ጎዳ? ጊዜ መልሱን የሚሰጣቸው ብዙ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይቻላል፡፡…
ወያኔ ኤድስ የያዛቸውን ዜጎች ከትግራይ አንድ ባንድ እየለቀመ አማራውን እንዲፈጁለት ወደተለያዩ የአማራው አካባቢዎች ተገቢውን ሥልጠናና ንቃት በመስጠት ታማሚ ትግራውያንን ታመውም እንኳን በተጋዳላይነት አሰልፎ ሟቾችን በጤናማ ዜጎች ላይ እንዲዘምቱ ለልዩ ተልእኮ ያሰማራቸው ነበር፡፡ ትግራይ ውስጥ ሳይቀር ሀገራቸውንና ኢትዮጵያዊ ባንዲራቸውን የሚወዱ ትላልቅና ታላላቅ የትግራይ ተወላጆችን በወባ መቆጣጠሪያ ክኒን መልክ በሚዘጋጁ መርዞች እየበከለ ይጨርሳቸው እንደነበርም ይታወቃል – ይህ ዓይነቱ ዜጎችን በልዩ ልዩ ሥልትና ዘዴ እየገደሉ በሚሰጠው ስሜት መደሰትና መዝናናት መለስን በመሳሰሉ ሴተኒስቶችና የኅቡዓን ማኅበረሰብ ቀንደኛ አባላት መካከል ጌታቸውን ሊቀ ሣጥናኤልን በደስታ የሚያስፈነድቅ እጅግ ተፈላጊ ተግባር ነው፤ ያሾማል ያሸልማልም፡፡ (It is one among the satanic ritual abuses /SRA/.)
ወያኔ ‹ዓሣን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ› በሚል መፈክሩ በዋና ጠላትነት የፈረጃቸውንና ባገኘው መሣሪያና ሥልት ሁሉ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚሌኒየሙን ትልቅ ዘመቻውን የከፈተባቸውን የአማራ ልሂቃን ለወደፊቱ ከመባቀያቸው ድራሻቸውን ለማጥፋት በአማራው ብዙ አካባቢዎች አምካኝ መድሓኒቶችን(መርዞችን) ማደሉ የሚታወቅ ነው፤ ሰሞኑንም በልዩ ልዩ ‹ነጻ ሚዲያዎች› በይፋ ተገልጾኣል (ይቅርታ – ‹ነጻ ሚዲያ› አለ ብዬ ስለማላምን ነው – አስቸጋሪ የክርክር ነጥብ ይመስለኛል፤ ‹ነጻ› የሞተ ብቻ ነው – የምትደግፈው ከሌለ የምትቃወመውም የለም – እንደ አካሄድ!)፡፡ በዚህም ሳቢያ በአሁኑ ወቅት በብዙ የአማርኛ ተናጋሪ አካባቢዎች ባልተለመደ ሁኔታ ትምህርት ቤቶች ተመዝጋቢ ሕጻናትን እያጡ ሊዘጉ መቃረባቸውን፣ ብዙ መንደሮች ውስጥ ለአምሮትም እንኳን የሚሆን አንድም እምቡር እምቡር የሚል ሕጻን አለመገኘቱን፣ አዲስ ተጋቢዎችና ነባር ወላዶች በልጅ ስጠን ተማጥኖ ጠበሎችንና አውሊያ ቤቶችን ሙጥናን ማለታቸውን፣ ወዘተ. በቅርቡ የወጣ ማጋለጫ መግለጫ አስታውቋል፡፡ይህን ዓይነት ሥራ ከሰይጣን በስተቀር ሌላ የሰው ልጅ ሊሠራው እንደማይችል መረዳት ይገባል – ወያኔዎች ሰይጣን ያደረባቸውና እንዲያውም ከራሱ ከሰይጣን በላይ ለጌታቸው መንግሥት አደግድገው የቆሙ ቅን ታዛዦች ናቸው፤ ሰው ምን አረመኔ ቢሆን ይህን ወንጀል አይሠራም – በጭራሽ፡፡ ለነገሩ በጃንጥላ እየወረደ የሚገኝን የጦር ምርኮ አየር ላይ በጥይት ከሚቀላ የአጋንንት ውላጅ ወያኔ መልካም ነገር አይጠበቅምና በአማራውም ሆነ በሌላው ላይ የሠራውና የሚሠራው ይህን መሰሉ ግፍና በደል ሁሉ ሊሠራው ከሚችለው በታች እንጂ በላይ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ተፈጥሮው ጥፋትና ከጥፋትም ነውና፡፡ ወያኔ የተሠራበት ጭቃ ወደ አፈርነት የተለወጠው ሔዋንን ያሣታት እባብ ቅሪተ ከይሲ አፈር ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን እኩል ዜግነት እንዳይሰማቸው አንዱን በላተኛ ሌላውን የበይ ተመልካች አድርጓል፡፡ ሥልጣንና ሀብት በአብዛኛው በትግሬዎች እጅ እንዲገኝ በሕግ ሽፋንና በጉልበት የሚችለውን ሁሉ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ የትግሬ ብቸኛ ሀብት መስላ እስክትታይ ድረስ ወያኔ አንዳችም ይሉኝታ ሳይኖረው ሁሉንም ምርጥ ምርጥ ነገር -አንድም ሣይቀር – ለትግራይና ለትግራውያን እንዲሆን ያደረገ ለትግሬዎች ብቻ ሣይሆን የሰው ልጆች ዘር አጠቃላይ ማፈሪያ ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት፣ እውነት እንጂ የፈጠራ አይደለም፡፡ የሚጠራጠር ሰው ካለ መዛግብትን ያገላብጥ ፤ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶም እኛን የቁም ምሥክሮችን ያነጋግር – የሠፊው ቃሊቲ እሥረኞች ነን ማለትም ይቻላል፡፡ በኢሳት አማካይነት የሚሠጡ እውነተኛ ምሥክርነቶችንም በአድራሻቸው ገብቶ ያንብብ ወይም ያድምጥ፡፡ ለምሳሌ ሰሞኑን ከሰማሁትና በፊትም ከማወቀው ለመጥቀስ ያህል አየር ኃይላችንን እንዴት እንዳጠፉትና ለሥልጠና የሚልኳቸው ደረጃቸውን ያልጠበቁ ዜጎች ሁሉም ከትግራይ እንደተመለመሉ የሚጠቁመውን በቦታው የነበረ የባለሙያ ገለጻ ማየት ይቻላል፡፡ ይህ የአሁኑ ትውልድ በዚህ አስገራሚ የታሪክ አንጓ ላይ የመገኘታንን አጋጣሚ ስታዘብ ፈጣሪ ምን ያህል ሊቀጣን እንደወደደ ትውስ ይለኝና በአግራሞት እወሰዳለሁ፡፡ እንደኛና የኛን ያህል የተቀጣ ሕዝብ ስለመኖሩም እጠራጠራለሁ፡፡ በጥይትም ሆነ በቦምብ አንዴ መሞት ፀጋ ነው፤ የኛ ግን ከወያኔ የሥልጣን ይዞታ የመጀመሪያ ዕለት አንስቶ በኅሊና በየሰከንዱና በየደቂቃው እየሞትን እንገኛለን፡፡ እውነቴን ነው የምለው – ስለወያኔ የአድልዖ ሥራ ባስታወስኩ ቁጥር ኢትዮጵያዊነቴን ብቻ ሣይሆን ሰው ሆኜ መፈጠሬን ጭምር እጠላለሁ፡፡ ይታይህ – ትግሬ በመሆንህ ብቻ የኢትዮጵያ ጓዳ ጎድጓዳ ለአንተ እንደልብህ የምትፏልልበት የራስህ ንብረት ሆኖ ለአንተ ለምሥኪኑ አማራ ወይም ሽናሻ ግን በዐይንህም እንዳታየው እንደውሻ ችው የምትባልበትና በአካባቢው ዝር እንዳትል በዱላ እየተቀለጠምክ የምትባረርበትን ሁኔታ ስትታዘብ በሰዎች ግብዝነትና አለማፈር ታፍራለህ – ደግ ሰው ከሆንክም የነዚህን ዓይነት ቂላቂል ሰዎች መጨረሻ ፈጣሪ ቀለል እንዲያደርግላቸው ልትጸልይላቸው ትችላለህ፡፡ የትም ስትገባ ፈላጭ ቆራጩ ትግሬ የመሆኑ ምሥጢር አልገባህ ይልናም ክፉኛ ልትተክዝ ትችላለህ፡፡ ይህ ነገር መቅሰፍት እንጂ ምን ሊሆን ይችላል? መቀሰፍት ደግሞ መቅሰፍትን ይጎትታል! እንደ እውነቱ ያለንበት ሁኔታ ሲታይ የህልምና የቅዠት እንጂ የእውን አይመስልም፡፡ ፈጣሪ ሰውን በመሥራቱ መጸጸት ካለበት ጊዜው አሁንና አሁን ብቻ ነው – የወያኔን ከዲያሎብስ የበለጠ ክፋትና ክፋተኝነት ሲያይ፡፡ እንዴ! እንኳንስ በጽንሰትህ በሞትህም እኮ አይለቁህም!
ትምህርትን በሚመለከት ከትግራይ ውጪ ሁሉም የሞተ ያህል ነው፡፡ ትውልድን ለመግደል ሲታሰብ ቀድሞ ዒላማ ውስጥ የሚገባው ትምህርት ነው፡፡ የትምህርትን ጥራት ከገደልክ ሀገርንም ትውልድንም በአንድ ጥይት ደብድበህ ትገድላለህ፡፡ ወያኔም ደርግ ያቆሰለውን ትምህርት ጨርሰው ገድለው ቀብረውታል፡፡ ‹ሀሁ›ንና ‹አቡጊዳ›ን በቅጡ የማይለዩ የኮሌጅ ምሩቃን አገሩን አጥለቅልቀውት ስታይ የትና መቼ በማን የተማረ የሰው ኃይል ሀገሪቱን ሊረከብ እንደሚችል በማሰብ ልትጨነቅ ትችላለህ፡፡ መሬቲቱ ምሁራንን ሳይሆን …
በሀገሪቱ ቅጥ ያጣ ድህነት ተስፋፍቷል፡፡ ጥቂቱ በጥጋብ ቁንጣን ሲጨነቅ ብዙኃኑ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቷል፡፡ የሀብት ክፍፍሉ ሰማይና ምድርን ያህል የተራራቀ ነው፡፡ ኢፍትሃዊነት ነግሷል፡፡ ሠራተኞች ተገቢ ክፍያ አያገኙም፡፡ የወያኔው ሥርዓት የሚደግፈው ሀብታሞችን እንጂ ተቀጣሪ ድሆችን አይደለም፡፡ በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ሳቢያ፤-
ልመናና ቧጋችነት ከምን ጊዜውም በበለጠ በሀገሪቱ የባህል ያህል ተንሰራፍቷል፤ ዛሬ መለመን አያሳፍርም፡፡ የማይለምን ሰው በነውረኝነት እስኪፈረጅ ድረስ ከትልቅ እስከ ትንሽ አብዛኛው ሰው ለማኝ ሆኗል፡፡ ልመናና በረንዳ አዳሪነት በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሴተኛ አዳሪነትም የዚያኑ ያህል ነው – የወሲብ ገበያው ከዐዋቂ እስከ ሕጻን እጅግ ደርቷል፡፡ ሽርሙጥናው በተለመደው የተቃራኒ ፆታ መካከል ብቻም እንዳይመስልህ – በተመሳሳይ ፆታም ብሷል፡፡ ብዙ ነገሮች ከመስመር ወጥተዋል – የሶዶምና ገሞራንም መዐት እየጋበዙ ይመስላል፡፡ ለዚህ ሁሉ የሞራል ዝቅጠትና የሃይማኖት መላላት ዋና ተጠያቂው የነእንትና እንደራሴ የሆነው ወያኔ መሆኑን ታዲያ አትርሣ፤ እግዚኦ በል – እግዚኦ እንበል፡፡ ቢሆንም …ቢሆንም… አይዞን ጊዜው ቀርቧል፤ ዘመኑ አልቋል፡፡ የምዕራፍ ሁለት የጅማሮው ብሥራት ገመገሙ እየታዬ ነውና አንተ ብቻ እንዳትሰናከል በርታ፤ አምላክህ እንዲረዳህም ለምነው፡፡ ከርሱ ብቻ ግን አትጠብቅ፤ ለነጻነትህ አንተም የድርሻህን ተወጣ፡፡
በሀገሪቱ ፍትሃዊ አስተዳደር ጨርሶውን የለም፡፡ ጉልበተኝነትና ዘረኝነት ትልቁን ሚና ስለሚጫወቱ ሕግ አለ ብለህ የትም ብትሄድ ዋጋ የለህም፡፡ የፈጣሪ ጥበቃ እንጂ አንድም ቦታ ፍትህና ርትዕ የለችም፡፡ ብትከስ ወይ ብትከሰስ ዋቢህ ገንዘብህ ወይም ጎሣዊ ማንነትህ ብቻ ናቸው፡፡ በጠራራ ፀሐይ አንዱ ትግሬ ወያኔ ንብረትህን ቢዘርፍህ ዕንባህን ወደላይ ፈንጠቅ ከማድረግና የላይኛውን ፍርድ በትግስት ከመጠበቅ ውጪ የሚረዳህ ፍርድ ቤትም ሆነ የሕግ ቦታ የለም – አንዲት ቀጭን የሥልክ ትዕዛዝ ሰበር ሰሚ ተብዬውን ‹ግዙፍ› ፍርድ ቤት አፉን ልታዘጋ ትችላለች – ያቺ ቀጭን ትዕዛዝ ደግሞ ከየት እንደምትመጣ አታውቃትም፤ ‹ጠ/ሚ› ኃ. ደሳለኝን ከመሰሉ ኮንዶሞች እንደማትሆን ግን መረዳት አለብህ – ፍትህን በማዛባት ረገድ ይተባበሩና በታዛቢነት ያገለግሉ እንደሆነ እንጂ እነደመቀ በወሳኝነት ሚና አይታሙም፤ እነሱ ምን ቤት ናቸውና፡፡ የንብረትህ ብቻ ሣይሆን የነፍስህም ፈጣሪ ወያኔዎችና በወያኔነት ያበዱ ትግሬዎች  ናቸው፡፡ (ጤነኞች ትግሬዎች የዛሬን ታገሡኝ ግዴላችሁም – የሆድ የሆዴን ልዘርግፈውና ልገላገል፡፡ ደግሞም ጥሩ ዕቃ ማስታወቂያ እንዲነገርለት አያስፈልገውምና ጥሩዎች ትግሬዎች ብዙም እንደማትከፉብኝ ብገምት ደስ ይለኛል፤ እነዲያቆን እገሌ ግን ቢንጣጡ ግዴለኝም – ለሁለት ዓለም  የሌሊት ወፍ መሰል ዜጎች ተጨንቄ አላውቅም፡፡ ከወያኔያዊ እድፍ የጸዳን ነን ብላችሁ የምታምኑ ጥሩዎች ትግሬዎች በምናገረው ብሶት ስሜታችሁ እንደሚጎፈንን ይገባኛል – ግን እንዳትፈርዱብኝ፡፡ በኔ ቦታ ሆናችሁ እዚህም ሆነ እዚያ የሚነገሩ እውነቶችን ለመቃኘት ሞክሩ፡፡ ስትቃኙ በጭፍን አይሁን፤ ስህተት እንኳን ብናገር ለስህተቴ መነሻው ማን እንደሆነ ተገንዘቡልኝ፡፡ ደግሞም የምለው ሁሉ የሚገናኘው ከወያኔና ጀሌዎቹ ጋር እንጂ ከችግሩ ተቋዳሽ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ጋር አይደለም፡፡ እንደዚያ ሊሆንም አይችልም፡፡ ከአድማስ ማዶ ሀገር ያለ እንኳን የማይመስለው ንጹሕ ዜጋ በነዚህ ስድ አደግ ወገኖቹ ሊወቀስ እንደማይገባው እኔ ቀርቼ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቃል፡፡ ‹ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ሲያለቅስ ይኖራል› እንዲሉ ሆኖብን ባልገው በሚያባልጉ ወገኖች ስሜታችን እየተነካ ጥሬ እውነቱን እንዳለ ስንናገር ለትዝብት እንዳረጋለን፡፡ ለማንኛውም በነዚህ ጉግማንጉግ ወንድሞቻችን መጥፎ ድርጊት ምክንያት ስማችንን አጠፋህ ለምትሉኝ ወገኖቼ በማቄን ጨርቄን ምንም ሰበብ ሳልደረድር ልባዊ ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ፤ የመካካስ ዘመን ሲብት(ም) በፍቅር እቀጣለሁ፡፡)
ሙስና እግር አውጥቶ ታየዋለህ፡፡ በእጅህ ካልሆነ በእግርህ ሄደህ የሚፈጸምልህ ጉዳይ ከስንት አንድ ነው፡፡ ይህን አሠራር ሆን ብሎ የሚያበረታታውም ወያኔ ነው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ባለሥልጣን ሙስና ውስጥ የተዘፈቀ ነው፡፡
የኑሮ ውድነቱ ከጣርያ በላይ ነው፡፡ ዛሬ እህል ቀምሶ የሚያድረው ዜጋ ቁጥር ከምን ጊዜውም በላይ እጅግ ጥቂት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ችግርን በመቻል ስለሚታወቁ ሲስቁና ሲጫወቱ የደላቸው ይመስላሉ እንጂ ሁሉም በየቤቱ አፍኖ የያዘው ችግር ቢፈነዳ ሀገሪቱ የችግር ኮረጆ እንደመሆኗ መዘዙ ወይም ዳፋው በቀላሉ የሚገደብ አይደለም፡፡ በግርድፍ ግምት ከ40 ዓመታት በፊት የነበረው አንድ ብር የዛሬውን ቀልበቢስ መቶ ብር አሳምሮ ይበልጠዋል፡፡ የዛሬው ግርማ ሞገሱ የተገፈፈ መቶ ብር መልክ ብቻ እንጂ ሙያ የለውም፡፡ እንደሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀርመን ልንሆን የቀረን ጥቂት ጊዜ ነው – እስካሁን ወደዚያ ያልደረስነውም በፈጣሪ ጥበቃና በእርሻ ምርቶች ባለቤትነታችን ነው፡፡ አብዛናውን የእህል ምርት ከውጪ የምናስገባ ብንሆን ኖሮ እስካሁን የለንም፡፡ በዚህ እግዜሩ ይመስገን፡፡
ወያኔ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሸጠ የወሮበሎች ቡድን ነው፡፡ የሕዝብን መብት አለማክበርና ዘወትር ዜጎችን መግደል የአምባገነኖች ባሕርይ ነው ብንል ወያኔ ግን ከመሰል አምባገነኖች በተለዬ ሁኔታ የሀገርን ግዛትና ለም መሬቶች ለውጪ ሀገሮችና ለውጪ ኢንቬስተሮች ባገኘው ዋጋ እየቸበቸበ በሚገኘው ገንዘብ በግሉ የሚከብር የከተማ ሽፍቶች ጥርቅም ነው፡፡ እነዚህ ወሮበሎች አገዛዙን የሚቀማቸው ጀግና አጥተው እንጂ ሀገሪቱን በኳስ አበደች ትርምስ ውስጥ ከትተው ቀደም ካለ ጊዜ ጀምረው ወዳዘጋጁት ሰሜናዊ የትግራይ ትግሪኝ ግዛታቸው  ለማምራት ያቆበቆቡ ይመስላሉ፡፡ ሁሉንም የመከላከያ ተቋም ወደ ትግራይ እንዳዞሩ የሚነገረውም ከዚህ መሠረታዊ የሽፍቶቹ አቋም ጋር በተገናኘ መሆን አለበት፡፡ በ23 ዓመታት ውስጥ ቅንጣትም ኢትዮጵያዊነት ስሜት ሊያድርባቸው ያልቻሉት እነዚህ በአስተሳሰብና በድርጊት ባዕዳን የሆኑ ገዢዎቻችን ነገና ነገ ወዲያ ምን አጥምደውብን እንደሚሄዱ ማወቅ አንችልም፡፡ ቢሆንም መታመን በፈጣሪ ነውና እርሱ ራሱ ያከሽፈዋል ብለን የምናምን ምሥኪን ዜጎች እነሱ ለራት ሲያስቡን አንድዬ ለምሣ ያደርጋቸው ዘንድ በርትተን እንጸልይ፡፡
ሃይማኖታችንን በየዘርፉ ለማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ በዚህም ብዙ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ኦርቶዶክሱን ከሞላ ጎደል አጥፍተዋል፡፡ የመጥፋቱ ምልክት ሁሉንም አመራር በሃሳዊ መሲህ የትግሬዎች ካህናትና ሰሜነኞች የቤተ ክርስቲያን ‹አባቶች› ቁጥጥር ሥር ማስገባታቸው አይደለም – ያ በራሱና ብቻውን ጥፋት አይደለም( በበኩሌና በመሠረቱ ሁሉንም የዓለማዊና ሃይማኖታዊ ሥልጣን ትግሬ ቢይዘው አንዳችም ቅሬታ የለኝም፤ ችግሬ ዐይኑን እያጉረጠረጠ የሚገኘው ዜጎችን እየቆረጣጠመ፣ ሀገርን እያወደመ ያለው የአድልዖና የማግለል ሥራቸው ነው – የዚህ ችግር መሠረትም ማይምነትና የጥቂትነት ባሕርይ የሚያሳድረው የበታችነት ስሜት፣ ያንንም ስሜት በቅጡ ካለማስተዳደር የሚመጣ ስግብግብነትና ራስ ወዳድነት፣ እንደዚሁም ሌሎችን ያለማመንና ‹ይችን ዕድል ካጣሁ ዳግመኛ ወደዚች ቦታ አያስደርሱኝም› ከሚል ፍርሀት የሚመነጭ ‹የሞኝ ሙርጥ ካለአንድ ቀን አይበልጥ› ዓይነት አስቀያሚ አጋጣሚ ነው – እንጂ ትግሬዎች በተፈጥሯቸው መጥፎና ይህን ያህል ጨካኝ ሆነው አይደለም – ነገሩ የሆድ ነገር ሆድ መቁረጡ ነው የማይዘሉት ፈፋ ሆኖ ብዙዎቹን ያስቸገራቸው፡፡  ይህ ዓይነቱ ማኅበረሰብኣዊ በሽታ በወደፊቱ የአብሮነት ሕይወት የሚጥለውን አሉታዊ አንድምታ ከአሁኑ ጀምሮ መርሳትን መለማመድ ጊዜን ይቆጥብልናልና በ‹ልጅሽን አንሺ ምጡን እርሺ› ይትበሃላችን ወይዘሪት ነጻነትን ለሁላችንን በሚጠቅም ጉጉት እንጠብቃት ብል በ‹መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች› ብሂል የምጎሸም ችኩል የምሆን አይመስለኝም – ጊዜው በጣም የቀረበ ይመስለኛልና – እኔ አላውቅም ግን እንደዚያ ይመስለኛል፡፡) ዋና ምልክቱ ታዲያን የሚሠራው ሥራ ሁሉ የመርገምት መሆኑና ያም መርገምት መቅሰፍትን የሚጠራ የኃጢኣት ፍሬ መሆኑ ነው፡፡ በየአድባራቱ ብናይ የሚሠራው ሥራ ሁሉ ክርስቲያናዊ ሣይሆን የማስመሰል ነው፡፡ በማስመሰል ሥራ ደግሞ ትክክለኛ ሃይማኖት አትቆምም፡፡ የማያዛልቅ ጸሎት ለመብረቅ እንደሚዳርግ መነገሩም ለዚህ ነው፡፡ እናም ቤተ ክርስቲያንም ልክ እንደ ቤተ መንግሥታችን ሁሉ የጽዳት ዘመቻው እኩል ተቋዳሽ ናትና ‹ቀበጥ አማት ሲሦ ብትር አላት› እንዲሉ አሣሯን ስትበላ የምናይበት አጋጣሚ ከፊት ለፊቷ ሳይደቀን አልቀረም፡፡ ቤቴ ብለው የተጠጉ ልጆ‹ቿ›ን ለነቀያፋና ለነጲላጦስ እንደይሁዳ በመሳም አሳልፋ የሰጠችና የምትሰጥም ቤተ ክርስቲያን ብትቀጣ በበኩሌ ዐይኔ ዕንባ የሚያቀርር አይመስለኝም – ቀላሉን ያድርግላት ብሎ መጸለይ ነው፡፡ በወደዱት መቁረብ ዛሬ አልተጀመረም፡፡ ከቻለች ይልቁንስ ከነዚህ በአጋንንት መንፈስ ከተሞሉ ወያኔዎች በቶሎ ትለይ  – ይህ ዓለምን ከዳር እዳር እየናጠ ያለ መንፈስ በራሷ ውስጥ እንደሌለ ካሰበች መፍትሄው ይሄው ብቻ ነው – ወደቀደመው የሃይማኖት ቀኖና መመለስና ቤትን በራስ ጊዜ ማጽዳት፡፡ አለበለዚያ የርሷ እንደሚቀድም መተንበይ አይከብድም፤ ምክንያቱም አባት ከልጅ ቀድሞ ሊያልፍ ይጠበቃልና፡፡
ወያኔዎች ይሉኝታ የሚባል ሀበሻዊ ንጥረ ነገር ከነአካቴው ኖሯቸው የሚያውቅ ከሆነ አላውቅም፡፡ በአሁኑ ሁኔታቸው ግን በፍጹም እንደሌላቸው ግልጽ ነው፡፡ ይሄ ይስማዕከ ወርቁ የሚባል ትልቅ ተስፋ ያለው ወጣት ደፋር ደራሲ በነዚያ የዴርቶጋዳ የዋሻ ውስጥ ምናባዊ ሣይንቲስቶቹ አማካይነት ከወደፊት ልቦለዶቹ በአንደኛው ይህን በወያኔዎች ሰውነት ውስጥ ተፈልጎ ለናሙናነት ያህል እንኳን ሊገኝ ያልቻለ ይሉኝታና ሀፍረት በላቦራቷር ካላሠራላቸው በስተቀር አሁንስ ክፉኛ ያሳዝናሉ፡፡ ወያኔ ትግሬዎች ሱቅ ውስጥ እንደገባ ሕጻን የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ሀብትና ንብረት የሆነን ሁሉ ለብቻቸው እየተሻሙ ለግላቸው እያዋሉት ስለሆነ ሌላው ዜጋ ለስደትና ለጦም አዳሪነት ተጋልጧል፡፡ በዚህም ምክንያት፡-
ከጥቅም ተጋሪ ወያኔ በስተቀር  ሁሉም ዜጋ ለስደት ተዘጋጅቷል፡፡ በሀገር ውስጥ የበይ ተመልካች ሆኖ በችግርና በችጋር ከሚጠበስ በሰው ሀገር ሄጄ ገረድና አሽከር ሆኜ ሕይወቴን ላትርፍ ብሎ በየአቅጣጫው ወደውጪ የሚተመው ሕዝብ ብዛት የትዬለሌ ነው፡፡ ያንንም ዕድል ሳያገኝ የባሕር ዓሣ ነባሪና ሻርክ፣ የበረሃ አንበሣና ጅብ ሲሳይ ሆኖ የሚቀረው ከርታታ ወገን ከቁጥር በላይ ነው፡፡ ለዚህ የወገን ስደትና እንክርት ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ያለን የተፈጥሮ ሀብት ለሁላችንም መብቃት ሲችል በተንሸዋረረ የዘር ፖለቲካ የሚመራው ወያኔ ለዚህ ዓይነቱ ችግር አጋልጦናልና የሚመጣውን ቀውስ የሚያወራርደው ይበልጡን ወያኔ ነው፡፡
ወያኔዎች በማንአለብኝነት የምርጫ ድምጽ አጭበርባሪዎች ናቸው፡፡ ለታይታ ብለው በሞከሩት የ97 ምርጫ ብዙ ሕዝብ ጨርሰዋል፡፡ አሥረዋል፤ አሰቃይተዋልም፡፡ ሀገሪቱ በሞላ እሥር ቤት እስክትመስል ድረስ ከዳር እዳር ዜጎችን በጅምላ በማፈስ ልዩ የምርጫ ነክ ትርዒት ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በዚያም በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ሰብኣዊና ቁሣዊ ኪሣራ አስከትለዋል፡፡ ይህ ፖለቲከኞችንና የመብት ተሟጋቾችን የማሰርና በ‹የእምዬን ወደ አብዬ› ግልብጥ ክስ ዜጎችን በሽብርተኝነት ዘብጥያ የማውረድ መጥፎ ወያኔያዊ ልክፍት አሁንም በስፋት ቀጥለዋል፡፡ ወያኔዎች እንደ አራስ ውሻ ነፍርተው ለያዥ ለገራዥ በማስቸገር ሕዝብንና ሀገርን የማደፍረስ ታሪካዊ ተልእኮኣቸውን በስፋት ቀጥለዋል፡፡
ወያኔን ‹የሚያስቀስፉ› እጅግ ብዙ ነገሮችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውን ግን አንባቢ እንዲጨምርበት ተትቷል፡፡ በበኩሌ ቤት ያፈራውን ሁሉ ለነገየ አንድም ሳላስቀር የመናገር አቅሜ በፈቀደ ተናግሬያለሁ፡፡ ሌላውን አክሉበት፡፡ በቃ፡፡

No comments:

Post a Comment