Tuesday, August 13, 2013

ሌሊሴ ወዳጆ በገ ገመዴ! (እኳን ደስ አለሽ!)

http://www.abetokichaw.com/wp-content/uploads/2013/08/183153_197148860303512_4124982_n.jpg?d8e047
ሌሊሴ ወዳጆ በገ ገመዴ! (እኳን ደስ አለሽ!)
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይሰራ የነበረው ዳበሳ ዋቅጂራ መንግስት ያለ ምንም ክስ ለሶስት አመት አስሮት ነበር፡፡ (እንደሚታወቀው ከሳሾቻችን የአይናችን ቀለም ካላማራቸውም ያስሩን የለ…) ከሶስት አመት በኋላ ሲፈታ “ነጋቲ” ብሎ በሀገሩ ተስፋ ቆርጦ ተሰደደ፡፡
መንግስታችን ግን አንዴ ከጠመደ “የወገብ ቅማል” አይነት ነውና ወደ መኖሪያ ቤቱ ሄዶ ባለቤቱን ጋዜጠኛ ሌሊሴ ወዳጆን በቁጥጥር ስር አዋላት፡፡
ቀጥሎም ከኦነግ ጋር በተያያዘ ክስ መስርቶባት የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ሌሊሴ አሸባሪ ተብላ አስር አመት እንድትታሰር ተፈረደባት፡፡
“ከታሰረ በኋላ የማይፈታው የስድስት ኪሎ አንበሳ ብቻ ነው” እንዲሉ የእኛ ሰፈር ልጆች፤ ሌሊሲ ወዳጆ በነሀሴ ወር ለሚሊኒየማችን ጊዜ የታሰረች አሁን ተፈታ አውስትራሊያ ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር መቀላቀሏን ሰምተናል፡፡
መላው ቤተሰቧን እና ወዳጆቿን በገ ገመዴ (እንኳን ደስ አለሽ) ማለት ይገባል!
(ዜናውን ያገኘሁት አያንቱ ኦንላይን ድረ ገፅ ላይ ነው ገለቶማ!)

No comments:

Post a Comment