Tuesday, August 6, 2013

ከኮፈሌ የደረሰኝ መልዕክ እንደወረደ!

ከኮፈሌ የደረሰኝ መልዕክ እንደወረደ!
ሃይ አቤ ሰላም ነዉ ? ይገርምካል በኮፈሌ ከተማ ዉስጥ እየሆነ ያለዉ ክሰተት ግራ እያጋባን ነዉ; የኢህአዴግ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ! ሰላማዊዉን ህዝብ ግራ እያጋቡት ነዉ ! በየ ሆቴሉ በየካፌዉ ; በይ ሻይቤቱ ; እየገቡ ዝም በሉ ; በአንድ ላይ ተሰብሰቦ መቀመጥ አይቻልም; እያሉ የመታወቂያ ካርድ ሁሉ እየጠየቁ ነዉ ; እኔ እንደሚመስለኝ ሙሉ የጦር መሳሪያቸዉን ታጥቀዉ በየቤቱ እየገቡ የሰላሙን ህዝብ ቆሌ የሚገፉት ለሌላ ነገር ሳይሆን እንዲህ ስራ ፈተን ከምንቀመጥ ለምን በየቤቱ እየገባን በማሰፈራራት ልጅ አገረድ ሴቶችን አናጠምድም በለዉ በማሰብ ነዉ !! በአሁን ሰአት በተለምዶ ኑ ቡና ጠጡ በሚል ሰም በየ መንገዱ ዳር ቡናቸዉን እየቸረቸሩ የእለት ጉሮራቸዉን ለመሸፈን ና በዚዉ ስራ ቤተሰቦቻቸዉን እየረዱ ያሉ በርካታ የከተማዋ ሴቶች ; አመንዝራ በጠማቸዉ ;በኢህአዴግ ወታደሮች ተከበዋል; በራሳቸዉ ግዜ ምንም የማያዉቀዉን መንገደኛ በመጥራት በያዙት ሰደፍ እየደበደቡ < ቀጥ> ብለክ ሂድ እያሉ ያሳድዳሉ ; ይገርምካል አባቴ እነዚህን ጋጥ ወጥ የሆኑትን የመንግስት ቅጥረኞች ፍረሃት 3 እህቶቼን ወደ ሻሸመኔ ሊልካቸዉ ተዘጋጅቱዋል ;; በአጠቃላይ በከተማዋ ያሉ ሴቶች በፍረሃት ተዉጠዋል ; ነገሩ እንዴት ነዉ ??
አቤ ለህዝብ አቅርበለኝ !
(በዚህ መልዕክት ውስጥ ማስተካከያ ያደረኩት፤ መልዕክቱን ያደረሰችኝ ወዳጄ የወያኔ ወታደሮች ያለቻቸውን እኔ ደግሞ “የኢህሀዴግ” በሚል መተካቴ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደኔ እምነት ወታደሮቹ የሚወክሉት ወያኔን (ህውሃትን) ብቻ ሳይሆን… ኦህዴዱንም፣ ደህዴኑንም፣ ብአዴኑንም፣ አጋሩንም ነው፡፡ በጥቅሉ የኢትዮጵያን መንግስት ነው!)
አረ ይሄንን መንግስቴን ተው በሉት… እነ እንትናም ጉድ የሆኑት እንዲሁ ሲደርጉ ነው….!
abe tokichaw

No comments:

Post a Comment