Thursday, August 8, 2013

በመንግሰት የችግር አፈታት ዘዴዎች ዛሬም አዝነናል፧ አፍረናልም!!!!

August 8, 2013
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ከሁሉም በማሰቀደም ሰማያዊ ፓርቲ ለመላው የሰልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም በማለት አደረሳቹ በዓሉ የሰላምና የደሰታ እንዲሆንላቹ ኢድ ሙባረክ በማለት ምኞቱን ይገልፃል ::Blue Party Ethiopia
ኢሕአደግ መራሹ መንግሰት ተቋማትን የመቆጣጠር አባዜው ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰባት በመምጣቱ ዛሬም እጁን ያላሰገባበት ምንም አይነት ተቋምና አሰተሳሰብ ባይኖርም በተለይ ባለፈው አንድ አመት ተኩል ጀምሮ ከሰልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፈጣረው እሰጥ አገባ መፍትሔ አጥቶ እሰከ አሁኗ ሰአት ቀጥሏል:: ሰማያዊ ታርቲ የመንግሰትን በሐይማኖት ጣልቃ መግባት አጥብቆ በመቃወም የራሳቸውን የእሰልምና እምነት መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲፈታና ችግሩም በውይይት እንዲፈታ በተደጋጋሚ ግዜ ጥሪውን አቅርቧል::
ነገር ግን መንግሰ ችግሮችን በሐይል ጨፍልቄ እፈታለሁ የሚል የተለማደ አካሔድ ለፓርቲያችን ጥሪ የሰጠው ምላሽ ካለመኖሩም በላይ የፓርቲያችንን ሰም በማጉደፍ የሀገር ጠላትና አሸባሪ ፓርቲ አድርጎ ለማሳየት ጎምበስ ቀና በማለት ላይ ይገኛል::
መንግሰት ከእሰልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን ጋር በፈጠረው ችግር ባለፈው ባለፈው አንድ አመት ተኩል ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል፣ ሓብትና እውቀት የሚያድግበት ግዜ ባክንኗል፣ በሰው አካልና ንብረት ጉዳት ላይ ደርሷል፣ ሕይወት ጠፍቷል:: ችግሩ ግን አሁንም አልተፈታም፧ እንደውም እያደገና እየከረረ ሔዷል:: በዛሬው ነሐሴ 2 ቀን 2005 ዓ.ም የኢድ አልፈጥር በአል አከባበር ላይ መላው ኢትዮጵያ በሕብረት የመሰገጃ ቦታዎች በተሳተፉ የእምነት ተከታዮች ላይ በመንግሰት ታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች አሰቃቂ ድብደባና የአካል ጉዳት ደርሷል:: በአሰር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደርሞ የማረሚያ ቦታዎች እና ፕሊሰ ጣቢያ አልበቃ ብሎ በጋራዦች ጭምር ታሰረዋል:: ባልተረጋገጡ መረጃዎችም የሰው ሕይወት ጠፍቷል:: በዚህም ነገር ፓርቲያችን ከልብ አዝኗል::
ሰላማዊ ፓርቲ አሁንም መንግሰትን ችግሮቹን በሐይል ለመፍታት የሚወሰደውን እርምጃ አጥብቆ እያወገዘ በቀላሉ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚችሉ የመብት ጥያቄዎችን በማፈን ዜጎች ተገደው ወደማይፈልጉት መንገድ እንዳይሄዱ በጥብቅ ሊታሰብበት እንደሚገባ ማሳሰብ ይፈልጋል:: ሐገራችን ያለችበትን ቀጠናና ታሪካዊ መሰተጋብርም በውል የሚረዳ መፍትሄ ባሰቸኳይ እንዲሰጥ አሁንም አሁንም አጥብቀን እንጠይቃለን::
ነሐሴ 2 ቅን 200 ዓ.ም አዲሰ አበባ
Blue Party Ethiopia

No comments:

Post a Comment