Thursday, August 8, 2013

በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ሰማሁ!


17737_491880560901490_24279230_nበአዲስ አበባ ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ ፖሊስ ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ ሰማሁ!
በአዲስ አበባ ስታድየም አመታዊውን የኢድ በዓል አክብረው እግረመንገዳቸውንም በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በፖሊስ የድብደባ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ እየሰማሁ ነው፡፡
በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች ከኢድ በዓል ጋር ተየያይዞ የተሰማውን ተቃውሞ ለምን አሰማችሁ ያለው መንግስት ርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በዛሬው ተቃውሟቸው ባለፈው ወቅት አንድ ግለሰብ አሮጌ ባንዲራ ሲያውለበለበ  እያሳየ የድምጻችን ይሰማ አባላት ባንዲራ እንዳቃጠሉ አድርጎ ሲዘግብ የነበረውን የመንግስት ሚዲያ ዘገባ ፉርሽ በሚያደርግ መልኩ በባንዲራ አጊጠው ነበር የወጡት፡፡
መንግስት ጥቃት እየፈጸመ ለው ለምን ባንዲራ ያዛችሁ ብሎ ይሁን፣ ለምን አላህ አክበር አላችሁ ብሎ ይሁን፣ ለምን ድምጻችን ይሰማ አላችሁ ብሎ ይሁን ለማጣራት ያደረኩት ሙከራ የለም… ብቻ ወገኖቻችን በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ መከራ እያዩ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment