Monday, August 19, 2013

የአልቃይዳው አመራር ሙሀመድ አልዛዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

የአልቃይዳው አመራር ሙሀመድ አልዛዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
የግብፅ የፀጥታ ሀይሎች የአልቃይዳ ከፍተኛ አመራርና በመስከረም አንዱ ጥቃትና በለንደኑ የትራንስፖርት ጥቃቶች እጁ እንዳለበት የሚታመነውን የአይማን አልዛዋሪን ወንድም መሀመድ አልዛዋሪን በጋዛ አካባቢ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ገለፁ፡፡
አሸባሪው መሀመድ አልዛዋሪ  የማሀመድ ሙርሲ ደጋፊ  ሲሆን በግብፅ ውስጥ አሁን ባለው ተቃውሞ ውስጥም ተሳታፊ ነው ፡፡
በግብፅ ካይሮ ከተማ በ1951 የተወለደው መሃመድ አልዘዋሪ ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር በ1980ዎቹ አጋማሽ በፓኪስታን የተገናኙ ሲሆን የአልቃይዳ መረብ ዋና አስተባባሪና የቢላደን ቀን እጅ እንደነበርም ይታመናል፡፡
መሃመድ አልዘዋሪ በ1999 እ.ኤ.አ በግብፅ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሞት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን በኬንያና ታንዛኒያ የአሜሪካ ኢንባሲዎች ላይ ለደረሰውም ጥቃት ተጠያቂ ነው ይባላል፡፡
የአክራሪው ጂሀዲ ሳላፊስት ቡድን መሪ የሆነውን መሃመድ አልዘዋሪን እ.ኤ.አ በ2001  አሜሪካን ካወጣቻቸው እጅግ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ይገኝበታል፡፡
ምንጭ፡-ሜይል ኦን ላይን

No comments:

Post a Comment