Tuesday, August 6, 2013

በኒ ሻንጉል፥ የአማሮች አቤቱታ

ቡለን በተባለዉ ወረዳ የሚኖሩ ተመላሾች እንደሚሉት እስካሁን ንብረታቸዉ አልተመለሰም፥መሬት፥ማደበሪያና ምርጥ ዘርም ማግኘት አልቻሉምከበኒ-ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ተብረረዉ በቅርቡ የተመለሱ የአማራ ብሔር ተወላጆች አሁንም በደል ይፈፀምብናል በማለት አቤት አሉ።በተለይ ቡለን በተባለዉ ወረዳ የሚኖሩ ተመላሾች እንደሚሉት እስካሁን ንብረታቸዉ አልተመለሰም፥መሬት፥ማደበሪያና ምርጥ ዘርም ማግኘት አልቻሉም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በስልክ ያነጋገራቸዉ ሁለት ሰዎች ድብደባ እንደተፈፀመባቸዉም አስታዉቀዋል።ከቡለን ወረዳ ተባረረዉ የነበሩ ከአምስት ሺሕ በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች  ወደነበሩበት ሥፍራ በቅርቡ ተመልሰዋል።ዝር ዝሩን እነሆ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ

DW

No comments:

Post a Comment