Thursday, June 13, 2013

“ማንም ያኮረፈ ሲያስታጥቀን አይደለም ትግል የምናደርገው”

Photo: "ማንም ያኮረፈ ሲያስታጥቀን አይደለም ትግል የምናደርገው"የአንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችን ጥሪ ተቀብሎ የትጥቅ ትግል ያነሳ ሃይል የህዳሴ ግደብ ግንባታ አደናቃፊ ነው - የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችየአባይ  ወንዘን አስመልክቶ  በኢትዮጵያና  ግብፅ  መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ዙሪያ  በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ  ፖለቲካ  ፓርቲዎች  አመራሮችን ጣቢያችን ያናገረ ሲሆን ፥ የአመራሮቹም  ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል ።አቶ ግርማ ሰይፉ   የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር“ለረዥም ግዜ ስናራምደው የነበረው አቋም አለ ፤ ኢትየጵያ ግድብ የመገንባት መብት አላት። በዚህ መብት እየተጠቀመችበት አልነበረም።ይሀንን መብታችንን መጠቀም አለብን ብለን ነው የምናምነው ። ሌሎች የምናነሳቸው ጉዳዮች አሉ።እነዚህ ጉዳዮች ግን በፍፁም ከግብፅ ጋር የሚገናኙ አይደሉም።በፍፁም ግብፅ ደስ እንዲላት ደስ እንዳይላት የሚባል ነገር የለም እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ነው የምንፈልገው።የግብፅ ተወቃዋሚ ፓርቲዎች ፣ ደጋፊዎች ወይም በፖለቲካው የሚሳተፉ ሰዎች ወሰዱት የተባለውን እርምጃ ሰምተነዋል። ምንም ትርጉም ያለው አይደለም ስስ ነው ። ምናልባት ለሃገር ውስጥ ፖለቲካቸው ይጠቅማል ብለው ያደረጉት ይሆናል እንጂ ያሰቡበት አይመስለኝም።ከእኛ ፓርቲ አንፃር ከምንከተለው የትግል ስልት ውጭ ነው።ማንም ያኮረፈ ሲያስታጥቀን አይደለም ትግል የምናደርገው። የእነርሱ ድጋፍ ለእኛ ምንም ጠቃሚ አይደለም ። ለእኛ የሚያስፈልገን የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ነው። እንታገላለን ለሚሉ ሰዎች የተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለማመስ ሙከራ አያደርጉም ተብሎ መቀመጥ አይቻልም። ዋናው ነገር የቤት ስራችንን መስራትና መጥተው በበሰላማዊ መንገድ እንዲደራደሩ ማድረግ ነው።አቶ ሙሼ ሰሙ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ፕሬዘዳንት          “ የኢትዮጵያ መንግስት ለግድቡ ግንባታ የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየሱን ተከትሎ በግብፅ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጀመረው አሉታዊነት ያለው እንቅስቃሴ    በመንግስት ደረጃም ከዛም አልፎ በታዋቂ ሰዎችና በሃይማኖት መሪዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በሚጋፋና  በሚደፍር መልኩ በሰፊው ዛቻም ማስፈራራትም በታከለበት ሁኔታ እየተነገረ እንደሆነ እየሰማን ነው።ይሄ የሚያሳየን መሰረታዊ ነገር የግብፅ ማን አለብኝነት ተገቢ ያልሆነ ትምክህትና አምባገነንነት ውስጥ እንዳልች ነው የምንረዳው ።ምክንያቱም ግብፅ እንደ አንድ ሃገር ሌላ ሃገር ሉዓላዊነትና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ምንም ዓይነት መሰረትም ሆነ መብት የላትም። አባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ወንዝ ነው። ይህ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ወንዝ እንደ ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት ኢትዮጵያን በሚመጥንና በሚያስፈልጋት ልክ የመጠቀም መብት አላት።  ስለዚህ የግብፅ መንግስትና ህዝብ ፍላጎት ምንም ይሁን ምን ቅድሚያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና መሰረታዊ ጥቅም ነው።ግብፆች ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ያደረጉት ጥሪም ከራሳቸው የውስጥ ጭንቀትና ፍላጎታቸው የመነጨ ነው። በእኔ እምነት ማንኛውም ተቃዋሚ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ የግብፅን ጥሪ ተከትሎ  በኢትዮጵያ መንግስት ላይ  የትጥቅ ትግል አንስቻለው የሚል ሃይል የተጀመረውን የህዳሴ ግደብ የሚያደናቅፍ ስራ የሚሰራ ከሆነ ይሄ ለሃገርም ለህዝብም ህልውና ፣ ሉዓላዊነትና አንድነት ያለመቆም ከመሆን ያለፈ ትርጉም አይኖረውም። ኢዴፖ ይህንን ግድብ በንቃትና በትጋት ስንከታተል ቆይተናል።በመቀጠለም ግድቡ ስራው እስኪጠናቀቅ እርዳታ ከመስጠት ባሻገር ይህንን አስመልከቶ ስብሰባ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራ አቋማችንን ለመግለፅ ዝግጁ ነን።”አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
የአንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችን ጥሪ ተቀብሎ የትጥቅ ትግል ያነሳ ሃይል የህዳሴ ግደብ ግንባታ አደናቃፊ ነው – የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችየአባይ ወንዘን አስመልክቶ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችን ጣቢያችን ያናገረ ሲሆን ፥ የአመራሮቹም ሀሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል ።አቶ ግርማ ሰይፉ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር
“ለረዥም ግዜ ስናራምደው የነበረው አቋም አለ ፤ ኢትየጵያ ግድብ የመገንባት መብት አላት። በዚህ መብት እየተጠቀመችበት አልነበረም።ይሀንን መብታችንን መጠቀም አለብን ብለን ነው የምናምነው ። ሌሎች የምናነሳቸው ጉዳዮች አሉ።እነዚህ ጉዳዮች ግን በፍፁም ከግብፅ ጋር የሚገናኙ አይደሉም።በፍፁም ግብፅ ደስ እንዲላት ደስ እንዳይላት የሚባል ነገር የለም እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ነው የምንፈልገው።
የግብፅ ተወቃዋሚ ፓርቲዎች ፣ ደጋፊዎች ወይም በፖለቲካው የሚሳተፉ ሰዎች ወሰዱት የተባለውን እርምጃ ሰምተነዋል። ምንም ትርጉም ያለው አይደለም ስስ ነው ። ምናልባት ለሃገር ውስጥ ፖለቲካቸው ይጠቅማል ብለው ያደረጉት ይሆናል እንጂ ያሰቡበት አይመስለኝም።
ከእኛ ፓርቲ አንፃር ከምንከተለው የትግል ስልት ውጭ ነው።ማንም ያኮረፈ ሲያስታጥቀን አይደለም ትግል የምናደርገው። የእነርሱ ድጋፍ ለእኛ ምንም ጠቃሚ አይደለም ። ለእኛ የሚያስፈልገን የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ነው። እንታገላለን ለሚሉ ሰዎች የተወሰነ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለማመስ ሙከራ አያደርጉም ተብሎ መቀመጥ አይቻልም። ዋናው ነገር የቤት ስራችንን መስራትና መጥተው በበሰላማዊ መንገድ እንዲደራደሩ ማድረግ ነው።
አቶ ሙሼ ሰሙ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ፕሬዘዳንት
“ የኢትዮጵያ መንግስት ለግድቡ ግንባታ የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየሱን ተከትሎ በግብፅ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተጀመረው አሉታዊነት ያለው እንቅስቃሴ በመንግስት ደረጃም ከዛም አልፎ በታዋቂ ሰዎችና በሃይማኖት መሪዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በሚጋፋና በሚደፍር መልኩ በሰፊው ዛቻም ማስፈራራትም በታከለበት ሁኔታ እየተነገረ እንደሆነ እየሰማን ነው።ይሄ የሚያሳየን መሰረታዊ ነገር የግብፅ ማን አለብኝነት ተገቢ ያልሆነ ትምክህትና አምባገነንነት ውስጥ እንዳልች ነው የምንረዳው ።
ምክንያቱም ግብፅ እንደ አንድ ሃገር ሌላ ሃገር ሉዓላዊነትና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ምንም ዓይነት መሰረትም ሆነ መብት የላትም። አባይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ወንዝ ነው። ይህ እንደመሆኑ መጠን ይህንን ወንዝ እንደ ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት ኢትዮጵያን በሚመጥንና በሚያስፈልጋት ልክ የመጠቀም መብት አላት። ስለዚህ የግብፅ መንግስትና ህዝብ ፍላጎት ምንም ይሁን ምን ቅድሚያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና መሰረታዊ ጥቅም ነው።
ግብፆች ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ያደረጉት ጥሪም ከራሳቸው የውስጥ ጭንቀትና ፍላጎታቸው የመነጨ ነው። በእኔ እምነት ማንኛውም ተቃዋሚ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ የግብፅን ጥሪ ተከትሎ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግል አንስቻለው የሚል ሃይል የተጀመረውን የህዳሴ ግደብ የሚያደናቅፍ ስራ የሚሰራ ከሆነ ይሄ ለሃገርም ለህዝብም ህልውና ፣ ሉዓላዊነትና አንድነት ያለመቆም ከመሆን ያለፈ ትርጉም አይኖረውም። ኢዴፖ ይህንን ግድብ በንቃትና በትጋት ስንከታተል ቆይተናል።በመቀጠለም ግድቡ ስራው እስኪጠናቀቅ እርዳታ ከመስጠት ባሻገር ይህንን አስመልከቶ ስብሰባ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራ አቋማችንን ለመግለፅ ዝግጁ ነን።”አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
goolgule.com

No comments:

Post a Comment