Monday, July 29, 2013

በታሪክ ሐቅ ላይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወግ የለም!!

የዐማራ ነገድ በየትኛውም ዘመን በዘር ተደራጅቶ ኢትዮጵያውን ገዝቶ አያውቅም። ነገር ግን ባለፈው 22 ዓመት ውስጥ እውነተኛ ታሪኩ በትግራይ ፋሽስቶች ተሰርዞና ተደልዞ ዐማራው ነፍጠኛ ፣ ትምክህተኛና ጡት ቆራጭ…ወዘተ ተብሎ በጅምላ ተፈርጇል። በዚህም በጅምላ የመገደል፣የመታሰርና የመፈናቀል ወንጀል ተፈጽሞበታል ፤ አሁንም እተፈጸመበት ይገኛል። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም የዐማራ ምሁር በትግራይ ባንዳዎችና በተላላኪዎቻቸው እየታተሙ ለሚሰራጩ ሀሰተኛ ውንጀላዎችና ታሪክ መሰል ልቦለዶች በመጽሐፍም ሆነ በቃል መልስ ሲሰጥ አልተስተዋለም።ለአብነት ብሥራት አማረ፣ ገብረኪዳን ደስታ፣ ዓለምሰገድ አባይ ተሰፋዬ ገብረአብና አሰፋ ጃለታ የተባሉ የወያኔና የኦነግ ጀሌዎች በታሪክ ስም በዐማራ ነገድ ላይ ለከፈቱት መሠረተቢስ የማንቋሸሽና የጥላቻ ዘመቻ አንድም የዐማራ ምሁር ምላሽ የሚሰጥ መጽሐፍ አለመጻፉ በጣም ያሳዝናል። ለአንድነት ሲባል ታሪካችንና ማንነታችን በትግራይ ፋሽስቶች ሲሰረዝና ሲደለዝ ዝም ማለት ባንዳዎችን ከሚጓዙበት የጥፋት መንገድ አልመሳቸውም። እንዲያውም ዝምታችንና ትዕግስታችን ከፍርሃት ተቆጥሮ በጅምላ “ሽንታም ዐማራ” ተብለናል። ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር ደማቸውን ያፈሰሱ አባቶቻችንና እናቶቻችን ሲቀለድባቸውና ታሪክ የሌለው ነገድ ስንደረግ አንዳንዶቻችን ከወያኔ ጋር አብረን እናጨበጭባለን።
ከላይ ከተዘረዘሩት አራት የወያኔ ጀሌዎች መካከል አንዱ የሆነው ብሥራት አማረ “ፍኖተ ገድል ከ1967 – 1977″ በሚል ርዕስ በጻፈው ልብወለድ ውስጥ ከገጽ 36-45 ስለ አጼ ምኒሊክ ሲተርክ “ምኒሊክ ማዕረጉንና ዘውዱን ለማረጋገጥ ኤርትራንና ነዋሪዎቹን ለጣሊያኖች ሸጠ። ከየትኛውም ማዕዘን የምኒሊክ ተግባራት ብንመለከተው ራሱን ከከሃዲነት ነጻ ለማውጣት የሚችልበት መንገድ የለም። ምኒሊክ የትግራይ ህዝብን በሁለት ጎራዎች ስለከፈለ ቢያንስ ለግዜው እቅዱ መሳካቱን አረጋግጠዋል” ይላል። ብሥራት በዚህ ብቻ ሳያበቃ “አክሱማዊያን ወይም ግዕዝንና የክርስትና ሃይማኖትን የተከተሉ ኤርትራና ትግራይ ብቻ መሆናቸውን በመግለጽ ባርያ መሸጥም ሃይማኖታቸው የማይቀበለው መሆኑን አውቀው ቀደም ብለው ካቆሙ ህዝቦች እንደሆኑ ታሪክ ዘግቦታል” ይለናል። ይሁን እንጂ ለዚህ የሚሆን አንዳችም ያቀረበው የታሪክ መረጃ የለም ፤ ሊኖርም አይችልም።
አሰፋ ጃለታና መስል የኦነግ ጀሌዎችም ስለአፄ ምኒልክ ጭካኔ ሲናገሩ ይሰማሉ፤ ይጽፋሉም። ግን ሁሉም የሚጽፉት ማስረጃ የሌለው፥ ከአፄ ምኒልክ ፍልስፍና ጋር የማይስማማ ፈጠራ ነው። ለምሳሌ አሰፋ ጃለታና ጃዋር መሀመድ በሚጽፋቸው መጽሀፎችና አርቲክሎች ውስጥ በተደጋጋሚ “5 ሚሊዮን ኦሮሞዎች በምኒሊክ ተጨፍጭፈዋ” ይሉናል። ነገር ግን አንዳቸውም ለዚህ ማስረጃም አያቀርቡም፤ ካላቀረቡም “በአፍ ሲወርድ ሲዋረድ ከእኛ የደረሰ ታሪካዊ ድርጊት ነው” ይሉናል። አንዳንዶቹ ደግሞ ፤ መሰሎቻቸው ዋሽተው የጻፉትን ለማስረጃነት ያቀርባሉ። የዋሾ ማስረጃ እውነትን በሚፈልጉ ዘንድ ቦታ የለውም። ይልቅስ አፄ ምኒልክ በአዋጅ ለማስቀረት ብዙ የሞከሩት የወንድን ብልት መስለብና “ሲዳምቲቲን” (ዐማራን) ሳይገድል ጠጉር አለመላጨት የማን ባህል እንደሆነም እባካችሁ ኦሮሞዎቹን ጠይቁልን።
ከላይ በመጠኑ ለመግለጽ እንደተሞከረው የወያኔም ሆነ የኦነግ ፀሐፊዎች ተመሳሳይነት አላቸው። ሁለቱም አፄ ምኒሊክን አምርረው ይጠላሉ፤ ጥላቻቸውንም እውነተኛ ታሪካቸውን በመሰረዝና በመደለዝ “ኮምፒዩተር” ላይ ተቀምጠው በሚጽፉት ተረተ-ተረት ለመተካት ይሞክራሉ። ያለፈውን ለታሪክ እንተወው ብለን ነው እንጂ ፤ ታሪክን ለፖለቲካዊ ዓላማ ማዋል ካስፈለገ ፤ እውነተኛው ታሪክ ግን ከዚህ እንደሚከተለው ይነበባል።
በቅድሚያ ብሥራት አማረና ሌሎች የትግራይ ባንዳዎች አፄ ምኒሊክንና ዐማራን ለምን በቀንደኛ ጠላትነት ፈረጁት ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት በርካታ የታሪክ ዋቢዎችን ማቅረብ ይቻላል። ነገር ግን ጊዜና ቦታ ለመቆጠብ በጣሊያን ወረራና በአሰብ ወደብ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን አነሳለሁ። አስብ ወደብ በ1861 ዓ.ም ሱልጣን ኢብራሂም በተባለ አንድ ግለሰብ ሩባቲኖ ለተባለ የጣሊያን የግል የመርከብ ኩባንያ በ3,100 ማሪያ ቴሬዛ ተሸጠ(Martin, 2008)። በወቅቱ ጁሴፔ ሳፔቶ በተባለ ጣሊያናዊ የጂኦግራፊ ባለሙያና ሚሲዮናዊ በተሰበሰበ የተጠናከረ ጥናትና መረጃ አማካይነት በሩባቲኖ የመርከብ ኩባንያ ስም ጣሊያኖች በአሰብ ወደብ ለመጀመሪያ ጊዜ ባንዲራቸውን አውለበለቡ፡፡ ይህ ኩባንያም ለ13 ዓመታት ወደቡን አስፋፍቶ ሲገለገልበት ከቆየ በኋላ በ1874 ዓ.ም የኢጣሊያ መንግሥት አሰብ ወደብን ከሩባቲኖ ኩባንያ ላይ በ20,800 ማሪያ ቴሬዛ በይፋ ከገዛ በኋላ ሰኔ 19 ቀን 1874 ዓ.ም አሰብ የኢጣሊያ ግዛት መሆኑን በአዋጅ አሳወቀ፡፡ በመቀጠልም ለዋናው የኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ወረራ እንዲረዳው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በ1876 ዓ.ም. በምስጢር ከተስማሙ በኋላ የካቲት 5 ቀን 1877 ዓ.ም. የኢጣሊያ ጦር ምጽዋን ተቆጣጠረ፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን አፄ ዮሐንስ በመጀመሪያ የትግራይና ኤርትራን ንጉሠ ነገሥት፤ ከ1864 ዓ.ም ሕይወታቸው መተማ ላይ እስካለፈበት እስከ 1871 ዓ.ም ደግሞ ራሳቸውን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ብለው ሰይመዋል። ይሁን እንጂ የሸዋ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ እውቅና አልሰጧቸውም። የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ እውቅና ያጡት አፄ ዮሐንስ ወራሪውን የጣሊያን ጦር ከመዋጋትና ከግዛታችው ከማስለቀቅ ይልቅ ፤ የአፄ ምኒሊክን እውቅና ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድረገዋል። ከበርካታ ጥረቶቻቸው አንዱ በ1874 ዓ.ም አፄ ምኒሊክ ሴት ልጃቸውን ለአፄ ዮሐንስ ወንድ ልጅ እንዲድሩላቸውና በጋብቻ ተሳስረው አፄ ምኒሊክ የአፄ ዮሐንስ አልጋ ወራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ሞክረዋል። ነገር ግን ጋብቻው ባለመሳካቱና ሁለቱ ተቀናቃኞች በተለያየ የተጽኖ ክልል ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው አፄ ዮሐንስ ሰሜን ኢትዮጵያ ፤ አፄ ምኒሊክ ደግሞ ደቡብና ምሥራቅ ኢትዮጵያን ለመግዛት ተሰማምተዋል።
በዚህም ስምምነት መሠረት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚመጣን ማንኛውምን ወራሪ ኃይል መመከት የአፄ ዮሐንስ ኃላፊነት ነበር። ነገር ግን ብስራት አማራና መሰል የትግራይ ባንዳዎች ይህንን ሀቅ ወደ ጎን በመተው ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከመሆናቸው በፊት አፄ ዮሐንስ ለፋሽስት ለጣሊያን የሸጧትን ኤርትራ ፤ “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” እንዲሉ “ምኒሊክ ማዕረጉንና ዘውዱን ለማረጋገጥ ኤርትራንና ነዋሪዎቹን ለጣሊያኖች ሸጠ። ከየትኛውም ማዕዘን የምኒሊክ ተግባራት ብንመለከተው ራሱን ከከሃዲነት ነጻ ለማውጣት የሚችልበት መንገድ የለም። ምኒሊክ የትግራይ ህዝብን በሁለት ጎራዎች ስለከፈለ ቢያንስ ለግዜው እቅዱ መሳካቱን አረጋግጠዋል” ይሉናል። እኛ ግን የትግራይ ባንዳዎችን እንዲህ የሚል ቀላል ጥያቄ እናቀርብላቸዋለን በጣም ጥሩ “ምኒሊክ ማዕረጉንና ዘውዱን ለማረጋገጥ ኤርትራንና ነዋሪዎቹን ለጣሊያኖች ከሸጡ ” ለምን በ1888 ዓ.ም ከሸዋ ተነስው ትግራይ ድረስ ዘምቶ ፋሽስት ጣሊያንና የትግራይ ባንዳዎችን አድዋ ድባቅ በመምታት መላውን ዓለም ያስደመመ ታሪክ አስመዘገቡ? ምናልባት ሰለ ዓድዋ ድል አልሰማንም ካላሰማችሁ እነዚህን መጽሀፎች ለማንበብ ሞከሩ:-
1. The Battle of Adwa: Reflections on Ethiopia’s Historic victory Agains European Colonialism,Edited by Paulos Milkias & Getachew Metaferia, 2005.
2.Armies of the Adowa Campaign 1896: The Italian Disaster in Ethiopia, Edited by Martin Windrow.
3.The Battle of Adwa : African Victory in the Age of Empire, edited by Jonas Raymond, 2011
ይህን ጽሐፉ ከማጠቃለላችን በፊት አንድ ተጨማሪ ጥያቄ መመለስ ያለብን ይመስለኛል። አፄ ዮሐንስ ለምን በ1871 ዓ.ም መተማ ዘምተው ሞቱ? ይህ ጥያቄ ገብረኪዳን ደስታ በ1998 ዓ.ም “የትግራይ ሕዝብና የትምክህተኞች ሴራ ከትናንት እስከዛሬ” በሚል ርዕስ የጻፈውን ተራ ልብወለድ ላነበበ መልሱ “በአፄ ምኒሊክና በትምክህተኞች በተፈጸመባቸው ሴራ” የሚል እንደሚሆን አያጠራጥርም። ሀቁ ግን የጣሊያን ፋሽስቶችን ማሪያ ቴሬዛና ክርስቲያና የተቀበለው አፄ ዮሐንስ ስብዕና ለእስልማና ከፍተኛ ጥላቻ ስለነበረው ድርቦሾችን(ሱዳኖችን) መተማ ላይ ጦርነት ለመግጠም አላቅማም። ይሁን እንጂ በጦርነቱ በለስ የቀናቸው ድርቦሾች የአፄ ዮሐንስን አንገት ቀልተው ወስደውታል።
ከላይ እንደተገለፀው አፄ ዮሐንስ ለእስልማና ከፍተኛ ጥላቻ ስለነበራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊሞችን አስገድዶ ክርስቲያን ከማድረግ እጅና እግር እስከ መቁረጥ የደረሰ ግፍና ሰቆቃ ፈጽመዋል። ለምሳሌ፥ በ1870 ዓ.ም. ቦሩ ሜዳ ላይ በንጉሠ ነገሥቱ በአፄ ዮሐንስ ዋና ወምበርነት የሃይማኖት ክርክር ተድርጎ ነበር። የተረቱት መላሳቸው እንዲቆረጥ አፄ ዮሐንስ ሲፈርዱባቸው እንዲምሯቸው ሊቃውንቱ በብዙ ለምነዋቸው ነበር። ግርማዊነታቸው ግን አገር የከዱ ይመስል፥ “በፈጣሪዬ ላይ በድፍረት ያልሆነ ቃል ተናግረዋልና አልምራቸውም ብለው እጅ እግራቸውንና ምላሳቸውን አስቆረጧቸው።” ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ የወያኔ ጀሌዎች ባንዳነታቸውን ለመደበቅ ታሪክ እያሉ ተረት ተረት ይነግሩናል።
በታሪክ ሐቅ ላይ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወግ የለም። እውነት እንደ ወረደ ለትውልድ ይውረድ ! ባንዳ ከባዕዳን ወራሪ ባላነሰ ደረጃ ኢትዮጵያን ጎድቷታል፤ አሁንም እየጎዳት ይገኛል። ታሪካችን ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ሳንወድ በግድ ተጫነብን ከሚሉ ከሃዲዎችና ባንዳዎች ነፃ ሆኖ አያውቅም። ይህ ትውልድ የታሪካችንን ታሪካዊ ፍሰት አይጣ ! ጀግኖች ሀገራችንን ጠብቀው ያቆዩት በየዘመኑ ባዕዳንና ባንዳዎችን ከትቢያ ጋር በማዋሐድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይህ እውነት ነው ! እውነትም ይህ ነው ! ሌላ እውነት የለም !
(ማስታወሻ:-በአክሱም ስልጣኔና ሃውልቶች ባለቤትነት ዙሪ ቀጣይ ጽሑፍ ይኖራል።)
References:-
1. A history of Abyssinia, by A. H. M. JONES and ELIZABETH MONROE, 1935
2. Modern Italy: 1871 to the Present, by Martin Clark, 2008.
3. A Journey through Abyssinia to the Nile, by Herbert Weld Blundell, 1900.
 Image

No comments:

Post a Comment