Sunday, October 13, 2013

በጎንደር ከተማ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ሞተው መገኘታቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



October 13, 2013

በደረሰን ዘገባ መሰረት በጎንደር ከተማ በተለምዶ አራዳ አየተባለ በሚጠራው አክሱም ሆቴል አከባቢ መስከረም 26,2006 ዓ/ም ሌሊት ገዳያቸው ያልታወቁ ምክትል ሳጅን ይፍጠር ዓሊና ምክትል ሳጅን ደምመላሽ ይርዳው የተባሉ ሁለት የፌደራ ፖሊስ አባላት ሞተው ተገኝተዋል፣ ከሟቸቹ አንዱ በጩቤ ተወግቶ የተገደለ ሲሆን በሁለተኛው ላይ በዓይን የሚታይ አካላዊ ጉዳት አልነበረውም፣ ታጥቀውት የነበረውንም ትጥቅ በገዳዮቹ መወሰዱን ቷውቋል፣ በስርዓቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት የሚደርሰው ጥቃት በሁሉም የሃገሪቱ ከተሞች የሚታይ ሲሆን በጎንደር ከተማ በሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት የደረሰውን ግድያ በIህአዴግ ስርዓት በተማረሩ የስርዓቱ ኗሪዎች የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ በከተማዋ በሰፊው ይወራል::

Source : TPDM

No comments:

Post a Comment