Friday, February 7, 2014

ወደ አዋጅነት ይቀየራል የተባለው ‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና የዕድሳት አገልግሎት›› ረቂቅ መመርያ ኃላፊነት የጎደለው እንዳይሆን የብዙዎች ስጋት ነው።

ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 

 የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ‹‹ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ጽ/ቤት ጋራ በመተባበር ያዘጋጀውና ከጥር 30 – የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ – ሌዊ ሪዞርት ‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና የዕድሳት አገልግሎት›› ረቂቅ ላይ ለውይይት እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ከመመሪያ ወደ ዐዋጅነት ይቀየራል እየተባለ የሚነገርለት መመርያ ምንነት እስካሁን በዝርዝር አልታወቀም።

‹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዋጁ ረቂቅ እንዲሰጣት እና አስተያየትና አቋም ለመውሰድ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ  አለማግኘቱን ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ብሎግ ጥር 28/2006 ዓም ገልጧል።

በኢትዮጵያ ከ 1952 ዓም ወዲህ ምንም አይነት ሃይማኖትን የተመለከተ አዋጅ  ወጥቶ አያውቅም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከ 40 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያሏት እና ክርስትና ከተመሰረተ ጀምሮ ላለፉት ከ 2000 አመታት በላይ ለሆኑ ዘመናት  በኢትዮጵያ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የፍቃድ እና የምዝገባ መስፈርት ተጠይቃ እንደማታውቅ ይታወቃል።ደርግም በዘመኑ ምንም አይነት ሃይማኖታዊ አዋጅ አለማውጣቱ ይታወሳል።ይህ ወደ አዋጅ ያድጋል የተባለው መመርያ ኃላፊነት የጎደለው እንዳይሆን የብዙዎች ስጋት ነው።

ጉዳያችን
ጥር 30/2006 ዓም 

ሰበር ዜና በሪያድ የኢትዮጵ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ አመራ ማምሻውን ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ሳይጀመር በሁከት ተበተነ !

Ethiopian Hagere's photo.Ethiopian Hagere's photo.

በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኮሚኒቲ ማህበር ስራ እመራር ኮሚቴ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በታደሙ አባልት እና የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ በሚታወቁት የቀድሞው የኮሚኒቲ ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ደጋፊዎች መሃከል ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ወደ ግጨት አምርቶ እንደነበር ምንጮች ከሪያድ ገልጸዋል። 

የስብሰባውን ታዳሚ ግራ ያጋባው ይህ ግጨት መነሻው የቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር እንደነበሩ የሚነገርላቸው ሼክ ሙሰጠፋ ሁሴን ለምን ከስልጣኔ ተነሳሁ በሚል በምከትል ሊቀመንበሩ አቶ ቃሲም ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች ሼክ ሙስጠፋ ከስብሰባው በፊት ሲያስተባብሯቸው የነበሩ ከ 50 የሚበልጡ ደጋፊዎቻቸው ባስነሱት ሁከት የመስብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ፡ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ ማምሸቱን ጠቅሰዋል። ....
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ በአካቢው የተፈጠረውን አለመረጋጋት የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባውን ለሌላ ቀን ለማስተላለፍ መገደዱን የሚገልጹት ምንጮች የሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች ጩቤ ታጠቀው ወደ አዳራሹ ገብተው እንደነበር ቢገልጹም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ውስጥ ዛሬ በተነሳው አንባጓሮ የተጓዳ ሰው እደሌለ አረጋግጠዋል ። ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ቀደም ሲል በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚቲ ለቀመንበር እንደንበሩ እና ምንጩ በግልጽ የማይታወቅ ሁለት ሚልዮን ሪያል በግል ካዝናቸው ተገኝቶ በሳውዲ መንግስት የደህነንት ሃይሎች ታስረው መክረማቸውን ተከትሎ የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በማህበሩ መተዳደሪያ ህገ ደንብ መስረት የስልጣን ሽግሸግ ለማድረግ በመገደዱ ግለስቡን ከሃላፊነታቸው ማስወገዱን ይናገራል። ዛሬ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ተከስተ በተባለው ሁከት በሳውዲ የኢትዮጵያው አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን እጅ እንዳለበት የሚገልጹ ወገኖች ሃገር እና ህዝብን ወክሎ ከተቀመጠ አንባሳደር የሚጠበቅ እንዳልሆነ በማውሳት ድርጊቱን አውግዘዋል።

ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ዝምድናን መከታ በማድረግ በኤንባሲው ማህተም ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጀቶች ገንዘብ በመሰብሰብ ከአንባሳደሩ ጋር ለግልጥቅማቸው ሲያውሉ የነበሩ መሆናቸውን የሚያወጉ የሪያድ ነዋሪዎች ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ኢትዮጵያ ውስጥ በከፈቷቸው 2 ኤጀንሲዎቻቸው በመታገዝ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እስከ 7 መቶ ዶላር በመሰብሰብ በእህቶቻችን ህይወት ሲነግዱ የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ በህገወጥ የሃላ ንግድ ተሰማርተው ከቀርብ ግዜ ወዲህ የከበሩ ሃብታም ነጋዴ እና የአንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ባለው ለታ መሆናቸው ይናገራል ።

ዛሬ ተቀሰቀሰ በተባለው ግጨት ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ የዲያስፖራውን ሃልፊ ለማንገጋር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።
በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን ከወኒ መወጣት እና እጃቸው ላይ ተይዞ ስለነበረው 2 ሚልዮን ሪያል « 10 ሚልዮን ብር » የድረሱንን መረጃዎች ወድፊት አጠናቅረን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፤