Friday, June 28, 2013

ESAT Daily News - DC June 28, 2013 Ethiopia


በአዲስ አበባ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ምዝገባ የተመዘገበው ህዝቡ ቁጥር መንግስት በቅርቡ ካወጣው አዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር ጋር የማይጣጣም ነው ሲሉ አንድ ባለሙያ ገለጹ

ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን ሰሞኑን የአዲስ አበባ ህዝብ ቁጥር 2 ሚሊዮን 900 ሺ መሆኑን ቢገልጽም፣ በ10 – 90 እና በ20 – 80 እየተባለ በሚጠራው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተመዘገበው ህዝብ ቁጥር ኤጀንሲው ያቀረበው አሀዝ  ትክክል አለመሆኑን የሚያሳይ ነው በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ ቀድሞ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ባለሙያ ለኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ ገለጹ።
ባለሙያው እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ መንግስት ከ800 ሺ እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ለቤት ፍለጋ እንደሚመዘገቡ ከገለጸ የከተማዋ ነዋሪ የዚህን አሃዝ ከ4 እስከ 5 እጥፍ ሊሆን ይችላል ማለት ነው ብለዋል።
መንግስት እስከሁን ከ700 ሺ ህዝብ በላይ እንደተመዘገበ፣ በሚቀጥሉት ቀናትም ተጨማሪ 100 ሺ ህዝብ ሊመዘገብ እንደሚችል መግለጹን ያወሱት ባለሙያው፣ ቀደም ብሎ ቤት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከ300 እስከ 600 ሺ የሚገመቱ ከሆነ በአጠቃላይ በከተማው ከ1 ሚሊዮን 100 ሺ እስከ 1 ሚሊዮን 400 ሺ ሰዎች ቤት ይፈልጋሉ ማለት ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ነባራዊ ሁኔታ አንድ ሰው ከ3 እስከ 4 ልጆች ሊኖሩት እንደሚችል የገለጹት እኝህ ባለሙያ በዚህ ስሌት መሰረት የከተማው ህዝብ ቢያንስ ከ3 ሚሊዮን 500 እስከ 5 ሚሊዮን 500 ሺ ሊደርስ ይችላል ብለዋል።
አሀዙ በቤት ምዝገባ ያልተካተቱትን እጅግ ደሀ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም አድራሻ አጥተው የተቀመጡትን ነዋሪዎች ካካተተ ከተማው ህዝብ ብዛት ከ5 ሚሊዮን ሊበልጥ እንደሚችል ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ መስተዳድር የከተማውን ህዝብ ቁጥር ከ5 ሚሊዮን በላይ አድርጎ ማቅረቡ ትክክል ሊሆን እንደሚችል፣ ስህተቱ ያለው ማእከላዊ ስታትስቲክስ ባወጣው መረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የህዝብ ቁጥርን መቀነስ ለምን አስፈለገ የተባሉት ባለሙያው አንዱ ምክንያት በመስሪያ ቤቱ አቅም ችግር ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው ፖለቲካዊ ምክንያት ሊኖረው ይችላል ሲሉም አክለዋል። ክልሎች የፌደራል መንግስቱን የገንዘብ ድጎማ የሚያገኙት በህዝባቸው ቁጥር መጠን በመሆኑ ትክክለኛ የህዝብ ቁጥር ካልታወቀ በማህበራዊ አግልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አስረድተዋል።

ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት

ነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የ…
የሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡
…በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንበርና በነሲብ ነበር እስትንፋሷ ውሎ እሚያድረው፡፡ ሰውዬው የሚፈልገው ሁሉ እዛው ባለበት እየቀረበለትና እንደአንበሣ በብረት አጥር ውስጥ እየኖረ በስልክና በደብዳቤ ሲገዛንና ሲሸጠን ኖረ፤ ፈጣሪ በወደደው ሰዓት ያን የእፉኝት ልጅ ወሰደ፡፡ ጦስ ጥንቡሱ ግን አሁንም እንደገነነ አለ፤ መቃብር ውስጥ ሆኖ በመግዛት መለስ አንደኛ ሣይሆን አይቀርም፡፡ ይቺ ራዕይ የሚሏት ሀገርን የማጥፋት ተልእኮ በየወያኔው ጭንቅላት ውስጥ ሠርፃ ገብታ እነሱንም እኛንም ዕረፍት ነስታለች፡፡ አዳሜ እየተነሣ “ከመለስ ራዕይ ጋር ወደፊት!” ይላል፡፡ “ራዕያቸው ምን ነበር?”ተብሎ ሲጠየቅ በቅጡ የሚመልስ የለም፡፡ የፈረደበት የአባይ የሚሌኒየም ይሁን የሕዳሴ ግድብ አለ፡፡ እሱው መሰለኝ ትልቁ ራዕይ፡፡ በሌሎች ሀገሮች እዚህና እዚያ የተትረፈረፈ የወንዝና የኩሬ ግድብ እኛ ሀገር ሲደርስ ብርቅ ሆኖ ሰውን በመዋጮና በተስፋ ቁንጣን እየገደለ ነው፡፡ ራዕዩ ይሄው ነው፡፡ በተረፈ በሚሊዮኖች ላብና ደም ጥቂት ቅንጡ ሀብታሞችን የመፍጠር ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለብዙ አሠርት ዓመታት ተከፍሎ በማያልቅ ብድር መንገድና ሕንጻ መሥራት ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ይበልጡን ለፖለቲካ ፍጆታ በሚመስል መልኩ የሀገርን ሀብት ለተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች በማዋል በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችና በኮብል ስቶን ሥራ አደራጅቶ ዜጎችን በጥቅም መከፋፈል ራዕይ ካልሆነ በስተቀር፣ ለዕይታ ሳይቀር የሚዘገንን የኔቢጤ (ለማኝ)፣ ወፈፌና ሰካራም፣ ብስጩና ግልፍተኛ፣ በረንዳ አዳሪና የዐዋቂና ሕጻናት ሴተኛ አዳሪዎችን በየዋና ዋና ከተሞች በብዛትና በስፋት ማምረት በልዩ ራዕይነት ካልተመዘገበ በስተቀር የመለስ ራዕይ ብሎ ነገር የሚጨበጥ ነገር አላየሁም – በዋና ራዕይነት እንዲመዘገብለት ከተፈለገ ዋናው የመለስ ራዕይ የተከፋፈለችና የደከመች፣ ለኤርትራ በምንም መንገድ የማታሰጋ ጥንጥዬ ኢትዮጵያን በሂደት መፍጠር ነው – ይሄ የሚታየው ብልጭልጭ ነገርና የዕድገት እመርታ የሚመስል የፎቅና የአስፋልት ወይም ሌላ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ሁሉ መለስ ሳይወድ በግዱ በሥሩ ባሉ ጥቂት ሀገር ወዳድ ወያኔዎች አማካይነት የተከሠተ – ‹ከሬዲቱ› ለርሱ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን ለማለት ነው- በመለስ የጥፋት ራዕይና በአፈጻጸሙ መካከል እንደሳይድ ኢፌክ ሊቆጠር የሚችል አጋጣሚ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው – መለስ ኢትዮጵያን በማጥፋት ሂደት ተጠምዶ ሳለ ያን ሂደት ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ኢትዮጵያዊ መስሎ መታየት ወይም ማታለል ስላለበት ለዚያም ሲባል አንዳንድ የሚታዩና የሚጨበጡ ነገሮችን ማድረግ ስለነበረበት በኢትዮጵያዊ ስብዕና ዓለም አቀፍ አመኔታን ለማግኘት ሲል ባልጠበቀው ሁኔታ ከእጁ ሾልከው ክፉ ገጽታውን በጥሩ ቅባት ያዋዙለት አጋጣሚዎች ነበሩ ወይም ናቸው(ለዚህም ይመስላል ብዙ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰው ‹ምትሃት› ተወናብደው የወያኔን ትክክለኛ ተፈጥሮ እንዳያውቁ የተደረገውና ዐይናቸው በወያኔ ጥፋት ላይ እንዳያማትር እንዲያውም በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም የርሱ ነገረ ፈጅ እስከመሆን እንዲደርሱ የተሞከረውና አሁን አሁን ደግሞ እየቆጫቸው መምጣቱን እየተገነዘብን ያለነው…) ፡- በሕክምና አነጋገር ለጉበት የወሰድከው መድሓኒት ኩላሊትህን ሊጎዳ ይችላል – ኔጌቲቭ ሳይድ ኢፌክት፡፡ ለራስ ምታት የወሰድከው መድሓኒት ከጨጓራ ህመምህ ሊፈውስህ ይችላል – ፖዚቲቭ ሳይድኢፌክት፡፡ የመለስም የአባይ ግድብና ሌላው ግርግር ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ እውነት ያለፈ አይደለም፡፡ እውነተኛ የሕዝብ ፍቅርና የሀገር መውደድ ስሜት ቢኖረው ኖሮ… ታውቁት የለ – ምን ወደዚያ ውስጥ ከተተኝ … ፡፡ ይቅርታ – በዋናው የሃሳብ መስመሬ ላይ እንደአረብ ጣቢያ ጣልቃ እየገባ ኳርት የሚለዋውጥብኝና እንድዘባርቅ የሚያደርገኝ ዘርፈ ብዙው የሀገራችን ችግር በመሆኑ ታገሱኝ፡፡
ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደረ ያለው ማን ነው? የት ተቀምጦ? በስምና በአካል ይታወቃል ወይ? ብለን እንጠይቅ፡፡
እኔ በ
ግል እንደምታዘበው ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እያስተዳደራት የሚገኘው ሰው አይመስለኝም፤ መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ ግማሹ ቅዱስ ነው፤ ግማሹ ደግሞ እርኩስ ነው – አሁንም በኔ ዕይታ፤ ዕይታየ ትክክል ነው ትክክል አይደለም የኔ ጉዳይና የናንተ የኅሊና ፍርድ ነው፡፡
ቅዱስ ያልኩት በተከመሩብን ሁለንተናዊ የፖለቲካና ማኅረሰብአዊ ችግሮች የተነሣ እርስ በርስ ተበላልተን እንዳናልቅ እየረዳን ያለ አንዳች ኃይል መኖሩን ከመገመት ባለፈ ስለማምን ነው፡፡ ይህ ኃይል ባይኖር ኖሮ በሀገሪቱ እንደሚታየው ጭቆናና የኑሮ ውድነት አንድም ሰው በአንጻራዊ ሰላም ከቤት ወጥቶ ወደቤት በሰላም ባልገባ ነበር – እውነቴን ነው የምለው ይህን ዓይነት ደግ መንፈስ ባይጠብቀን ኖሮ ተበላልተን ለማለቅ የሚፈጅብን ጊዜ ሰዓታትን ብቻ በወሰደ ነበር(ሦርያንና ሊቢያን… ያዬ ይፍረድ – ሊያውም ከኛ በእጅጉ ያነሰ ጭቆናና እንግልት ደርሶባቸው!) ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠረው በረንዳ አዳሪ፣ ሥራ አጥና ቤት አልባውም በ”ሰላም” ካደረበት ከየቱቦውና ከየላስቲክ ቤቱ ወጥቶ በቀጣዩ ቀን በየአደባባዩ ባላየነው ነበር፡፡ ካለአንዳች አለሁህ ባይ የመንግሥት መዋቅር በራሱ ኃይልና እንዲሁ በኪነ ጥበቡ ርሀብና ችግሩን ችሎ የሚኖር ሕዝብ ማየት የሚገርምም የሚሰቀጥጥም በድንቃ ድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባውም የሚሌኒየሙ ተዓምር ነው፡፡ አንድም ሥራና አንድም ደመወዝ የሌለው በሚሊየን የሚገመት ዜጋ ቀኑን አለበቂ ምክንያት እዚህና እዚያ ሲንከራተትና ሲንገላወድ ውሎ አሁንም ልድገመውና በየሥርቻውና በየሥርጓጉጡ በ”ሰላም” አድሮ የቀጣይዋን ዕለት ጀምበር ለማየት እባቡር መንገዱ ላይ ተሰጥቶ መታየቱ የትንግርትን እንጂ የመንግሥትን ኅልውና አያመላክትም፡፡ በዚህ ምክንያት የሀገራችንን በትረ ሥልጣን ከያዙ ሥውር ኃይሎች ውስጥ የተወሰነውን ‹የፓርላማ ወንበር› የተቆናጠጠው አንዳች የተቀደሰ ነገር መሆን አለበት ብዬ አምለሁ፡፡ እንዲያ ባይሆንማ ማን እየተዘባነነ ማንስ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በርሀብና በጥም እየተሰቃዬ ይኖር ነበር? ሀሰት ነው?
በሌላ በኩል የሚታየውን መቋጫ የሌለው የግፍ አገዛዝና የዘረኝነት ቱማታ ስንቃኝ ከነዚህም ጋር የሚቆራኘውን አጠቃላይ የድቀት ሕይወት ስንታዘብ በተለይ በፖለቲካውና በሃይማኖቱ አመራር ረገድ የእርኩሱ መንፈስ ምን ያህል የበረታ እንደሆነ መረዳት አይቸግርም፡፡ ስለዚያም ምክንያት ይመስለኛል ይህ በመለስ የሙት መንፈስ የሚነዳ የአጋንንት መንጋ አንዳች ሥፍራ ተደብቆ ደህና ሰው ወደ አመራር ዝር እንዳይል እነአዜብንና በረከትን እየተመሰለ በላያችን ላይ የሚያንዣብብብን፡፡ እንደሚወራው አዜብ ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሆና አይደለም ጽዳትና ዘበኛም ሆና ብትመጣ እንኳን ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት፡፡ በሌላ ቦታ እያለች የማዘጋጃ ቤት ሹሞችን በስልክ እያስፈራራችና በአካል እያስጠራች ስንትና ስንት ግፍና በደል መፈጸሟ እየታወቀ አንድያውን በዚያ ቢሮ ስትገኝማ ከተማዋን ብቻ ሣይሆን እኛን ነዋሪዎቹን በጅምላና በችርቻሮ ባወጣንበት ዋጋ ቸብችባ በጥቂት ወራት ውስጥ ትጨርሰናለች፡፡ አዜብ – ዮዲት ጉዲት – እንኳንስ ማዘጋጃ ቤት ገብታ በሩቅ እያለችም – ለብልግናየ ይቅርታና – ለውሽማዋም ይሁን ለምትፈልገው ማንኛውም ሰው ቦታ ለማሰጠት፣ መብራት ለማሰጠት፣ የንግድ ፈቃድ ለማሰጠት፣ (እንዳስፈላጊነቱ ተመላሽ ሊደረግ ወይ ላይደረግ የሚችል) የባንክ ብድር ለማሰጠት፣ በመንግሥት ወጪ ረጃጅም የስልክና የውኃ መስመር ለማዘርጋት፣ የፈለገችውን ለማሾም ወይም ለማሻር፣ ንጹሕን ሰው ካለበደልና ጥፋቱ ዘብጥያ ለማስወረድ፣ በጥፋቱ የታሠረን በቅጽበታዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ፣ የዜጎችን ሀብትና ንብረት በሕግ ሽፋን ለማዘረፍና ለራሷ ካምፓኒዎች ወይም ለመሰላት ለማሰጠት፣ በነባርና አዳዲስ የአክሲዮን ካምፓኒዎች ራሷን በአባልነትና በቦርድ ሰብሳቢነት ለማስገባት፣ ወዘተ. ታደርገው የነበረውና አሁንም ከማድረግ የማትመለሰው አቅል ያጣ ሩጫ በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ሴትዮዋ ለገንዘብና ለእንትን ሲሏት ገደል እንደምትገባ የሚያውቋት ይመሰክራሉ – አጉል ተፈጥሮ፤ ከምን ዓይነት ሥጋና ደም ተፈጥራ ይሆን ወገኖቼ? በዚህ ዓይነቱ ለከት የሌለው የገንዘብና የሀብት ፍቅሯ ነው እንግዲህ ሰውዬውን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንደውሻ አሥራ በርሱ ስምና በርሷ ድፍረት ባጠራቀመችው ንዋይ ከዓለም መሪዎች መለስን በሀብት የሚበልጠው እንዳይገኝ ከፍተኛ ጥረት ላይ የነበረችው – በየባንኩ ብዙ ገንዘብ ታቁር የነበረችው፣ በየዓለም ማዕዘናት ብዙ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን ትመሠርት የነበረችው፣ በፍቅረ ንዋይ መታወሯ እንዳንዳች እያደረጋት እንዲያ ዐይን ባወጣ መንገድ ትዝብት ላይ ወድቃ የነበረችው፡፡ ይህች በገንዘብና በእንትን ፍቅር ያበደች የድብቁ ቢግ ብራዘር ተወዳዳሪ ሴት አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብትገባ ምን ተዓምር ልትሠራ እንደምትችል ገምቱ – የምን መገመት ነው – ፍንትው ብሎ እየታዬ! የስንቱን ቤት እንደምታፈናቅልና ባወጣ እንደምትሸጥ፣ ስንቱን የኪስ ቦታ እንደምትቸበችብ፣ እንደ አንደኛው ባሏ ‹የዐይናችሁ ቀለም አስጠላኝ› እያለች ስንቱን ምሥኪን ሰው ከሥራና ከደመወዝ እንደምታግድ፣ እንደምታሳስርና ደብዛ እንደምታስጠፋ፣ ስንትና ስንት የሀገር ማፈሪያ ወንጀልና የቁጭ በሉ አሣፋሪ ድርጊቶችን እንደምትሠራ፣ ስንቱን ኮበሌ ካልተኛኸኝ እያለች ከትዳሩና ከጤናማ ኑሮው እንደምታፈናቅል (“አሮጊት ለምኔ! ገንዘብና ሥልጣን ባፍንጫየ ይውጣ!” ብሎ አሻፈረኝ የሚልን መቀመቅ እንደምታወርድ)፣ … በበኩሌ ቁልጭ ብሎ ይታየኛል – እባካችሁን ‹ህልም እልም› ብለን ሁላችን እናማትብበት፡፡ አዜብ ብሎ ከንቲባ? ወያኔ ይህን ካደረገ በርግጥም ራሱን ለማጥፋት ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ይህችን የአጋንንት ውላጅ የባንዳ ልጅ ማሳረፍ ይገባል – በሰላም፡፡ በቃ – በመለስ ቀብር እንዳለችው ልጆቿን በማሳደግ ፈተና ላይ ብቻ ታተኩርና በዚያው ትታይ፡፡
አዜብ በሌብነቷ አይደለም ሹም አትሁን እያልኩ የምከራከረው፤ በሌብነቷ ከሆነ መብቷ ነው፡፡ ዓለማችን በሌቦችና አጭበርባሪዎች የተሞላች በመሆኗ የርሷ ሌባ መሆን እንግዳ ነገር አይደለም – በአመራርም ሆነ በተራ ዜጋነት ሌባና አጭበርባሪ ሀገር ምድሩን ሞልቶታል፡፡ አዜብ በተፈጥሯዊ ደመ ሞቃትነቷና ያንንም ተከትሎ በጉልህ ስለሚንጸባረቅባት የሴሰኝነት ጠባይዋ አይደለም ሹም እንዳትሆን የምመኘው፡፡ ያም መብቷ ነው – ካልሰለቻት እንኳንስ ነባር ታጋዮችን አዳዲሶቹንና እምቦቀቅላ ታጋዮችንም ታነባብራቸው፡፡ አዜብም ሆነች ቤቲ በተፈጥሮ የተሰጣቸውን መብት እስከፑንት (ላንድ) ቢጠቀሙበት የነሱ ጉዳይ እንጂ የማንም ራስ ምታት ሊሆን አይገባም፡፡ እኔን ክፉኛ የሚያሳስበኝ ድንበር የማያውቀው ውሸቷ ነው፡፡ በተራ ቃል ‹ውሸታም› መባል በፍጹም አይመጥናትም፡፡
በባህር ዳሩ የወያኔ ስብሰባ የተናገረችው ውሸት ስለሷ ባሰብኩ ቁጥር ስለእውነት በጣም ያመኛል፡፡ በዚያ ስብሰባ ‹መለስ ከዓለም መሪዎች በደመወዙ ብቻ ቤተሰቡን እያሰቃየ የኖረ ብቸኛው መሪ ነው፤ ከስድስት ሺ ብር ደመወዝ ለኢሕአዲግ ተቆርጣ በምትደርሰው አራት ሺህ ምናምን ብር ወርን ከወር እየጣጣፍን በመከራ ሲያኖረን የነበረና አእምሮውን ብቻ ይዞ የተወለደ… ይህ ሊሠመርበት ይገባል ፤ ሰው የሚለው አይደለም – እርሱ በዚያች ትንሽ ደመወዝ ብቻ ኖሮ ያለፈ የተለዬ መሪ ነው…› እያለች የቀላመደች ዕለት ስለርሷ ጨረስኩ፡፡ ስለርሷ ብቻም አይደለም፡- ስለወያኔ/ኢሕአዴግም ያኔውን ጨረስኩ፡፡ አንድ አንጋፋ ድርጅት ያን የመሰለ በሬ ወለደ ዓይነት ነጭ ውሸት ሰምቶ እርምጃ አለመውሰዱ ገርሞኛል – የዚያን ድርጅት የለዬለት ባዶነትም አረጋግጫለሁ፤ የሴትዮዋ ንግግር እውነትነት ቢኖረውም እንኳን የሀገርንና የድርጅትን ምስል በማጠየም ረገድ ቀልማዲት ያደረገችው ነገር እጅግ ሰቅጣጭ በመሆኑ በሕይወት የመኖርን መብት ሳይጨምር ከብዙ ነገር ልትታገድ በተገባት ነበር፡፡ ሕዝብ በሆነ ምክንያት በይሁንታ አፉን ቢለጉም እውነት እንዳይመስላቸው፡፡ ሕዝቡ በዕውቀት ከነሱ ስለሚበልጥ በዚያን ሰሞን ይህን የአዜብን የድህነት ወሬ የቡና ማጣጣሚያ ነው ያደረገው – ሳይጠማን እየጠጣን ብዙ ቡና ፈጅተንበታል – ጊዜው ሲደርስ ይህንን ኪሣራችንንም ታወራርዳለች፡፡ የዚህች ቀልማዳ ሴት ንግግር በአሣፋሪነቱና አጸያፊነቱ በሺዎች ዓመታት አንዴ እንደሚያጋጥም እጅግ ነውረኛ አነጋገር ሊወሰድ ይችላል፡፡ የርሷ ስህተት እንደግለሰባዊ ስህተት ተቆጥሮ በዝምታ ሊታለፍ ይችላል፡፡ የወያኔው ድርጅት በፍርሀት ይሁን በሌለው ይሉኝታ እርሷን በዝምታ ማለፉ ግን ይቅር የማይባል ታሪካዊ ህፀፅ ነው፡፡ ለነገሩ አሁንም ብዙም አልረፈደምና የሴትዮዋን ተፈጥሮ የምታውቁ ወያኔዎች እባካችሁን አንድ ነገር አድርጉ – ለናንተው ስትሉ፡፡ እኛ ሁሉንም ለምደነዋልና ስለኛ ብላችሁ እንደማትጨነቁ እናውቃለን፡፡ ሀፍረቱ ይበልጡን ለእናንተው ስለሆነ አዜብን ግዴላችሁም ተዋት፡፡
ቁጭ ብዬ በእርጋታ ሳስበው ሕዝብንና የታሪክ ፍርድን ንቆ ይህችን ሴት ባለሥልጣን ማድረግ የኋላ ኋላ ኢሕአዴግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለው ይመስለኛል፡፡ እናም ኢሕአዴግ ለክብሩ ሲል – ክብር ካለው ነው ለዚያውም – አለበለዚያም ውርደቱን ቅጥየለሽ ላለማድረግ ሲል ይህችን ሴት ከማዘጋጃ ቤት ሹምነት የዕጩ መዝገብ ይፋቃት፡፡ እኔ ውርድ ከራስ ብያለሁ፡፡ ሰውን መናቅ ፈጣሪን መናቅ እንደሆነ ለሃይማኖት የለሹ ወያኔ መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ እርግጥ ነው – በአምባገነኖች ዘንድ ማይምንና እንደጤናማ ሰው ማሰብ የማይችልን አጋሰስ መሾም የተለመደ ነው፡፡ ሲበዛ ግን ያንገሸግሻል፡፡ ሕዝብ ስቆ ቢያልፈው የውሻን ደም መና የማያስቀረው ፈጣሪ፣ አይደለም ይህችን በሰው ቋንቋ ከመናገሯ ውጪ ከውሻ ብዙም የማትለየው ሴት ትቅርና ሂትለርንና ሙሶሊንን የመሰሉ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አምባገነኖችን አይቀጡ ቅጣት አከናንቦ በጭቁኖች መሃል አዋርዷቸዋል፡፡
ይህች መናኛ ሴትም ከወያኔ ጋር የምትዋረድበት ዘመን እየመጣ ቢሆንም ማምሻም ዕድሜ ነውና ማሰብ ያልተሳናችሁ በጣት የምትቆጠሩ ወያኔዎች ካላችሁ የዛሬን ማሩን፤ ቀድሜ እንደገለጽኩት ውርደቱ የጋራችን ነው፡፡ ይበልጡን ግን – ልድገምላችሁ – የእናንተው ነው፡፡ ሴትዮዋን መሾማችሁ የግድ ከሆነ ብትፈልጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓት፡፡ ያ ቦታ ከሕዝብ የራቀ በመሆኑ አንገናኝምና እንደፍጥርጥራችሁ፡፡ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ግን ሺዎችን በየቀኑ የሚያስተናግድ የሕዝብ መናኸሪያ በመሆኑ ባለሥልጣናቱ የሕዝብን ቀልብ እንደነገሩም ቢሆን የሚስቡ መሆን አለባቸው፡፡ ይህች ሴት እኮ አርከበ ዕቁባይ ለሕዝብ ጥሩ ሠራ በመባሉና ሕዝብም በተወሰነ ደረጃና በግል አበርክቶው ስለወደደው በዚያ ቀንታበት ኤች አይ ቪ ሲመረመር የሚያሳየውን ቢልቦርድ በተሰቀለ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንዲወገድና ከዕይታ እንዲሠወር አድርጋለች፡፡ የባል ተብዬው የመለስና የሚስት ተብዬዋ የአዜብ የክፋት ደረጃ እንግዲህ እስከዚህ የወረደና ከአንድ ተራ ዜጋ እንኳን የማይጠበቅ ነው – ለቅጣት መምጣታቸውን በበኩሌ አምናለሁ፡፡ ተራ ዜጋ ምቀኛና ቀናተኛ ቢሆን ምንም አይደለም፡፡ የአንድን ሀገር በትረ ሥልጣን የጨበጠ ቁንጮ ያገር መሪና ሚስቱ ግን እንዲህ ያለ በራሱ በመለስ ወራዳ የቋንቋ አጠቃቀም ለመግለጽ እንዲህ ያለ ወራዳና ልክስክስ ጠባይ ሲያሳዩ የሀገርን አጠቃላይ ውድቀት ነው በጉልህ የሚያስረዳን፡፡ ያልዘሩት መቼም አይበቅልም፡፡ የዘራነውን እያጨድን ነን፡፡
ለማንኛውም አዜብን በከንቲባነት መሾም – ምክትልም ሆነች ዋና ለውጥ የለውም – የሚያስከትለው አደጋና ውርደት ታስቦበት በጊዜ አንድ ነገር እንዲደረግ የዜግነት ጥሪየን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡
በሌላም በኩል ይሄ ለይምሰል ያህል በብሔረሰብ ተዋጽዖ አንጻር የሚደረገው ሹመት ይቁም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ማንም አያምንም – ይህን ያረጀ ያፈጀ ሥልት አንቀልባ ውስጥ ያለ ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቀዋልና፡፡ እኔ ለምሳሌ በደመቀ መኮንን መሾም ምክንያት አልተደሰትኩም፡፡ አንደኛውና ትልቁ ነገር እንደውሻ አጥንትና ደም አላነፈንፍም፡፡
በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም የሚኒስትር ካቢኔ ከኮንሶና ከሙርሲ ቢሆን ሃሳቡ አይበላኝም፤ ወያኔንም የጠላሁት በመጥፎ ድርጊቱ እንጂ በተሹዋሚዎች የዘር ሐረግ አይደለም – በጭራሽ፡፡ ሁለተኛ የደመቀ መሾም ስሜትን በማይነካ የቃላት አጠቃቀም ለየዋሃን አማሮች ካልሆነ በስተቀር መሬት ላይ የፈጠጠውን ኢትዮጵያዊ እውነት ለሚረዳ ሰው ‹አማራ ተሾመልኝ!› በሚል የሚያስፈነጥዝ አይደለም፡፡ ራሱን ከጥቃት የማያድን አማራ፣ የራሱ ናቸው የተባሉ ወገኖችን ጥቃትና እንግልት ለማስቆም አንዳችም ተሰሚነት የሌለው በድንና ገልቱ ሰውዬ ተሾመልኝ ብዬ ጮቤ የምረግጥ ሞኝና ተላላ መስዬ ከታየኋቸው – አዝናለሁ – ሞኞቹ እነሱ እንጂ እኔ አይደለሁም፡፡ ደመቀን መሣይ ከረፈፍ ሆዳሞች በሥርዓቱ ውስጥ ወይነው ገብተው ሀገሪቱን ምን ያህል እየጎዱ እንደሆነ ማስታወስም ተገቢ ነው፡፡ በጣም የምወደው ኦባንግ ሜቶ ቅድም ሲናገር እንደሰማሁት ሁልጊዜም እኔ ራሴ እንደምለው ወያኔ ማለት በዘርና በቋንቋ ተወስኖ ወይም ተቀንብቦ የተቀመጠ አለመሆኑንም መረዳት ይገባል፡፡ መነሻውና አስኳል አመራሩ ከትግራይ ይሁን እንጂ ለዚህ የወያኔ ሥርዓት ማበብና ማፍራት ዋና ተባባሪዎቹ ትግሬ ያልሆኑ የተጋቦት ወያኔዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡ ግን ግን “የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ዞረ” እንዲሉ ሆኖብን አንዴ የፈረደበትን የትግራይ ሕዝብ ብዙዎቻችን እንወርድበታለን፡፡ በበኩሌ አሁን እየሆነ ባለው ነገር ሁሉ የእያንዳንዳችን ልብ ሳይሰበር ነገ ይቅርታ እንደምንባባልና አብሮነታችን ካለሣንካ እንደሚቀጥል በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ንዴትና ብስጭት የማይፈጥረው አእምሮኣዊ ምስል ባለመኖሩ ደመናው ሲጠራና እውነት ስታሸንፍ አሁን ችግር የሚመስሉን ብዙ ነገሮች ከላያችን ላይ ተገፍፈው ይጠፋሉ፤ ያለ ነገር ነው – በዚህን መሰሉ ጊዜ የሚያጋጥም ብዙ ነገር አለ፡፡ መምሰልና መሆን ስለሚለያዩ የደፈረሰው ሲጠራና የሰላም አየር በሀገራችን ሰማይ ሲያረብብ የግጭትና የሁከት እርኩሳን መናፍስት ተጠራርገው ይወገዳሉና ስለነገው ከመጠን በላይ አንጨነቅ፡፡ የወቅት ንፋስ የሚፈጥራቸው ብዙ አላፊ ክስተቶች አሉ – በኛ ብቻ ሳይሆን በየሀገሩ፡፡ ሁሉም እንደሚያልፍ መረዳትና ለዚያ በርትቶ መታገል እንደሚገባ ተረድተን በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ተባብረን ይህን የለያየንን ቆሻሻ ሥርዓት ለማስወገድ አብረን መታል ብቻ ነው የሚያዋታን፡፡ አለጥርጥር ሥርዓቱ ይወድቃል – ችግሩ በጣም ብዙ ምናልባትም ከእስካሁኑ የከፋ ቨስጠሊታ የታሪክ ጠባሳ ሳይተው የሚወድቀው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም ምክክር፣ ትብብርና ስምምነት ያስፈልጋል፡፡ እውነት ምን ጊዜም ከእውነት መንገድ ለማትወጣው ነገር በመለያየት አዲስ ግን በወያኔያዊ ትልምና ዐቅድ የተለወሰና በፀረ-ኢትዮጵያነት የተመረዘ ታሪክ ለማስመዝገብ የምንቻኮል ሰዎች ካለን ቆም ብለን እንድናስብ በእገረ መንገድ ጠቆም ባደርግ ደስ ይለኛል – ከወያኔ ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ የሕዝቡ ችግረና ፍላጎት ይግባን፡፡ ‹ሕዝቡ ምን ይላል? ምንስ ይፈልጋል ?› ብለን እንራመድ እንጂ በየግል ፍላጎታችን የተጓዝን ተሳስተን አናሳስት፤ ታሪክም ይቅር አይለንም፡፡ መደማመጥ ለመልካም የጋራ ስኬት ጠቃሚ መሆኑን እየዘነጋን ለየህልማችን እውን መሆን በተናጠል ስንሮጥ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ፡፡
ማንዴላ እጅ ሆነዋል፡፡ ምናልባትም ይህች ጽሑፍ በአንዱ ድረ ገፅ ከመለጠፏ በፊት አንዳች ነገር ሊከሰት ይችላል፤ ወይም በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ዜና ዕረፍታቸውን እንሰማ ይሆናል – ለነገሩ ‹እግረ ቀጭን እያለ እግረ ወፍራም ይሞታል› እንዲሉ ከማንዴላ በፊት ለምሳሌ እኔ ራሴ ልቀድም እችላለሁ፡፡ የወደፊቱን ያለማወቃችን ምሥጢር ነው ሕይወትን ትርጉም ያላት እንድትሆን ያደረጋት፡፡ ተስፋ ባትኖር ሁሉም በቁም እንደሞተ ያህል ነው – ጧት ከቤቱ በሰላም የወጣ ሰው ማታ ሬሣው ወደቤቱ ሊመለስ እንደሚችል ቢያውቅ ማንም የመኖር ጉጉት አያድርበትም – የእግዜሩም እንበለው የተፈጥሮ ጥበብ መገለጫም ይሄው ነው – ስለወደፊቱ አለማወቅ፡፡ በዚህም አለ በዚያ በማንዴላ ሁኔታ ዓለም በጭንቀት ላይ የምትገኝ ትመስላለች፡፡ ጭንቀቷ ግን ለማንዴላ ለራሱ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምሥጢሩ ወዲህ ነው፡፡(በነገራችን ላይ ‹ድኅረ ገፅ› የምንል ሰዎች ‹ድረ ገፅ› ማለትን ብንለምድ ደስ ይለኛል፡፡ ‹ድኅረ› ማለት ‹በኋላ›(post) ማለት እንደሆነና ‹ድረ› የሚለው ቃል ግን ‹ድር› ከሚለው የአማርኛ ቃል ተወስዶና ከ‹ገፅ› ጋር ተጋምዶ ‹website› የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል እንዲተካ መደረጉን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ ዕውቀት አይናቅምና በተለይ ድረ-ገፆች እባካችሁን ይቺን ነጥብ አትናቋት፡፡ መናደድ ሲያምረኝ ከምናደድባቸው ነገሮች አንደኛዋ ይህች ነች፡፡ )
የዓለም ሕዝብ አንድ አባሉ ከ94 ዓመታት በላይ በመሬት ላይ እየኖረ እንዲሰቃይ የሚፈልግ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሰዎች እስከዘላለሙ እንዲኖሩ የሚፈለግበት ምኞት – ከልብ ስለመሆኑ ማወቅ ቢያስቸግርም – በብዛት የሚታየው በኛይቷ ሀገር በኢትዮጵያ ነው፡፡ የመቶ ሃያ ዓመት ሽማግሌ ሲሞት ፊት የሚነጨው በሌላ ሀገር አይደለም – በኢትዮጵያ ነው – ሊያውም ይበልጡን በአማራው አካባቢ፡፡ ባህላችን ከኛ ወቅታዊ ግንዛቤ በልጦ የሚገኝበትን ሁኔታዎች አንዳንዴ እንታዘባለን፤ ከአንዳንዴም በላይ እንዲያውም፡፡ ለዚህም ነው በዛሬዋ ውሎየ እንኳ ሁለት ተቃራኒ ጸሎቶችን የታዘብኩት – አንድ ከኢትዮጵያውያን፣ አንድ ከደቡብ አፍሪካውያን፡፡ መቼም እኛ ከነሱ በልጠን እግዜሩ ለማንዴላ የማቱሳላን ዕድሜ እንዲሰጥልን ልንጸልይ እንደማንችል ቢያንስ ኅሊናችን ያውቃል – እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፡፡ ይህ ምን ያሳያል? ፊት ለፊት የሚታየው ባህላችን ለሰው መጥፎ የማይመኝ መሆኑንና በብዙ ነገር ከሌሎች የምንለይ ሕዝብ መሆናችንን ነው ለዓለም እያስመሰከርን የምንገኘው – ምነው እውነተኛና በምንም ዓይነት ማዕበል የማይናወጥ አቋም ባደረገልን!
ማንዴላ እንዳይሞት የምንፈልግበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ዓለማችን በሰው እጦት ምች ስለተመታች ጥሩ ሰው ስናገኝ እንደብርቅ እናየዋለን፤ ሞት እንዳይነጥቀንም እንሳሳለታለን፤ እስከወዲያውም አብሮን እንዲኖር እንመኛለን – ትውልድ ቢያልፍም ከቀጣዩ ትውልድ ጋር፡፡ ብዙ ደጋግ ሰዎች ቢኖሩን ኖሮ የዓለም ሕዝቦች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት ያለቪዛና የትራንስፖርት ወጪ ደቡብ አፍሪካ ሄዶ ፕሪቶሪያ ሆስፒታል ዙሪያ ባልከተመ ነበር፡፡ ጥሩ ሰው ብርቅ በሆነበት ዘመን መፈጠር እንዴት መታደል ነው! መለስም እንዲያ የተንጫጫንለት እኮ የርሱን አእምሮ ይዞ የሚወለድ – እንደአዜብ አነጋገር በዓለም የአንጎል ገበያ ተመራጭ ጭንቅላት ይዞ በሺዎች ዓመታት አንዴ የሚወለድ ዐዋቂና ታዋቂ በመሆኑ ነው፡፡ እኔ ለመለስ የነጨሁት ፊት እስካሁን አላገገመም፤ የምለብሰውም ማቅ ከላየ ላይ አልወረደም፡፡ እርግጥ ነው – ይበልጡን ለክፋት ቢጠቀምበትም መለስን በዕውቀቱ መቀጣጠብ አይቻልም፤ ሰይጣን ለዘዴው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባል መለስም የነበረው ሁለገብ ዕውቀትና ብልጣብልጥ ተፈጥሮ ከብዙዎች መሪዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም፡፡ የኔነህ ሳይለኝ ቢሞትም የኔነው ማለት ወጪ የለውምና ሳልወድ በግዴ የኔነው ብዬ ብቀበለው ከሚኮሰኩሰው ኢትዮጵያዊነቱ አንጻር ብቻም ሳይሆን ከአጠቃላይ ስብዕናው የሚፈልቁ ብዙ የሚደነቁ ሰብኣዊ ተሰጥዖዎች እንደነበሩት አልክድም – አጭበርባሪው፣ አስመሳዩና መልቲው መለስ ዜናዊ፡፡ ግን ተሰጥዖዎቹን ለተንኮልና እንደሥራየ ቤት ነገርን በመጠምዘዝ ሕይወቱን ጨርሶ ዕውቀቱን ሳይጠቀምበት ሞተና ዐርፎ ዐሣረፈን፡፡ በሚስቱ ሲንገበገብ የነበረ አንድ ፈላስፋ መቃብሯ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍሯል አሉ፡- My wife lies here; let her rest in peace, so do I.
አትታዘቡኝ፡፡ በበኩሌ ማንዴላ እንዲያርፍ እጸልያለሁ – በሰላም ማረፍ ለኔ አይገባኝም – ሰው እየሞተ ምን ሰላም አለና፤ ማንዴላ በ‹ሰላም› እንዲያርፍም በ‹ሰላም› እንዲድንም ከጸሎት ጀምሮ ሁሉም ነገር ቢደረግም እስከዚች ሰዓት ድረስ አልዳነም ወይም አላረፈም፤ የዚህን ደብዳቤ የመጀመሪያ ረቂቅ ስጽፍ – አሁን ሰዓቱ ከሌሊቱ ስምንት ገደማ መሆኑን ልብ ይሏል – የማንዴላ የጤና ሁኔታ እንደሰሞኑ ሁሉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኝ፤ ከአሳሳቢነቱም የተነሣ ፕሬዚደንት ጃኮብ ዙማ ሊያደርጉት የነበረውን የሀገር ውጪ ጉዞ እስከመሠረዝ ደርሰዋል፡፡ ዕንቁ ልጃችን – ብርቅዬ የአፍሪካ ብቻ ሣይሆን የዓለማችን ልጅ ማዲባ ሲያርፍ ደግሞ ነፍሱ በማኅተመ ጋንዲና በእማሆይ ተሬዛ፣ በአብርሃምና በያዕቆብ ነፍሳት አጠገብ እንድትቀመጥ የቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆን ዘንድ የሁላችንንም ጸሎት እኔም በበኩሌ እጸልያለሁ፡፡ ይቅርታችሁን – ቀደም ብዬ ማዲባን በአንቱታ የጠራሁት ብዙ ሰው ያለው እኔስ ለምን ይቅርብኝ ብዬ ከሰው ለመመሳሰል ነው፤ ስጨርስ በአንተ የጠራሁት የሕዝብ ሰው አንቱ እንደማይባል ስለምረዳ የአንጀቴን ነው – የሕዝብ ሰው ማለት ደግሞ የሚፈቀርና የሚወደድ ማለት ነው፡፡ አብንና ወልድን ማን አንቱ ይላል? ቅድስት ማርያምንስ? ኧረ መለስ ዜናዊንስ ማን በአንቱታ ጠርቶት ያውቃል? የሕዝብ ሰው ማለት እንዲህ ነው – ቺንዋ አቼቤ A man of the people የሚል ርዕስ ለአንድኛው መጽሐፉ የሰጠው እኮ ለነማንዴላ ዓይነቱ መላ ሕይወታቸውን ለራሳቸው ጥቅም መስዋዕት ላደረጉ ሣይሆን ለነመለስ ዜናዊ ዓይነቱ ለቤት ቀጋዎች ለውጭ አልጋዎች ነው፡፡ ዓለም ግን ምን ዓይነት የዕንቆቅልሽ ምድር ናት ጎበዝ?!
ውድ ማንዴላ ሆይ! ሁልጊዜ ከኅሊናችን አትጠፋም – በአካል ብትለየን በመንፈስ ምንጊዜም አብረኸን አለህ – ከአሁኑም ከወደፊቱም ትውልዶች ጋር፤ ፈጣሪ አንተን እንደወሰደ በምትክህ ለዓለም ሰላም የሚተጉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን አሳቢ ዜጎችን እንዲልክልን ስትሄድ አሳስብልን፡፡ አፈሩን ገለባ ያድርግልህ፡፡ የሁለት ወር ሀገርህን ኢትዮጵያንም በፈጣሪ ፊት አስባት፡፡ ስቃይና ጣር ሳይበዛብህ በቶሎ ሂድልን፡፡ በዚህች አንተን ሳይቀር ለ27 ዓመታት በእሥር ባንላታች የእርጉማን ምድር ከአሁን በኋላ ለሴከንድም መቆየቱ መከራና ስቃይ መጨመር እንጂ ጤናውም ጤና አይሆንህም፡፡ ሰዎች ስንባል ራስ ወዳዶች ነን፤ ‹ቆይልን› የምንልህ በአንተ ስቃይ የኛን ‹ኢጎ› ለማስደሰት እንጂ አንተ አልጋ ላይ ውለህ የመከራ ቀናትንና ሌሊቶችን በእዬዬ ማሳለፍህ፣ በድጋፍ ሰጪ የሕክምና ቴክኖሎጂ እየታገዝክ ካለ እንቅልፍ መቆየትህ አንዳችም ነገር አይፈይድልንም – ለአንተም ለእኛም፡፡ በሀገሬ ሰው ይሙት ተብሎ እንደማይጸለይ አውቃለሁ ማዲባየ – ግን ‹ይህን አለ› ተብዬ ኩነኔ መግባቱን እመርጣለሁ እንጂ ስትሰቃይ ለማየት ከእንግዲህ ቆይልን አልልህም፡፡ በቃ፡፡ በሰላም ሂድልን፡፡ ስትመጣ እንደምትሄድ ይታወቅ ነበር፡፡ እኛም በሕይወት አለን የምንል ወገኖችህም ወረፋችንን ጠብቀን እንከተልሃለን፡፡ ዱሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው መባሉም ለዚህ ነው፡፡ ይብላኝ ለኛ ግና፡፡ በጅቦችና በእሪያዎች መካከል እንደተጣልን ተለይተኸን ለምትሄደው ለኛ ይብላኝ እንጂ አንተማ ከፋም ለማም 95 የሚጠጉ ክረምቶችን ለሕዝብህ ስትል ከአፓርታይድና ከመጥፎ ግላዊ ገጠመኞችህ ጋር ስትፋለም ኖረህ አሁን በመጨረሻው ሥጋዊ ሽንፈትህ ደረጃ ላይ ደርሰሃል፡፡ በዚያች በደቡብ አፍሪካዊቷ አዜብ እንኳን ያየኸውን አበሳ ማን ይረሳዋል? ብቻ ሆድ ይፍጀው ማዲባየ፡፡ እዚያው እስክንገናኝ ደህና ሰንብትልኝ፡፡
ሰላም ለኢትዮጵያና ሕዝቧ፤ በዚህ ዓለም አቀፍ ሀዘን መጽናናት ለሚያስፈልገው ሁሉ ፈጣሪ እንዲያጽናናው እመኝለታለሁ፡፡

Wednesday, June 26, 2013

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው

ኢየሩሳሌም አርአያ
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅትBereket Simon is the Ethiopian Communications Minister የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
http://ecadforum.com/Amharic/archives/8672/

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዎ

• በሚኒስትር ማዕረግ ሦስት ምክትል ከንቲባዎች ይሾማሉ እየተባለ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይነት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ በሚሾም አንድ ከንቲባና በሚኒስትር ማዕረግ በሚሾሙ ሦስት ምክትል ከንቲባዎች እንደሚመራ ምንጮች ጠቆሙ፡፡
ምንጮች እንደሚሉት፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ለከተማው ከንቲባ ሆነው የሚሾሙት አቶ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡ አቶ ድሪባ በአሁኑ ወቅት የትራንስፖርት ሚኒስትር ሲሆኑ፣ መሰንበቻውን ከወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየታዩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በሚኒስትር ማዕረግ የከተማው ቀጣዮቹ ምክትል ከንቲባዎች የሚሆኑት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩርያ ኃይሌ፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበውና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ናቸው ሲሉም ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
ነገር ግን ወ/ሮ አዜብ በየትኛውም ቦታ መሾም እንደማይፈልጉ እየገለጹ መሆናቸውን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ሪፖርተር በዚህ የመዋቅር ለውጥና ሹመት ጉዳይ ማረጋገጫ ለማግኘት ለአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢያቀርብም፣ እየተካሄደ ያለውን ሥራ በዝርዝር መግለጽ ባለመፈለጉ አልተሳካም፡፡
ምንጮች እንደሚያብራሩት፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ ቢሮዎችን በኃላፊነት የሚመሩት ዕጩ ተሿሚዎች በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ እንደሚሾሙ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር የሚፈቅደው አንድ ምክትል ከንቲባ በመሆኑ፣ ከአንዱ ዕጩ ተሿሚ በስተቀር ሁለቱ ተሿሚዎች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ እንደሚሾሙ አመልክተዋል፡፡
ምንጮች እንደሚገልጹት፣ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ይህንን ያደረገበት ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የተጀመሩና በቀጣይ የሚጀመሩ የልማት ሥራዎች ሰፊ በመሆናቸው፣ ይህንን የሚሸከም የአስተዳደር የሥልጣን እርከን ማደራጀት ያስፈልጋል በሚል ነው፡፡
የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጀማል ረዲ መዋቅሩንና አሿሿሙን ባይገልጹም፣ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አዲስ አበባን የሚያስተዳድረው የሰው ኃይል በከፍተኛ ደረጃ እየተዘጋጀ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ በማደግ ላይ ያለች ከተማ ብትሆንም፣ በከተማዋ ውስጥ አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች በርካታ ናቸው፡፡ ኅብረተሰቡ አምርሮ ከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች መካከል የመኖርያ ቤት እጥረት፣ የኑሮ ውድነት፣ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር፣ የትራንስፖርት እጥረትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ አስተዳደር እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ተግባራትን ቢያከናውንም አዲስ አበባውያን ሊረኩ አልቻሉም፡፡ ኢሕአዴግ የኅብረተሰቡን ችግሮች ለመቅረፍ መወሰኑን በሚያመለክት ደረጃ ለአዲስ አበባ ከተማ ትኩረት እየሰጠ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት ይናገራል፡፡
ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን ከፌደራል ወደ አዲስ አበባ በሚያዝያ ወር በተካሄደው ምርጫ አማካይነት ቢያዛውርም፣ በእነዚህ ሹማምንት ምክንያት የተፈጠረውን የፌዴራል መንግሥት የአመራር ክፍተት የመሙላት ሌላ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል፡፡
ethiopian reporter

ስለ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ መረጃ

 UKእና በመላው ዓለም በስደት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችና መላው ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያውያን።

ከሃገሩ ርቆ በስደት ዓላም የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ በፈጣሪው ተራዳዒነት ጥሮና ግሮ ላለፉት 40 ዓመታት ያቆማትና ያሳደጋት ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያስተዳድሩና መንፈሳዊ አባት እንዲሆኑት መርጦ የሾማቸው አባ ግርማ ከበደ በገንዘቡም ሆነ በማንኛቸውም ነገር ላይ አዛዥና ፈራጭ ቆራጩ እኔ ካልሆንኩ በማለት ሆነ ብለው ያስነሱት ውዝግብ አልሰምር ሲላቸው እነሆ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗን ከነ ሃብትና ንብረቷ ከስደተኛው ህብረተሰብ ወስጄ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ትሆናለች በሚል አስባብ በአውሮፓ ውስጥ በስደተኛው የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናትን በቀጥታ ለመቆጣጠር ሲባል ለተቋቋመው ሃገረ ስብከት አስረክቤ ጥቅሜን አስረክባለሁ በማለት ተከታዮቻቸውን ይዘው በሚያደርጉት ትግል ትንቅንቁ ቀጥሎ ይገኛል።
ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሃገር፤ በሕዝብና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚከተለውን የዘረኛ ፖሊሲና አሠራር ባለመቀበል የዚህም ዘረኛ አገዛዝ ተዋናኝ ለነበሩት ለአባ ጳውሎስ ሳትበገር ለ22 ዓመታት የመንግሥትም ሆነ የፓለቲካ ተጽዕኖ ሳይኖርባት  በነፃነት ቆማ የኖረችና ነጻ በመሆኗም ለከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃች በአውሮፓ አንጋፋዋ ቤተ ክርስቲያን ነች።
ይህንን በመሰለ አኩሪ የነጻነት ታሪክ የምትታወቀውን ቤተክርስቲያን ነው ዛሬ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው ለንዋይና ለሥልጣን ሲሉ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ላቋቋመው ሃገረ ስብከት ለማስረከብ የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ የሚገኙት።
ይህ የእነ አባ ግርማ የክህደት ሥራ ተግባራዊ ሆነ ማለት ደግሞ በስደት ላይ የሚገኘው ሕዝብ ሳይተርፈው ከራሱና ከልጆቹ አፍ በመነጠል ከ1.7 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ገንዘብ በማውጣት ጥሮና ግሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምትተላለፍልኝ የሃይማኖቴና የኢትዮጵያውነቴ ቅርስ ትሆነኛለች ብሎ ህንፃ ገዝቶ ያቆማትን ቤተ ክርስቲያን ሃገር አይል ኤምባሲ ከመሸጥ ወደ ኋላ የማይለው ወያኔ ተረክቦ ህዝበ ክርስቲያኑን በመበታተን ቢያሻው ሊሸጣት ካልሆነም ደግሞ የራሱ ሰዎች መገልገያ ብቻ እንዲያደርጋት እድሉን አገኘ ማለት ነው።
በሌላ በኩል ቤተ ክርስቲያኗን የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ተሿሚዎች ተቆጣጠሯት ማለት ደግሞ ነፃነትና ፍትሕ በሰፈነበት ሃገር  የወያኔ አገዛዝ ልክ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚካሄደው ሁሉ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት የሆኑ ስደተኞችን ከPersonal Data ጀምሮ ሥራቸው፤ ግንኙነታቸው፤ የፓለቲካ አመለካከታቸውና በአጠቃላይ እንቅስቃሴአቸውን ሁሉ በአገዛዙ የስለላ መነጽር ውስጥ በስገባት መብትና  ነጻነታቸውን ሁሉ መቆጣጠር ተቻለው ማለት ነው ።
ከዚሁ ጋርም የወያኔ አገዛዝ ሹመኞች አንድ እግራቸው ቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ገባ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ገቢ ያላቸውንና ቁልፍ ሚና አላቸው የሚባሉትን አብያተ ክርስቲያናት በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወያኔ በሚጠቀመው ስልት መሠረት የአገዛዙን የጎሳ አባላትና ደጋፊዎች በብዛት የቤተ ክርስቲያኗ አባል በማድረግና under cover ካህናትን አስርጎ በማስገባት በቤተክርስቲያኗ የሥራና የኃላፊነት ዘርፉ ሁሉ የራሱን ሰዎች በመሰግሰግ የቤተ ክርስቲያኗን ሃብትና ንዋይ በቁጥጥር ሥር ማዋልና አባላቷ የወያኔ አገዛዝ የሚሰራውንና የሚለውን ከመደገፍና ከመቀበል ሌላ በነፃነት ማሰብም ሆነ በነፃነት መወሰን የሚባል ነገር እንዳይኖራቸው በማድረግ ለወያኔ ሹመኞች ሰጥ ረጥ ብለው የሚገዙበትን ሁኔታ ማመቻቸ ቻሉ ማለት ነው።
ይህም ብቻ አይደለም ሌላው ቤተ ክርስቲያኗ በሃገር ስብከቱ ሥር እስከ ሆነች ድረሥ ከምታገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ለሃገረ ስብከቱ ፈሰስ በሚልና በሌላ ሰበብ አስባብ በተ ክርስቲያኗን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ምንጭ አድርጎ ለመጠቀም ነው። ይህ ማለት ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ቤተ ክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ በደልና ግፍ ሁሉ በፋይናንስ የምታጠናክር ተቋም ሆነች ማለት ነው።
አባ ግርማ ከበደ ትላንትና ቤተ ክርስቲያኗ በአባ ጳውሎስ ላይ እና በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ላይ የወሰደችውን አቋም መደገፍ ብቻ ሳይሆን ከዛም አልፈው የወያኔን አገዛዝ በሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ በመገኘትና የተቃዋሚ ፓለቲካ ድርጅቶችንና የኮሚኒቲ አመራሮችን በመቅረብ ሃገርና ሕዝብን የሚወዱና የወያኔን አገዛዝ የሚቃወሙ እውነተኛ መነኩሴ ተደርገው ለመታየት ይሞክሩ ነበር።
እሳቸው ግን ይህን ሁሉ ያደርጉ የነበረው ሥልጣናቸውን ለማደላደል እንዲችሉ የስደተኛውን ስነ ልቦና ለመግዛት እንጂ የእውነት ስላልነበር በአሁኑ ወቅት ስደተኛው ህብረተሰብ ከቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት የዘለለ የጵጵስናም ሆነ የሃገረ ስብከት ሹመት ስለማይሰጣቸው አምኖና አክብሮ፤ አቅፎና ደግፎ ያኖራቸውን ስደተኛ ህብረተሰብ ጀርባችውን በመስጠት 180 ዲግሪ ከዞሩ ውለው አድረዋል። በዚህም መሠረት ከጥቂት ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ለወያኔ ኤምባሲና ሃገረ ስብከት በማደር ቤተ ክርስቲያኗን ከስደተኛው መዳፍ ፈልቅቀው ለማስረከብ ከመማጸን አልፈው ከኢትዮጵያ ድረስ ጳጳሳትን በማስመጣት፤ የሳቸው ደጋፊ ከሆኑ ጥቂቶች በስተቀር በሺህ የሚቁጠሩት በገንዘብና ጉልበታቸው የቤተ ክርስቲያኑን ህንፃ ገዝተው ያቆሙ የቤተ ክርስቲያኗን አባላት በመካድ እነሱ በሌሉበትና ባልተጠየቁበት ሁኔታ የሌሎች ቤተ ክርስቲያናት አባላትን በመሰብሰብ በጳጳሳቱ ፊት ቤተ ክርስቲያኗ ሙሉ በሙሉ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በጎሳ መርጦ ባቋቋመው ሃገረ ስብከት ሥር ነች በማለት ቤተ ክርስቲያኗን በጠራራ ፀሐይ ሸጠዋል።
አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው በሺህ የሚቆጠረውን የቤተ ክርስቲያኗን አባላት እንደሌለ ቆጥረው ይህንን የመሰለ የክህደት ተግባር ከፈጸሙ በኋላ፡
1) በ26/05/2013 በዕለተ እሑድ ቤተ ክርስቲያኑ ተዘግቶበት ለራሱም ሆነ ለልጆቹ መጸለያና ማቁረቢያ አጥቶ፤ ወንጌልን ተጠምቶ በከፍተኛ ሃዘንና ትካዜ ውስጥ የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያኑን ግንብ ተጠግቶ የዕለት ጸሎቱን በሚያደርስበት ወቅት አባ ግርማ ከበደ ግን ቤተ ክርስቲያኑን የዘጉበትና ሊከፍቱም የሚችሉበት የቤተ ክርስቲያኑ መዝጊያ ቁልፍ በኪሳቸው እንደያዙ፤ ከዚህም ሌላ የስላሴን ቤተ ክርስቲያን አማራጭ አድርገው ሲያገለግሉና ሲገለገሉ እንዳልሰነበቱ ልክ እንደ ሕዝቡ ተበዳይ መስለው ለመታየት እቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመግባት በሚሞክሩበት ወቅት በድርጊታቸው የተቆጣው ሕዝብ የቤተ ክርስቲያኑን ቁልፍ ስጡን በማለት በሩን አላስገባም በማለቱ፤ በተነሳው ሁከት አባ ግርማ ከበደ እግዚአብብሄርን ሳይፈሩና ሰውንም ሳያፍሩ ቤተ ክርስቲያኗ የግል ንብረቴ ነች (This is my Property) ባማለት ለፖለስ አቤቱታ በማቅረብ የባለቤትነት መብታቸው ተጠብቆላቸው ፓሊስ አጅቦ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ግቢ እንዲያስገባቸው ጠየቁ። (ይህን ያሉበት ምክንያት ሕዝቡ የገዛውን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና የቪካሬጅ ህንፃ አደራ ጠባቂ (Holding Trustee) ሆነው እንዲጠብቁ አምኖ አደራ ከጣለባቸው ሁለት ካህናትና ሁለት ምእመናን መካከል አንዱ በመሆናቸው ነው) ሕዝብ ከሌሎች ሦስት ሰዎች ጋር ሆነህ ንብረቴን ጠብቅልኝ ብሎ የሰጠውን አደራ እዛው አደራ የሰጠው ሕዝብ ፊት ቆሞ ይህ የግል ንብረቴ ነው በማለት አይን ያወጣ ክህደት የሚፈጽምን ሰው ከቶ ማን ይሉታል? እግዚአብሔርን ለማገልገል ለዚህ ዓለም ሞቻለሁ ያለ መነኩሴ ወይስ አይን ያወጣ፤ ተራ ሌባ?
2) በ02/06/2013 በዕለተ እሑድ እንደተለመደው አባ ግርማ ከበደ ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የመገልገልና የማገልገል አማራጩ እያላቸው አማራጭ አጥተው በሃዘንና በቁጭት የቤተ ክርስቲያናቸውን ግንብ ተጠግተው ጸሎታቸውን የሚያደርሱትን የቤተ ክርስቲያኗን አባላት ለመምሰል በሚሞክሩበት ወቅት ከሕዝቡ በተነሳው ቁጣ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ መግባት ያልቻሉ ሲሆን አባ ግርማ ከበደ ግን የሚፈልጉት በእሳቸው ምክንያት በሕዝቡ መካከል ጸብና እረብሻ ተነስቶ በሕዝብ መካከል ከፍተኛ መጎዳዳት እንዲደርስ ቢሆንም ሕዝቡ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር በመሆን ሁከቱ እንዳይስፋፋና ጉዳት እንዳይከሰት በማድረግ አባ ግርማ ከበደን ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሳይገቡ ከውጪ እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።
3) በ09/06/2013 በዕለተ እሑድ የአባ ግርማ ከበደ ደጋፊ የሆኑ የሰንበት ት/ቤተ ወጣቶች የነበሩና አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኗ አባላትም ሆኑ ያልሆኑ ጭምር ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ሲገቡ አንዳችም ነገር ሳይፈጠር ከቆየ በኋላ ሕዝበ ክርስቲያኑ የዕለት ጸሎቱን ጨርሶ ባለበት ወቅት አባ ግርማ ከበደ የፓሊስ ኃይልን በማስጠራት መግቢያ በሩ በፓሊስ መጠበቁን ካረጋገጡ በኋላ ረፋዱ ላይ ከወደ ደቡብ በኩል ብቅ እንዳሉ ሰው ሁሉ ዓይኑን ወደ እሳቸው ሲወረውር ይባስ ብለው መሰቀል መያዝ ባለበት እጃቸው የቪዲዮ ምስል መቅረጫ ሞባይል ፍታቸው ላይ ደቅነው በመያዝ ግራና ቀኝ በትዕቢት እያዘዋወሩ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለውን ምእመን በቪዲዮ ሲቀርጹ በሳቸው ምክንያትና በሳቸው አማካኝነት ቤተ ክርስቲያኑ ተዘግቶበት በጠዋት ቁር በቤተ ክርስቲያን አጥር ጥግ ጥግ ተኮራምቶ የቆመውን ሕዝበ ክርስቲያ ሃዘንና እሮሮ እግዚአብሔር አይቶ ከሰማይ ቁጣ ያወረደ በሚመስል ሁኔታ ከየት እንደሚዘንብ የማይታወቅ ያልበሰለ እንቁላል መዓት በአባ ግርማ አናት ላይ መፍረጥ ጀመረ።
London Ethiopian Orthodox church controversy
አባ ግርማ ከበደ የምስል ቀረጻቸው በዚህ የእንቁላል አደጋ ከተቋረጠባቸው በኋላ በር ላይ የነበሩትን የጸጥታ አስከባሪዎች መከታ አድርገው በጉልበት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ካልገባሁ በማለት ትግልና ግብ ግብ በገጠሙበት ወቅት ራሳቸው ላይ ያለው ቆብ በእንቁላሉ ተሙለጭልጮ ወልቆ ሊወድቅባቸው ችሏል። ይህ በተፈጠረበት ወቅት አባ ግርማ ይበልጥ በመበሳጨታቸው ሊሆን ይችላል ሰውን ለመማታት ሲወራጩ በአካባቢያቸው ሆኖ ሁኔታውን በቪድዮ ይቀርጽ የነበረን ጋዜጠኛ በቅርብ አግኝተው እሱን ለመደባደብ እጃቸውን ሲሰነዝሩ በፓሊስ ገላጋይነት ቪዲዎ ቀራጩ ከመመታት ሊተርፍ ችሏል።
አባ ግርማ ከበደ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉበት ምክንያት እንደምንም ብለው ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት እውስጥ በሚገኘው የእሳቸው ደጋፊና ተቃዋሚ በማለት የተፈረጀው አንድ ሕዝብ መካከል ጸብ እንዲነሳና ሕዝቡን እርስ በእርሱ በማጎዳዳት ጸቡ ጥላቻውና በደሉ ሁሉ በዝቡ መካከል ሆኖላቸው ሕዝቡ ሲፋጅ እሳቸው ከጎን ቆመው ለማየትና ችግሩ የእሳቸው እንዳልሆነ አድርገው ለማሳየት ነበር።
ሆኖም ግን ውርደቱ ሁሉ በሳቸው ላይ እንጂ በሕዝብ መካከል አልነበረምና ዕቅዳቸው ባለመሳካቱ የተበሳጩት አባ ግርማ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ካልገባሁ የሚለው ትንቅንቃቸውን ማቆም ስላልቻሉ በመጨረሻ በጸጥታ ኃይሎቹ አማካኝነት ከአካባቢው እንዲርቁ ተደርገው በሕዝቡ መካከል እንዲከሰት ፈልገውት የነበረው ጸብና መጎዳዳት ሳይከሰት ቀርቷል።
4) በሦስቱ ተከታታይ ሳምንታት የሕዝቡ ተቃውሞው እሳቸው እንደተመኙት ክራሳቸው አልፎ ሕዝብን ከሕዝብ ወደ ማጎዳዳት አልሸጋገር ያላቸው አባ ግርማ ከበደ በ16/06/2013 በዕለተ እሑድ ከጠዋቱ 0730 ሰዓት ጀምር በቁጥር ወደ 20 የሚጠጉ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ያልሆኑና በቤተ ክርስቲያንም አካባቢ ታይተው የማይታወቁ ወጣቶችን እቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማሰማራት የፀብና የአምባ ጓሮ አሰላለፍ እንዲይዙ አስደረጉ። 
ቤተ ክርስቲያኗን ከስደተኛው ሕዝብ እጅ ወስዶ ለዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሹመኞች ለማስረከብ የሚደረገውን ጥረት ለማሳካትና የአባ ግርማን ሃጢአትና በደል ሽፋንና ከለላ ለመሥጠት የተሰማሩት ወጣቶች እነዚህ ነበሩ።
UK, London Ethiopian Orthodox Church
ቀጥሎም የቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ ጸጥታ ያሰጋቸው የፓሊስ ኃይሎች ወደ ቤተ ክርስቲያኗ አካባቢ እንደደረሱ አባ ግርማ ከበደ በቤተ ክርስቲያኑ አጥር መግቢያ ግራና ቀኝ ባሰለፏቸው ወጣቶች ተከልለው ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ሲገቡ ሕዝበ ከርስቲያኑ በሰለጠነ መንገድ ለሥራቸው የሚመጥን የተቃሞ ድምጽ ካሰማ በኋላ በዚህ ዕለትም አባ ግርማ የሚመኙት በሕዝብና በሕዝብ መካከል ምንም ግጭትና አንባጓሮ ሳይነሳ ነገሩ በሰላም ሊያልፍ ቻለ።
በዚህ ዕለት ሕዝበ ክርስቲያኑ የታዘበው ነገር ቢኖር ከአሁን በፊት አባ ግርማ ከበደ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በመቀስቀስና በማደራጀት በ10/02/2013 በዕለተ እሑድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወጣቶቹ አባ ግርማን አይደግፉም ያሏቸውን አባትና አያቶቻቸው የሚሆኑትን አዛውንቶችን ሳይቀር እጅግ የሚያጸይፍ ስድብ እንዲሰድቧቸውና እንዲያዋርዷቸው በማስደረግ ይህ ድርጊታቸውም በቪዲዮ ተቀርጾ በዩ ትዩብ ዓለም እንዲያየው ሆነ።
ነገሩ ከተፈጸመ በኋላም ወጣቶቹ ንሰሃ ገብተው ሕዝቡን ይቅርታ በመጠየቅ ጉዳዩ መክሰም ሲችል የወጣቶቹን ከሕዝብ ጋር መጋጨት የኃይል ማጠናከሪያቸው አድርገው የሚጠቀሙበት አባ ግርማ ከበደ ቅራኔው የባሰ ሰፍቶ ሄዶ ቤተ ክርስቲያኗ በሁከትና በብጥብጥ ዓለም የሚያውቃት አስደረጓት።
አሁንም እንደገና አባ ግርማ ከበደ ከወያኔ የስለላና የደህንነት አካል ጋር ቁርኝት በመፍጠር የቤተ ክርስቲያኑን ችግርም ሆነ የሃገሪቱን Criminal Law ጠንቅቀው ያውቃሉ ሊባሉ የማይችሉ፤ በቤተ ክርስቲያኗ እና በአባላቷ ዘንድ ጨርሶ የማይታወቁ እንግዳ ሰዎችን ሆነ ብለው በማሰማራት በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ውስጥ ብጥብጥና ረብሻ ተነስቶ ሕዝብ እርስ በእርሱ የሚጎዳዳበት ሁኔታ ሊያመቻቹ ችለዋል።
የእነዚህ በቁጥር ከ20 የማይበልጡ ወጣቶች ትክክለኛ ማንነትም ሆነ በምን ምክንያትና ለምን ዓላማ በዛን ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ እንደመጡ በሚመለከተው አካል ክትትልና ጥናት እየተደረገበት ሲሆን አባ ግርማና ደጋፊዎቻቸው ግን ራሳቸው መሸፈንና መከለል ያቃታቸውን አሳፋሪ የክህደት ተግባራቸውን ወጣቶቹ እንዲሸፍኑላቸውና እንዲከልሏቸው በመሣሪያነት ለመጠቀም መሞከራቸው ወጣቶቹ ገና በለጋ ዕድሜአቸው በማያውቁት ነገር ውስጥ ገብተው ከሕዝብ ጋር በመጣላትና በመጋጨት ያልተገባ ነገር ፈጽመው በወንጀለኝነት መዝገብ (Criminal record) ውስጥ እንዲገቡና ወደ ፊት የሚጠብቃቸው የብሩህ የተስፋ ህይወታቸው ሁሉ ጨልሞ ዕድሜአቸውን በሃዘንና በፀፀት እንዲያልፍ የሚያደርግ በመሆኑ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው።
ሕዝቡ ግን የአባ ግርማንና የተከታዮቻቸውን የተንኮል ተግባር አስቀድሞ ተረድቶ ሥለነበር የዕለቱ ሂደት በሰላም እንዲያልፍ አስቀድሞ አቅዶ የመጣ ስለነበር በዕቅዱ መሠረት ዕለቱ በሰላም ሊያልፍ ችሏል።
ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ፡ አሁንም ቢሆን አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው የቤተ ክርስቲያኗን አባላት ክደውና ንቀው በሕገ ወጥ መንገድ ቤተ ክርስቲያኗን ባለንብረት ከሆነው ስደተኛ ሕዝብ ነጥቀው ለወያኔ አገዛዝ ሹመኞች ለማስረከብ የሚያደርጉት ጥረት እንደቀጠለ ሲሆን ይህ የሚቆመው አባላቱ መብታቸውን ተጠቅመው በሚያደርጉት ትግልና የምንኖርበት ሃገር ሕግ ለጉዳዩ እልባት በሚሰጥበት ወቅት ነው። እስከዛው ድረሥ ግን የቤተ ክርስቲያኗ አባላትና መላው በስደት ላይ የሚገኝ ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህቺን በእግዚአብሔር ተራዳኢነትና በስደተኛው ሕዝብ ሃብትና ጉልበት የቆመችን ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ከማይፈሩና ሕዝብን ከማያከብሩ የሥልጣንና የንዋይ ጥመኞች  ለመከላከልና ለማዳን ገንዘቡንና ጉልበቱን አስተባብሮ በአንድነት በመቆም በቁርጠኝነት በመታገል ደባና ተንኮላቸውን ሁሉ በጣጥሶ ጥሎ ለአንዴና ለመጨራሻ በአሸናፊነት መወጣት ይኖርበታል።
አባ ግርማ ከበደ ዛሬ አሉ ነገ አላፊ ናቸው ሕዝብ ግን ትውልድ ትውልድን እየተካ ለዘለዓለም ኗሪ ነውና የነገሩ ሁሉ ቀንደኛ ተዋናኝ፤ የችግሩ ሁሉ ዋንኛ መሠረት፤ ሰላማዊ መፍትሄዎችን ሁሉ አምካኝና በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ በአንደኛ ደረጃ ተጠያቂ አባ ግርማ ከበደ እንጂ ሕዝብ ስላልሆነ በተለይ በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ችግር ቀሰቀሰ የተባለው ነገር ቀርቶ የሲኖዶስንና የሃገረ ስብከትን አጀንዳ በማንሳት ሕዝብን የበለጠ ለመከፋፈልና እርስ በእርሱ ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ ዋንኛ ተዋናኝ አባ ግርማ ከበደ ስለሆኑ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ወዳጅና ጠላቱንም ሆነ ክፉና ደጉን በሚገባ በመለየት ከሁሉም በላይ የስደት ቅርሱና ትንሿ ኢትዮጵያው የሆነችውን ቤተ ክርስቲያኑን ተነጠቀ ማለት በነፃነት ሃገር ነጻነቱን፤ ክብሩንና ህልውናውን አሳልፎ ሰጠ ማለት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያኑንም ሆነ ነጻነቱን እና ክብሩን ማስከበር ሰብዓዊ ግዴታው መሆኑን አውቆ ትግሉ በሚጠይቀው መስክ ሁሉ በመገኘት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ ሁሉ እንዲፈጽም በእመቤታችን ቅድስት ድግል ማርያም ሥም ጥሪ ተላልፎለታል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን!!

በዋልድባ ገዳም በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ

በታሪካዊው በዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ሰበብ እየደረሰ ያለውን ችግርና በገዳማውያኑ አባቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን እንግልትና መፈናቀል አስመልክቶ፣ ከዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት (ዋልድባን እናድን ኮሚቴ) የተሰጠ መግለጫ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
waldiba-ethiopia

Tuesday, June 18, 2013

የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ እና ለስልጣን ጸብ ጫሪው ህውሃት!


ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2005 ዓ.ም. (Tuesday, June 18, 2013)
የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው። ዛፍ ላይ ሆነህ እንቅልፍ ይወስድሃል? ሸለብ እንኳን ያደርግሻል ዛፍ ላይ ሆነሽ? እነደዚያ ነው የአባይ ጉዳይ ለግብጽ። ይኽ እንቅልፍ ማጣት እና ስጋት ዛሬ የጀመረ አይደለም። ባጭሩ ልተርክ። ሪቻርድ ፓንክረስት በግብጽ የተገኙ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ክርስቶስ ከመወለዱ ከ3 ሺ አመቶች በፊት ጀመሮ የግብጽ ነጋዴዎች በእግራቸው የአባይን ወንዝ ዳርቻ ተከትለው እንዲሁም በቀይ ባህር በነፋስ በሚገፉ ጀልባዎች ዛሬ ኢትዮጵያ (ያኔ የፐንት ግዛት) በሚባለው ግዛት ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ጋር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን እና ግዛቱን ምድረ ታ-ኔትጄሩ (Land Ta-Netjeru) ማለትም “ምድረ አማልዕክት” እንደሚሉት እና “የመጀመሪያ አገራችን ነው” ይሉም እንደነበር የኢትዮጵያውያን ድንበር-መሬቶች (The Ethiopian Borderlands) በሚለው መጽሐፉ ዘርዘር አድርጎ ጽፏል። የቅርቡን ብንመለከት ደግሞ በተለይ ከ1813 ዓ. ም. ጀመሮ ግብጽ የኢትዮጵያ ባለቤትነቷን በጦርነት ለማረጋገጥ የዮሐንስን ኢትዮጵያ ከሱዳን ቀላቅላ ለመግዛት በአራት አቅጣጫዎች ወረራዎች ከፍታ ሳይሳካለት ወደ መጣችበት መመለሷን ተክለ ጻዲቅ መኩሪያ “ዐፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሐፉ በሰፊው ተርኳል። በኃይለስላሴ እና በደርግ ዘመንም ለኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የጦር መሳሪያ እና ስልጠና በማቀነባበር፣ ገንዘብ በመለገስ፣ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ አገሮችን በማስተባበር፣ የአማርኛ ስርጭት ሬዲዮ በመክፈት ድጋፍ ማድረጓን እናውቃለን። ህውሃት ከተጠቃሚዎቹ ተቃዋሚዎች ውስጥ አንዱ ነው። በአባይ ጉዳይ ከጥንት ጀምሮ ግብጽ ከስጋት ነፃ የሆነ እንቅልፍ የለታም። ዛሬም ሆነ ወደፊት ግብጽ የሰላሙን መንገድ ትታ የጸበኛነቱን መንገድ ከመረጠች እንቅልፍ አይኖራትም። ይኽን የግብጽ ጭነቀት እና ስጋት ህውሃት ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ግንቦት 20 ቀን ጸብ ጫረ። ላብራራ።
የጥናቱን ውጤት ተቀበለችውም አልተቀበለችው ስለ አባይ ጉዳይ በጥናት ላይ የተሰማራው ኤክስፐርቶች ቡድን ሪፖርት እየጠበቀች ሳለች ድንገት ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም. ህውሃት የአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩን ሰበር ዜና ተሰራጨ። የኢትዮጵያ ሽብርተኛው ኢ.ት.ቭ. አስተጋባ። ዜናው ግብጽ ደረሰ። ከጥንት ጀምሮ የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ የሆነባት ግብጽ ተደናገጠች። አምባገነኑ ሞርሲ ከገበባት የውስጥ ችግር ለማምለጥ የህውሃትን ቁስቆሳ ተጠቀመ። አካራሪ የግብጽ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ጋበዞ ‘እኔ ሳልሞት ግብጽ አትጠማም’ አለ። ያጀቡት አክራሪዎችም ‘ግፋ’፣ ‘በርታ’፣ ‘አይዞህ ከጎንህ ነን’ አሉት። ይኽ ምክክራቸው ዜና ሆኖ አደባባይ ወጣ። ህውሃት ሁካታውን ያልጫረ መስሎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግብጽ ልትወጋህ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ጀመረ። የቀድሞ አባቶቻችን ድሎች ሳይቀሩ እየተጠቀሱ የቀረርቶ ድምጽ በአዲስ አበባ እየጎላ መጣ። አልባራዳይን የመሰሉት የግብጽ ዴሞክራሲ ኃይሎች የግብጽን መንግስት ወቀሱ። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎችም ቀረርቶው ገደብ ይበጅለት አሉ። የኢትዮ-ግብጽ የጦርነት ሁካታ አነሳሱ ይኽን ይመስል ነበር። ህውሃት የማያስፈልግ ጸብ ጭሯል።
ለመሆኑ ለምን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን ተቀየረ? ዜናውስ ለምን ግንቦት 20 ቀን አደባባይ ወጣ? ለዚኽ ጥያቄ አቶ በረከት ስሞዖን ሰኔ 7 ቀን ግድም 2005 የሰጠውን መግለጫ እንመልከት፥ የአባይ ወንዝ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን የተቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ህውሃት ሰልጣን ከጨበጠበት ቀን ጋር እንዲገጣጠም ሆን ተብሎ የተደረገ እንዳልሆነ ሊያስተባብል ሞክሯል። ይኽ የበረከት ስሞዖን ማስተባበያ በሽብርተኛው ኢ.ቲ.ቭ. እና በኢሳት ተዘግቧል። የአቶ በረከትን መቀላመድ ወደ ጎን አድርገን እውነቱን ሃቁን እንመልከት። የአባይ ወንዝ ፍሳሽ አቅጣጫ ግንቦት 20 ቀን እንዲቀየር ያስደረገው ህውሃት ነው። ዜናው ግብጽ እንዲደርስ ያደረገውም ህውሃት ነው። ግቡም ስልጣን ነው። ላብራራ! (1ኛ) የተለየ አሳቢ እና ከድኽነት ነፃ አውጪህ እኔ ህውሃት ነኝ የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተላለፍ እንዲችል ሆን ብሎ የአባይ ፍሳሽ የተቀየረበትን ቀን ስልጣን ከጨበጠበት ግንቦት 20 ቀን ጋር አገጣጠመው። የዚኽ እርምጃ ፖለቲካዊ ግብ ህዝቡ እንዲያመልክበት እና ስልጣኑ እንዲጠናከር ነው። ግድብ መገንባት አይደለም ግቡ። በተጨማሪ (2ኛ) የአባይ ጉዳይ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ለሆነባት ግብጽ የአባይ ፍሳሽ አቅጣጫ መቀየር ዜና የጦርነት ፖለቲካ ውስጥ እንደሚያስገባት ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በምላሹ የኢትዮጵያን ህዝብ በአገር ወዳድነት ስሜት አሳውሮ በሚፈልገው የፖለቲካ አቅጣጫ ለማስጓዝ አስልቶ ነበር። የዚኽም ፖለቲካ ስሌት ግቡ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ኃይሎች ለመምታት እና ስልጣኑን ለማጠናከር ነበር። በአገር ከሃዲነት እና በሽብርተኛነት ሽፋን። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ፈጥነው ስላጋለጡት የኢትዮጵያን ህዝብ በአባይ ስሜት አሳውሮ የዴሞክራሲ ኃይሉን ለመምታት የሚያስችለው ጊዜ ሳያገኝ ቀረ። ከሸፈበት።
ህውሃት ከግድቡ ይልቅ ስልጣኑ እንደሚበልጥበት ለአንዲት ደቂቃ እንኳን መዘንጋት አያስፈልግም። ወደፊትም ሌሎች ጸቦች ሊጭር እና ከዚያ ግብጽ ልትወጋን ነው ይልሃል። የዴሞክራሲ ኃይሎች የነፃነት ሰላማዊ ትግላቸውን አጠናክረው በመቀጠል እራሳቸውን ከህውሃት ማጭበርበር እና ጥቃት መጠበቅ አለባቸው።

Saturday, June 15, 2013

አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?

“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”
የሁለት አገር ነዋሪዎች
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት ናቸው” በሚል ወደ ውጪ በጉቦ የላካቸው ሰዎች ጉዳይም ከሳቸው ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።  ከጨው ንግድ፣ ከካሜራ ፊልም ብቸኛ አስመጪነት ሌላ በአሁኑ ወቅት ሂልተን ጀርባ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ቪክ ሬስቶራንት ጎን ግዙፍ ህንጻ ያስገነቡት አቶ ነጋ ቃሊቲ ባላቸው የነዳጅ ማደያ የከፈቱት ብቸኛ የክብደት መለኪያ/የከባድ የጭነት መኪኖች የክብደት መለኪያ “የገንዘብ ማምረቻ ማሽን” አግባብነት የሌለው ቢዝነስ እንደሆነ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ የግል የንግድ ተቋማቸው ነው። ቀደም ሲል ከኤርትራዊያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ነጋ ሃብታቸው በድንገት የተመነጠቀው ከ1991 ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እንደሆነ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ ከኢህአዴግ የቀድሞው የኦዲት ኮሚሽን ጸሐፊ ከነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃና ከቴክኒክ ክፍል ሃለፊው መቶ አለቃ ዱቤ ጁሎ ጋር በጋራ ይሰሩ እንደነበር ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ማስረጃ እንደደረሰው የገለጸ የጎልጉል ምንጮች፣ የፌዴሬሽኑ የውጪ ምንዛሬ ሂሳብና በአትሌቶች ስም ወደ ውጪ የተላኩ በርካታ ወጣቶች ጉዳይ እንደሚመመረመር ጠቁመዋል። ኮሚሽኑ ከበቂ በላይ መረጃ ቢኖረውም ማህበራትንና የርዳታ ድርጅቶችን መመርመር የሚያስችል ህጋዊ ውክልና ስለሌለው ሙስና አለባቸው በሚባሉት ማህበራትና ርዳታ ተቋማት ላይ ምርመራ ለማድረግ አዲስ ህግ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል። የኢህአዴግ የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድ ካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን አስፍሯል። በቤተሰብ ተዘረፈ የተባለው ሃብት በስም ዝርዝር ባለቤቶቹም ይፋ ሆነዋል።
በሙስና ቤተሰብ ስም የተከማቸ ሃብት ንብረቶች ታገዱ
በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ተፈፀመ በተባለው የሙስና ወንጀል በ544 ተጠርጣሪዎች ድርጅቶችና በቤተሰቦቻቸው ስም በመንግስትና በግል ባንኮች የተቀመጡ ጥሬ ገንዘብ ፣ አክሲዮኖች እንዲሁም የከበሩ ማእድናት ታገዱ።
በሌላ በኩል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች እስካሁን 92 ተሽከርካሪዎች እገዳ ተጥሎባቸዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ኮረኔል ሃይማኖት ተስፋይ ስም የተመዘገቡ ሲሆኑ ፥ 54 የሚሆኑት ደግሞ በአቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ስም የተያዙ ናቸው።
ከተሽከርካሪዎች አራቱ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን የአዳማ ቅርንጫፍ ስራ አሰኪያጅ በነበሩት አቶ አሞኘ ታገለ ስም የተመዘገቡ ሲሆን ፥ ከውጭ የሚመጡ ባለሃብቶች ወደ ሃገር ቤት እቃዎቻቸውን ሳያስፈትሹ እንዲያስገቡ በማድረግ በእነርሱና በጉሙሩክ የስራ ሃላፊዎች መካከል ጉቦ በማቀባበል መንግስትን ጎድቶ ራሳቸውን ጠቅመዋል በሚል በተጠረጠሩት በአቶ ዳዊት መኮንን ስም  እንዲሁ አራት ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል።
ሌሎች ሰባት ተሽከርካሪዎች በአልቲሜት ፕላን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሲመዘገቡ ፥ ስድስት የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች ደግሞ በኢትባ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተመዝግበው ይገኛሉ።
የፌደራሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በተጠቀሱ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶች እና ሌሎች አካላት እግድ የተጣለባቸው ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ ፣ እንዳይለወጡ እና ለሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፉ አስደርጓል።
የእነ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና ሌሎች መዝገቦችን ሳያካትት በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ በተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች ፥ ተፈጸመ በተባለው የሙስና ወንጀል  ከቀረጥና ታክስ ጋር በተያያዘ ከተገኙ ሰነዶች ብቻ መንግስት ከ 230 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንደደረሰበት ነው የሚለው የኮሚሽኑ መረጃ የሚያመለክተው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)
በፌስቡክ “የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ስም ዝርዝር ይፋ ወጣ” እየተባለ የተዘበተባቸው የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ሙስ ስም ዝርዝር
አባቡ አለሙ ገብሩ
ምስጋናው ይስሃቅ እጅባ
በረከት ይስሃቅ እጅባ
ታደሉ አለምነው ተፈራ
ፀጋነሽ አለምነው ተፈራ
አባተ ጋሻው ቦጋለ
ጌጤ ጋሻው ቦጋለ
ዘርፌ ጋሻው ቦጋለ
ፀሐይ ጋሻው ቦጋለ
ትዕግስት ጋሻው ቦጋለ
አስፋው ጋሻው ቦጋለ
መብራት አበበ አብርሃ
ቤቴልሄም አማኑኤል ሰይፈ
እቁባይ ተከለ አርአያ
ብሌን አማኑኤል ሰይፈ
ሊዲያ አማኑኤል ሰይፈ
እየሩሳሌም ስማቸው ከበደ
መቅደላዊ ስማቸው ከበደ
ኤልሻዳይ ስማቸው ከበደ
ኢቫና ስማቸው ከበደ
አያልነሽ ይመር ጌታሁን
ሠለሞን ከበደ ካሳ
ምንትዋብ ከበደ ካሳ
ዳንኤል ደባሽ ሀገሩ
ናኑ ደባሽ ሀገሩ
ሰላማዊት ደባሽ ሀገሩ
ሣራ ደባሽ ሀገሩ
ኤፍሬም ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ሄኖክ ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ይትባረክ ነጋ ገ/እግዚአባሄር
ሠላም ነጋ ገ/እግዚአብሔር
ራሄል ነጋ ገ/እግዚአብሄር
ዮርዳኖስ ደሣለኝ ገ/እግዚአብሄር
ቅድስት ድጉማ ዋቅጅራ
አናኒያ ብርሃኔ እጅጉ
ተዋበች ወርቁ ወልፃዲቅ
ብሩክ ከበደ ታደሰ
ፍቅረማርያም ከበደ ታደሰ
ክብነሽ ከበደ ታደሰ
ዳኝነት ከበደ ታደሰ
ትዕግስት ከበደ ታደሰ
ሙሉነህ ከበደ ታደሰ
ትዕዛዙ ከበደ ታደሰ
ቴዎድሮስ ማዕረግ አዱኛ
አይንአዲስ በረከት ኃ/ጊዮርጊስ
ወይንሸት ወርቁ አንጋሶ
መብራቱ እጅጉ አበራ
የማነ ብርሃን እጅጉ አበራ
መሀሪ እጅጉ አበራ
ዮሐንስ እጅጉ አበራ
ለምለም እጅጉ አበራ
ሠናይት እጅጉ አበራ
ካሰች አምደመስቀል መገርሳ
ዮናታ ማርክነህ አለማየሁ
ኤልሻዳይ ማርክነህ አለማየሁ
ባልጊቴ አለማየሁ ወዳቦ
ባፋነ አለማየሁ ወዳቦ
አየለ አለማየሁ ወዳቦ
ብርሃኑ ዓለማየሁ ወዳቦ
አበራ አለማየሁ ወዳቦ
እጀትግስት ዓለማየሁ ወዳቦ
ሚካኤል አምደመስቀል መገርሳ
ዳኛቸው አምደመስቀል መገርሳ
ተረፈ አምደመስቀል መገርሳ
ተክሉ አምደመስቀል መገርሳ
ደርባቸው አምደመስቀል መገርሳ
መቅደስ አምደመስቀል መገርሳ
ትዝታ አምደመስቀል መገርሳ
ሙሉጸጋ አምደመስቀል መገርሳ
ውቢት ኃይለገብርኤል አስፋው
ያዕቆብ ደጉ ሆቢቾ
ዮናታል ደጉ ሆቢቾ
ዳግማዊ ደጉ ሆቢቾ
ኡፋይሴ ሆቢቾ አልቤ
ዲቃም ቤቢሶ አልቤ
ካሳሁን ኃይለገብርኤል አስፋው
አምሃ ኃይለገብርኤል አስፋው
ዝናሽ ኃይለገብርኤል አስፋው
ምሳዬ ኃይለገብርኤል አስፋው
አበባ ኃይለገብርኤል አስፋው
ፍሬህይወት ጌታቸው ሀብቴ
ጌታቸው ምስጋና ተፈሪ
ዮሴፍ ጌታቸው ምስጋና
ዮናታን ጌታቸው ምስጋና
ጌታቸው ሀብቴ ተክለሃይማኖት
አብረኸት ገብረመድህን ጣሰው
አበባው ጌታቸው ሀብቴ
ገስጥ ጌታቸው ሀብቴ
ደሳለኝ ጌታቸው ሀብቴ
ቤተልሄም ጌታቸው ሃብቴ
ዜና ጌታቸው ሀብቴ
ሳህሌ ገላው ፈንቴ
ላይኩን ውብየ ተሰማ
አበባው ላይኩን ውብየ
በትረወርቅ ላይኩን ውብየ
ዳዊት ላይኩን ውብየ
አብርሃም ለይኩን ውብየ
ህሉፍ አብርሃ ሐጎስ
አስመለሻ አብርሃ ሐጎስ
ስዬ አብርሃ ሐጎስ
አሰፋ አብርሃ ሐጎስ
ወ/ስላልሴ አብርሃ ሐጎስ
ትምኒት አብርሃ ሐጎስ
ፀሐይነሽ ገ/ሚካኤል ገብሩ
ንግስቲ ሳመሶነ ብሩ
እጅግጋየሁ ሳምሶን ብሩ
ኢትዮጵያ ሳምሶን ብሩ
ያለም መብራት ሳምሶን ብሩ
ቢተወደድ ሳምሶን ብሩ
ሚዛን ሳምሶን ብሩ
በእግዚአብሔር አለበል ኃይሉ
ኤልሳ ታደለ ኃይሉ
ናአምን በእግዚአብሔር አለበል
ቅዱስ በእግዚአብሄር አለበል
በረኽት በእግዚአብሄር አለበል
አለበል ኃይሉ አዱኛ
እቴነሽ ብሩክ ደስታ
ዘላለም አለበል ኃይሉ
ነፃነት አለበል ኃይሉ
የሰውዘር አለበል ኃይሉ
በሁሉም አለበል ኃይሉ
ሰላም አለበል ኃይሉ
ዮናስ ታደለ ኃይሉ
ሚካኤል ታዳለ ኃይሉ
ዮሴፍ አዳዩ ገብሩ
ሃና በርሄ ሀጎስ
ግሎሪ ዮሴፍ አዳዩ
ሊዮ ዮሴፍ አዳዩ
አዳዩ ገብሩ ዲኒ
አብርሃ አዳዩ ገብሩ
ራህዋ አዳዩ ገብሩ
ብርክቲ አዳዩ ገብሩ
ኢንዲሪያስ አዳዩ ገብሩ
ፋና አዳዩ ገብሩ
ታበቱ አዳዩ ገብሩ
ስላስ አውዓለ ሐጎስ
ኃ/ስላሰ በርሄ ሀጎስ
ተስፋይ በርሄ ሀጎስ
ብሩር በርሄ ሀጎስ
ዘቢብ በርሄ ሀጎስ
ጌታነህ ግደይ ንርኤ
ኤደን ብርሃነ ገ/ህይወት
አበባ ግደይ ንርኤ
ዙፋን ግደይ ንርኤ
ደስታ ግደይ ንርኤ
ዮሐንስ ግደይ ንርኤ
መንግስቱ ግደይ ንርኤ
ሀብቶም ግደይ ንርኤ
ቢኒያም ብርሃነ ገ/ህይወት
ኤልሻዳይ ብርሃነ ገ/ሕይወት
ብርክታዊት ብርሃን ገ/ህይወት
ገ/መድህን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ገ/ህይወት ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ኪዳን ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሱራፌል ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ብርያ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
እግዜሄሩ ወ/ጊዮርጌስ ወ/ሚካኤል
ግደይ ተስፋ ገ/ስላሴ
ስላስ ተስፋይ ገ/ስላሴ
ለተመስቀል ተስፋይ ገ/ስላሴ
ማህተመሥላሴ ጥሩነህ በርታ
ማሞ በርታ ባቦ
ታደሰ በርታ ባቦ
ዳዊት በርታ ባቦ
ብሩክ በርታ ባቦ
አበበች በርታ ባቦ
አመለወርቅ በርታ ባቦ
እመቤት በርታ ባቦ
ፍቅርተ በርታ ባቦ
ይልማ ፈንታ ቻይ
አንጋች ፈንታ ቻይ
ሸዋዬ ፈንታ ቻይ
ፈጠነ ታገለ አወቀ
ቻለ ታገለ አወቀ
እማዋ ታገለ አወቀ
አልጋነሽ ታጋለ አወቀ
እመቤት ታጋለ አወቀ
ዳዊት አሰፋ ዘውዱ
ትዕግስት አሰፋ ዘውዱ
ጥሩወርቅ አሰፋ ዘውዱ
ተወዳጅ አሰፋ ዘውዱ
መልካም አሰፋ ዘውዱ
ማህሌት አሰፋ ዘውዱ
ዝናሽ ብርሃኑ በሻህ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
ፍሬህይወት ብርሃኑ በሻህ
አብዮት ብርሃኑ በሻህ
ግልነሽ ብርሃኑ በሻህ
ሰለሞን ብርሃኑ በሻህ
አዲስ ብርሃኑ በሻህ
ካህሳይ ጉላል አለመ
ዘውዲቱ ለምለም ገ/ማርያም
ብስራት ገ/መድህን ተስፋይ
ግርማይ ብስራት ገ/መድህን
ዮሀንስ ብስራት ገ/መድህን
አበባ ብስራት ገ/መድህን
ለተመስቀል ብስራት ገ/መድህን
ሚዛን ብስራት ገ/መድህን
አክበረት ብስራት ገ/መድህን
ገ/መድህን ሀጎስ ንጉሴ
ጌቱ ገ/መድህን ሀጎስ
ሳራ ገ/መድህን ሃጎስ
ፍፁም ገ/መድህን አብርሃ
ነፃነት ብርሃኑ በሻህ
አለም ስንሻው አማረ
ሐጎስ ፍፁም ገ/መድህን
ኃይሌ ፍፁም ገ/መድህን
ኤርሚያስ ፍፁም ገ/መድህን
ደሊና ፍፁም ገ/መድህን
ገነት ገ/መድህን ሀጎስ
ኮነ ምህረቱ እሸቱ
መንበረ ታምራት በየነ
ፍስሐ ኮነ ምህረቱ
ፍረህይወት ኮነ ምህረቱ
መስከረም ኮነ ምህረቱ
ቅድስት ኮነ ምህረቱ
ዘይሰድ ኢሳ አወል
ተስፋዬ ወልዱ ፍስሃ
ሰብለወንጌል ዘውዴ ዋለ
ዳንኤል ዘውዴ ዋለ
ሙሉቀን ዘውዴ ዋለ
ብርሃኑ ዘውዴ ዋለ
ጌትነት ዘውዴ ዋለ
ታምራት ዘውዴ ዋለ
አምባው ሰገድ አብርሃ
ብርነሽ ሐጎስ ካህሳይ
ህሊና አምባው ሰገድ
ብሩክ አምባው ሰገድ
ሜሮን ገ/ስላሴ ገብሩ
ሳባ ኪሮስ ወ/ገብርኤል
አፀደ ገ/ስላሴ ገብሩ
አብርሃ ገ/ስላሴ ገብሩ
ያሬድ ሰገድ አብርሃ
ክብሮም ሰገድ አብርሃ
ፀዳለ ሰገድ አብርሃ
ፅጌ ሰገድ አብርሃ
ፀሐይነሽ ሰገድ አብርሃ
ተክለአብ ዘርአብሩክ ዘማርያም
ፅጌረዳ ደርበው አዳነ
ዘርአብሩክ ዘማርያም ረዳ
ሂሩት ፀጋዬ ገ/መድህን
አቤል ተክለአብ ዘርአብሩክ
ምህረትአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሠላማዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ፀጋዘአብ ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ሣምራዊት ዘርአብሩክ ዘማሪያም
ዳንኤል ደርበው አዳነ
ሠላዊት ደርበው አዳነ
ሄሳን ደርበው አዳነ
ኤደን ደርበው አዳነ
ጌታሁን ቱጂ ደበላ
ምኞት ብርሃኑ አበራ
ሮዳስ ጌታሁን ቱጂ
አዴራት ጌታሁን ቱጂ
ሲሳይ ቱጂ ደበላ
እመቤት ቱጂ ደበላ
ጋሻው ብርሃኑ አበራ
አዲሱ ብርሃኑ አበራ
ሠላም ብርሃኑ አበራ
ክብረወሰን ብርሃኑ አበራ
ዘለቀ ልየው ካሳ
ግንቻየው አድሮ ኃይሉ
ዮሐንስ ዘለቀ ልየው
ሊዲያ ዘለቀ ልየው
ጥሩአለም አድሮ ኃይሉ
ዮሴፍ አድሮ ኃይሉ
ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ተናኜ እሸቴ አዳፍሬ
ሠላማዊት ያዴሳ ሚዴቅሳ
ገመቺሳ ያዴሳ ሚዴቅሳ
ብልሴ ያዴሳ ሚዴቅሳ
መኮንን ሚዴቅሳ ዲባባ
በጂጌ ሜዴቅሳ ዲባባ
ሽታዬ ሚዲቅሳ ዲባባ
ፅጌ ሚዴቅሳ ዲባባ
ልኪቱ ሞሲሳ ቦኮ
ከበደ ደጀኔ ገለታ
ፍስሐ ደጀኔ ገለታ
የሻነው ደጀኔ ገለታ
ዘላለም ደጀኔ ገለታ
ትዕግስት ደጀኔ ገለታ
መታሰቢያ ደጀኔ ገለታ
ሠናይት ደጀኔ ገለታ
መላኩ ግርማ ገብሬ
እህተ ቱኒ ኦርጋጋ
ብርሃኑ ግርማ ገብሬ
ጌትነት ግርማ ገብሬ
አብርሃም ግርማ ገብሬ
ዳዊት መኮንን ተመስገን
እሴታ ባረጋ ሽራጋ
አሚን ዳዊት መኮንን
ዘሪሁን ዳዊት መኮንን
ዜና መኮንን ተመስገን
ማርታ መኮንን ተመስገን
መኮንን ተመስገን የሽታ
ፍሬሕይወት ማሞ አና
መቅደስ ባረጋ ሽራጋ
ብርሃኑ ባረጋ ሽረጋ
ቅጣው ባረጋ ሽራጋ
ባረጋ ሽራጋ ሽራጋ
አስፋው ስዩም ታፈረ
ማርታ የማነህ ተስፈሚካኤል
መስፍን ስዩም ታፈረ
መንገሻ ስዩም ታፈረ
አንባቸው ስዩም ታፈረ
ሂሩት ስዩም ታፈረ
ሠላማዊት ግርማ ፈለቀ
በፀሎት አበበልኝ ተስፋዬ
ኪሮስ ገ/መድህን ገ/ተክለ
ትዕግስት ተስፋዬ ፊታሞ
ሊዲያ ተስፋዬ ፊታሞ
ሐዲያወርቅ ተስፋዬ ፊታሞ
ታሪኩ አበበ ፊታሞ
ፍስሃ አበበ ፊታሞ
ማርክስ አበበ ፊታሞ
ምንአለ አበበ ፊታሞ
ዘይነባ እሸቱ ኃይሌ
ኑርሃን ጌታቸው አሰፋ
ሐይመን ጌታቸው አሰፋ
ሰሚሩ ጌታቸው አሰፋ
ኢምራን ጌታቸው አሰፋ
የንጉስነሽ አሰፋ ሀምዛ
መንገሻ አሰፋ ሃምዛ
መሰለ አሰፋ ሃምዛ
ልዑልሰገድ አሰፋ ሀምዛ
መሐመድ አሰፋ ሀምዛ
ናስር እሸቱ ሃይሌ
ዛህር እሸቱ ሃይሌ
መሐመድ እሸቱ ሀይሌ
ራቢያ እሸቱ ሃይሌ
ምፅላል ሃይሉ አለማየሁ
ጌጤ ማቲዮስ ገ/ኪዳን
ትዕግስት በላቸው በየነ
ሱራፌል በላቸው በየነ
ሰላማዊት በላቸው በየነ
አበባየሁ ዘበነ ተኮላ
ማሚቱ በየነ ገ/ዮሐንስ
አዳነ ተሰማ በረሳ
ታሪኩ ተሰማ በረሳ
ሲሳይ ተሰማ በረሳ
ተፈሪ ተሰማ በረሳ
ዜና ተሰማ በረሳ
ሙሉጌታ ተሰማ በረሳ
እመቤት ተሰማ በረሳ
ጠጅነሽ ጎሳዬ በረሳ
አንለይ አሳምነው ተሰማ
ራሄል ገበደ ኃ/ማርያም
ናርዶስ አንለይ አሳምነው
ፍፁም አሳምነው ተሰማ
ማናዬ አሳምነው ተሰማ
ይርጋለም አሳምነው ተሰማ
ፍፁም ከበደ ኃ/ማርያም
በኃይሉ ከበደ ኃ/ማርያም
ሱራፌል ከበደ ኃ/ማርያም
ቢኒያም ከበደ ኃ/ማርያም
መስፍን ከበደ ኃ/ማርያም
እመቤት ከበደ ኃ/ማርያም
መሰረት መንግስቱ በየነ
ሠላማዊት ማሩ ፍቅሩ
ፍቅርተ ማሩ ፍቅሩ
ስንታየሁ ወይም አሰለፈች ማሩ ወርዶፋ
በቀለች ማሩ ወርዶፋ
ጥሩወርቅ መንግስቴ በየነ
ገ/መድህን ገ/የሱስ ስብሃት
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የሱስ
ንብረት ገ/መድህን ገ/የሱስ
ማሞ ኪሮስ በዛብህ
ራሄል አስረስ መኮንን
አዶኒያስ ማሞ ኪሮስ
ብሩክ ማሞ ኪሮስ
ዳግም ማሞ ኪሮስ
ኢዮስያስ ማሞ ኪሮስ
ናሆም ማሞ ኪሮስ
ደሳዊ ማሞ ኪሮስ
ኪሮስ ገ/ህይወት በርሄ
አለም ኪሮስ በዛብህ
ፅጌ ኪሮስ በዛብህ
ፋና ኪሮስ በዛብህ
አፀደ ኪሮስ በዛብህ
አብይ አስረስ መኮንን
ቤተልሄም አስረስ መኮንን
ሂሩት አስረስ መኮንን
ፀደይ አስረስ መኮንን
ሸዋዬ መስፍን አበራ
ኤልዳና ስንሻው አለምነህ
አርሴማ ስንሻው አለምነህ
ምስጋና ይሳቅ ገድባ
በረከት ይሳቅ ገድባ
የመከረ መኮንን ተሰማ
ማራማዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
መቅደላዊት ዳዊት ኢትዮጵያ
ቤተል ዳዊት ኢትዮጵያ
ወለላ ተስፋዬ ብሩ
ተፈሪ ኢትዮጵያ መኮንን
ፍሪው ኢትዮጵያ መኮንን
ግሩም ኢትዮጵያ መኮንን
ትዕግስት ኢትዮጵያ መኮንን
ውቢቱ ኢትዮጵያ መኮንን
ለምለም ኢትዮጵያ መኮንን
ፀሐይነሽ መንግስቱ አዳል
መቅደስ መኮንን ተሰማ
እሸቱ ግረፍ አስታክል
ብስኩት ደመቀ ታከለ
ማየት እሸቱ ግረፍ
ቤተል እሸቱ ግረፍ
ኢዮስያስ እሸቱ ግረፍ
ታደሰ ደመቀ ታከለ
በኃይሉ ደመቀ ታከለ
ብርሃኑ ደመቀ ታከለ
ልፍነሽ ገለታ ዳዲ
እቴነሽ ግረፍ አስታክል
በላይነሽ ግረፍ አስታክል
ዘውዱ ግደይ ካህሲ
በረከት ተመስገን ስዩም
ሚሚ ተመስገን ስዩም
ካህሳይ ጉልላት አለመ
ሰመረ ግደይ ካህሲ
ኢሊኑ ግደይ ካህሲ
ምህረት ገ/መድህን ገ/የስ
ትርሃስ ገ/መድህን ገ/የስ
ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ
ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማ
ኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል
አዲስ የልብ ህክምና ክሊኒክ
ምፍአም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ነፃ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዎው ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ኤምዲ ትራንዚት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ዲ ኤች ሲሚክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የስም ዝርዝሩን የወሰድነው ከኢሳት ነው።

ESAT Daily News Amsterdam June 15, 2013 Ethiopia


Friday, June 14, 2013

ESAT Daily News Amsterdam June 14, 2013 Ethiopia


አቶ አብርሃም ያዬህ የምላስዎትን አፈሙዝ በአቶ ገ/መድኅን አርአያ ላይ አያዙሩ!

ሸግዬ ነብሮ
የዚህ ጽሑፍ መነሻ በቅርቡ አውራምባ ታይምስ የተባለው ድረ-ገጽ ከአቶ አብርሃም ያዬህ ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስና ማለዳ ታይምስ የተባለው ሌላው ድረ-ገጽ “መደመጥ ያለበት ቪዲዮ” በማለት ያናፈሰው ነው።
Abraham Yayeh
አብርሃም ያዬህ
ወደ አቶ አብርሃም ቃለ – መጠይቅ በዝርዝር ከመግባታችን በፊት “ማን ያርዳ የቀበረ፣ ማን ይናገር የነበረ” የሚለውን የሀገራችንን ብሂል በማጤን አቶ አብርሃም ያዬህንም ሆነ አቶ ገ/መድኅን አርአያን በተመለከተ በቅርብ የማውቀውን አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ አቶ አብርሃም ወደ ሀገር ቤት በገቡበት ጊዜ የነበሩ እማኞች በሙሉ በሕይዎት የሉም፤ ወይም ቢኖሩም እንኳን ምንም አይሉም ብለው አስበው ከሆነ መሳሳታቸውን አስቀድሜ ልጠቁማቸው እወዳለሁ።
አቶ አብርሃምያዬህ የመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍንና አባይ ፀሐዬ የሕወሓት ማፊያ ዘራፊ ቡድን ቁንጮ አባላት የቅርብ ጓደኛና የአንዳንዶቹም የሥጋ ዘመድ ናቸው። ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በሥራ ዓለም በቆዩበት ዘመን ምንም በደል ያልደረሰባቸውና የተደላደለ ኑሮ የነበራቸው ሲሆን፣ ግብር እየከፈለ ያስተማራቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በመክዳት እንደ ዘመዶቻቸው የጎጠኝነት ህመም (Narrow Tribal Mentality) ተጠናወቷቸው ትግራይን ከኢትዮጵያ ለማስገንጠልና የትግራይ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከተመሠረተ በኋላ የአመራር ቦታ እይዛለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ ሀገር ጥለው የፈረጠጡ ደካማ ፍጡር ናቸው። (እንደ ቀድሞ ታጋዮች፣ የአሁን ሀገር ዘራፊዎች የናጠጠ ዲታ እሆናለሁም ብለው ሊሆን ይችላል።)
አቶ አብርሃም እጀ ለስላሳ፣ ባለረጅም ምላስ፣ ለሜዳ ትግል የማይበቁና የወንድነት ሀሞት የሌላቸው በመሆናቸው ከመከረኛው የትግራይ ሕዝብ በሚገኘው የድርቅ እርጥባን ፍርፋሪ ካርቱም ውስጥ እየተንደላቀቁ የኖሩ ቅምጥል “ታጋይ” ናቸው። የአቶ አብርሃም የውጭ የሥራ ተልዕኮ ከዚህ በፊት እርሳቸው ለማናፈስ እንደሞከሩት የሕወሓት የመረጃ መኮንንነት አይደለም። የመረጃ መኮንንነት መለፍለፍን ሳይሆን ማዳመጥንና ማመዛዘንን የሚጠይቅ እነ ምን ይዤ ልቅረብ ብለው የሚሠሩት ሞያ ሳይሆን፣ የሰከነ አዕምሮ የሚጠይቅና በተክለፈለፈ የአብርሃም ያየህ ዓይነት ፍጡር የሚከናወን ተግባር አይደለም። ስለሆነም የግለሰቡን ፀባይ የተረዱት ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው የአብርሃም ምላስ ይጠቅማል ባሉት የአገናኝነት (Laison Officer) ተግባር ላይ መደቧቸው። ለግል ጥቅም የቆሙ የሱዳን ባለሥልጣኖችን በገንዘብ በመያዝ ድጋፍ ማስገኘት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባንኮች ወያኔ በዘረፈው ገንዘብ የምዕራቡ ዓለም ሆዳም ጋዜጠኞችን በመደለል በየሆቴሉ በመጋበዝና ውስኪ በማጠጣት የድለላ ሥራ በመሥራት ትግራይ ገብተው ድርቅን በተመለከተ ቪዲዮና ፎቶ በማንሳት በድርቅ ዕርዳታ ስም ለወያኔ እኩይ ተግባር የሚውል ገንዘብ የሚያስገኝ የፕሮፓጋናዳ ሥራ እንዲሠሩ ማድረግ ነው።
በሌላ በኩልም የዛሬ የሕወሓት መኳንንቶች ወደ ሱዳን ብቅ ሲሉ ማረፊያና ቆነጃጅቶችን በማዘጋጀት፣ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት ይላላኩ እንደነበር ከጤፍ የማይቆጥሩዋቸውና የሚንቁዋቸው ዛሬ በሸራቶን ልዩ ክፍል ተዘጋጅቶላቸው የሚንደላቀቁት የሕወሓት ማፊያ ቡድን ዘራፊ ቢሊዬነሮች ሁሌም የሚሉት ነው። አቶ አብርሃም የትግራይን በረሃ ያልረገጡና የስሚ ስሚ ከሌላ ያዳመጡትን ሽንኩርትና ቅመም ጨምረው አጣፍጠው የሚያቀርቡ ጥሩ የሸክላ ድስት ናቸው። የአቶ አብርሃም ምላስ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ መቋጠሪያ ሸምቀቆ ስለሌለው እነ ስብሃት ነጋ ወደ ሚስጥሩ ጓዳ ሳያስገቡ በጥንቃቄ በገደብ በሩቅ የያዙዋቸው አገልጋያቸው (Servant) ነበሩ።
ማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ (ማሌሊት) ሲመሠረት አቶ አብርሃም በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ቀርቶ በተራ አባልነት እንኳን ያልታጩ ጀሌ መሆናቸውን ሲገነዘቡ ነው “እኔ ከማን አንሼ ነው” በማለት ተቆጥተው እና መለስና ስብሃት ጋ ካልቀናኝ የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ልብ እሰርቃለሁ፤ የናቀኝንም እበቀላለሁ ብለው በማስላት ነበር ወደ አዲስ አበባ የገቡት።
አቶ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ የተቀበላቸው የመረጃ መሥሪያ ቤቱ ቢሆንም የግለሰቡን ፀባይ በመረዳቱ ያሠማራቸው በፕሮፓጋንዳ ሥራ ብቻ ነው። አቶ አብርሃም ስለሕወሓት ወያኔ የሆነውን ታሪካዊ መረጃ ከማነብነብና ከተለያዩ ጽሑፎች ካገኟቸው መረጃዎች በስተቀር ትግራይ በረሃ ውስጥ ስላለው ሁኔታ የሚያውቁት የስሚ ስሚ ካልሆነ በስተቀር አንድም ነገር የለም። ስለትግራይ በረሃና ጓዳ ጎድጓዳ የእጃቸውን መዳፍ ያክል የሚያውቁትና ለመረጃው መ/ቤት እጅግ ጠቃሚ መረጃ የሰጡት ግን አቶ ገ/መድኅን አርአያ ነበሩ። ሆኖም ግን ሚስጥሩ ያልገባቸውና የአብርሃም ያየህን ንግግር በቴሌቭዥን መስኮት ያዳመጡና አሁንም ወያኔ በሀገራችን ላይ ከሚፈፅመው ጋር እያዛመዱ ሰውየውን እንደትንቢተኛ የሚያዩዋቸው አሉ። ሀቁ ግን በመረጃ መሥሪያ ቤቱ ቢሮ አብርሃም ያየህን ተዋናይ አድርጎ የተሠራ ድራማ ነው። መረጃው የተገኘው ከአቶ ከአቶ ገብረ መድኅን አርአያና ከመረጃ መ/ቤቱ ነው።
ወያኔ ኢትዮጵያን ሲወር አቶ አብርሃም የፈረጠጡት ወደ ዩጋንዳ ነው። በዩጋንዳ ቆይታቸውም ወያኔን እታገላለሁ በሚል ከኮሎኔል መንግሥቱ ገንዘብ ለመቦጨቅ ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ ግለሰቡ ባላቸው የሲጋራ፣ የመጠጥና የሴሰኝነት ባህሪ ገንዘብ ስለማይበቃቸው ወደ ተራ ሌብነት በመዝቀጥ በንጉሡ ጊዜ የፖሊስ ጄኔራል የነበሩትን የጄኔራል ጋሻው ከበደን ሴት ልጅ ለመዝረፍ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው አራት ዓመት ተፈርዶባቸው ካምፓላ ውስጥ ሉዚራ ወደተባለው ወህኒ ቤትና ከባድ ወንጀለኞች በሚታሰሩበት Block A ተወርውረው ሳለ በዩጋንዳ፣ አሜሪካና መላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከእሥር እንዳስፈቷቸውና ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ እንደረዷቸው ይታወሳል።
ውለታ ቢሱና በልቶ ካጁ አብርሃም ያዬህ ግን በዴንማርክ ኑሯቸውን ካደላደሉ በኋላ ቅንጅትንና የረዷቸውን ኢትዮጵያውያን ለምን እኔን በትግል አመራርነት አላቀፉኝም በሚል በተለያዩ ጊዜያቶች ሲያንቋሽሹና የመለስ ዜናዊን ታላቅነት ሲለፍፉ የወያኔ ድረ-ገጽ በሆነው በአይጋ ፎረም ሳይቀር ተስተውለዋል።
በቅርቡም በለመደ አፋቸው አውራምባ ታይምስ በተባለው ድረ-ገጽ ላይ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ በጊዜው የነበሩት ሰዎች ያለቁ መስሏቸው “ላም ባለዋለበት ኩበት ለቀማ” እንዲሉ እራሳቸውን አዋቂ አድርገው አቶ ገብረ ምድኅን አርአያን አንቋሽሸዋል። በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በቀረበው ቃለመጠይቅ ላይ አቶ ገብረ መድኅን ለመሳተፍ ፈቃደኛ እንዳልነበሩና እንዲያውም ፊታቸውን ለማሳየት እንዳልፈለጉ፣ ወደ መገናኛ ብዙሐን ያመጧቸው እርሳቸው እንደሆኑ፣ ሰዎች ከአቶ ገ/መድኅን ጋር በአንድ ላይ መቅረብ እንደሌለባቸውና ነገርም ስለሚያበላሹ እንደመከሯቸው፣ አቶ ገ/መድኅን ከእርሳቸው በፊት ሁለት ዓመት ቀድመው የገቡ ቢሆንም ጠቃሚ ሆነው ባለመገኘታቸው ተጥለው እንደተቀመጡ፣ በሐውዜን ጉዳይ ላይ የተናገሩት ሁሉ ሀሰት እንደሆነና እንዲያውም ሐውዜን ሲደበደብ አዲሰ አበባ እንደነበሩ፣ አብርሃም ያዬህ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ቀባጥረዋል።
አቶ ገ/መድኅን አርአያ የወያኔ በጅሮንድ ወይም ገንዘብ ያዥ የነበሩ፣ ሕወሓት ሲመሠረት ጀምሮ አብረው የነበሩ፣ የወያኔን ገመና ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ከካርቱም መሸታ ቤት ሳይሆን ከትግራይ በረሃ የመጡ፣ የረጋ መንፈስ ያላቸው፣ አስተዋፅዎአቸው (ክሬዲታቸው) በከፊል በአፈ-ጮሌው አብርሃም ያዬህ የተሰረቀባቸው ሀቀኛና ጥሩ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ናቸው። ከላይ እንደተገለፀው በአቶ አብርሃም አፈ-ጮሌነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቀረበው ገለፃ መረጃው የተገኘው ከአቶ ገ/መድኅንና ከደኅነነቱ መ/ቤት የመረጃ ዘገባ (Intelligence Analysis) ነው።
በእንግሊዝ ሀገር በለንደን ከተማ የወያኔ የመረጃ ሠራተኛ ተባባሪ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው ኃይለ ሥላሴ ግርማይ የተባለው ቅጥረኛ እየተከፈለው አቶ አብርሃም በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን ሲለፈልፉ ከጀርባ ሆኖ መረጃ ሲያቀብልና ጽሑፍ ሲሰጥ የነበረ ነው። የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንዲሉ ኃይለ ሥላሴ ግርማይ የአቶ ገ/መድኅን አርአያ  የእናታቸው ልጅ ታናሽ ወንድማቸው ሲሆን፣ በተለያዩ ጉዳዮች በተለይም እነ ተክሉ ሐዋዝ በእነ ስብሓት ነጋ በመገደላቸው ተጣልቶ እየተከፈለው ለደኅንነቱ መ/ቤት መረጃ ሲያቀብል የነበረ ግለሰብ ነው። ሮም ላይ በጣሊያን መንግሥት አማክኝነት የደርግና የወያኔ የእርቅ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት የአውሮፕላን ቲኬትና የልዩ ልዩ ወጭ ተልኮለት ከለንደን ወደ ሮም በመሄድ ከረጅም ዓመታት በኋላ ከአቶ ገ/መድኅን ጋር እንዲገናኝ ተደርጓል። (አቶ አብርሃም አዲስ አበባ በቴሌቭዥን ሲለፈልፉ የአቶ ገ/መድኅንን የሮም ጉዞ እንኳን አያውቁም ነበር።)
ህምባባ ሼዊት በተባለ ኦፕሬሽን ወያኔ አቶ ገ/መድኅንንና አቶ አብርሃም ያዬህን ለማጥፋት ያደረገው ዝግጅት ተደርሶበት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲነገራቸው መሬት ተቀድዳ በዋጠችኝ ሲሉ የነበሩት አቶ አብርሃም ስንት ማደሪያ እንደቀያየሩና ያሳዩት የባህሪ መለወጥ ማንነታቸውን አስመስክሯል። በአንፃሩ ግን አቶ ገ/መድኅን በመገናኛ ብዙሐን ከመቅረባቸው በፊት በአንድ የመንግሥት መ/ቤት እንደ ማንኛውም ሰው ሳይፈሩ ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩና እንኳን ሸፍኑኝ ሊሉ ግምባር ቀደም ሆነው ደረታቸውን ሰጥተው ወያኔን ፊት ለፊት የመፋለም ቁርጠኛ አቋማቸውን እጃቸውን ለመንግሥት ከሰጡ ቀን ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ያስመሠከሩ ሀቀኛና ቀጥተኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
አቶ ገ/መድኅን አርአያ አቶ አብርሃም እንደሚሉት ከእርሳቸው በፊት ሁለት ዓመት በኢትዮጵያ ካለሥራ ተጥለው የቆዩ አይደሉም። አቶ ገ/መድኅን ከአቶ አብርሃም በፊት ኢትዮጵያ ውስት የቆዩት ለዘጠኝ ወራት ሲሆን ስለ ሕወሓትም ሆነ በትግራይ በረሃ የውሃ ኩሬ ሳይቀር የት እንዳለ የማስታወስ ከፍተኛ ችሎታ ስለነበራቸው ሳይጋለጡ ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲሠሩ የቆዩ እንጅ በሬዲዮና በቴሌቭዥን የሚያቅራሩ የድል አጥቢያ አርበኛ ወይም የከተማ ፋኖ አልነበሩም።
ለመሆኑ አቶ አብርሃም ቀን በቴሌቭዥን ሲጮሁና ማታ ማታ ደግሞ ከአዲስ አበባ እስከ ናዝሬት በሚገኙ መሸታ ቤቶች “አሆይ ላሎዬ” ሲሉ፣ ጀግናውና ሐቀኛው አቶ ገ/መድኅን ግን ትግራይ በረሃ ድረስ እንደገና ገብተው አመርቂ ሥራ ሠርተው መውጣታቸውን ብነግረዎት ምን ይላሉ!? አቶ አብርሃም ያዬህ የት እንደነበር ሊያውቁት ቀርቶ ምንነቱን እንኳን ሰምተው የማያውቁትና የወያኔ ሬዲዮ ጣቢያ የነበረበት ክሳድ ግመል የተባለ ተራራማ ቦታ ድረስ በመሄድ ገ/መድኅን አርአያ ኢትዮጵያዊ ግዴታቸውን ተወጥተው የተመለሱ ጀግና መሆናቸውን በሕይዎት ኖሬ ስመሠክርላቸው ክብርና ኩራት እየተሰማኝ ነው። ይህንና ሌሎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊነገርላቸው የሚገባቸውን ድንቅ ሥራዎች አንድ ቀን በሕይዎት ያለን ምሥክሮች በአካል ቀርበን የመንመሠክረው ሀቅ ስለሆነ አቶ አብርሃም ዛሬ አፍዎ እንዳመጣ መዘላበዱ ነገ ትርፉ ውርደት ይሆናልና ቢታቀቡ እመክረዎታለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ዕውነታውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ወደፊት ሊያቀርቡ የሚችሉ ብዙ ሰዎች ስላሉ አቶ አብርሃም ያዬህ የምላስዎትን አፈሙዝ ከጀግናውና ሀቀኛው ገ/መድኅን ይልቅ ወደ ሀገር አጥፊው ወያኔ እንዲያዞሩ ስመክር፣ ሌሎችም እበላ ባይ ሆድ አደሮች ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስማቸውንና ታሪካቸውን ባይለውጡ መልካም ነው እላለሁ።

በኩራት ተሞልቼ ሁለንተናዬ ሰማያዊ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)


June 14, 2013
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
‹‹በየቀኑ በየቀኑ ሰማያዊዎች አሉኝ›› (ሰማያዊ ወይም “ብሉስ” አፍሮ አሜሪካውያን የሚታወቁበትና ይዘውት የተሰደዱት የንጉርጉሮ ባህላዊ ሙዚቃቸው ነው)  አለ ዘማሪው ቢቢ ኪነግ  በሚወዳት ክራር “ሉሲል” ላይ፡፡ እኔም በየቀኑ በየቀኑ ላለፉት ስምንት ዓመታት የ‹‹193/763 ሰማያዊዎች›› ነበረኝ:: “አስከ 25ኛው ሰአት ድረስ አላቋርጥም ምክኛቱም አሁን የምኖረው በሰማያዊ ተስፋ ላይ ነውና” አለ ዘማሪው ኤሪክ ክላፕተንም!፡፡እኔም በበኩሌየሰማያዊውን ሃይል እየተጎናጸፍኩ ነው::
እኔም ሰማያዊና ደስተኛ ነኝ፡፡ ማለትም ሰማያዊ እንደ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ፡፡ሰማያዊን ቀለም የመረጡበትም ምክኒያት የአንድነታቸውን መሰረት፤ ሰላምን ተስፋን በኢትዮጵያ  ለማጠናከር ነው፡፡ ሰማያዊ ሲባል ልክ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሰማያዊ ለሁሉም ሕዝቦች፤ በወደፊቱ ተስፋና ሠላም ላይ ለመተባበር ላለሙት ሁሉ ሰማያዊ አይነት ነው፡፡ ልክ እንደ አውሮፓ ሕብረት ሰማያዊ፤ ወደ 24 የሚጠጉ ሃገራት ለትክክለኛው የኤኮኖሚና ለፖለቲካዊ ጥምረት እንደሚሰሩት አይነት ሰማያዊ ነው፡፡ ልክ
እንደኢትዮጵያዊያን ሰማያዊ ሁሉ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሕብረት ላይ እንደተሳሰሩትና በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሰላማዊ፤ ተስፋ በለመለመበት ለመተባበርና አንድ ለመሆን እንዳቀዱት አይነት ሰማያዊ ነው፡፡ ወደፊት ሰማያዊ! ቀጥሉ!!! በርቱ!!!Ethiopia's Semayawi party (blue party)
ሰማያዊውን መስመር ተከተሉ
ላለፉት ዓመታት እንደምታስታውሱት ስለኢትዮጵያዊያን ኦቦሸማኔዎች (የወጣቱ ትውልድ ማለት ነው) ስናገር፤ ስጽፍም  ነበር:: ስለ ኦቦሸማኔ፤ ትውልድ ለበርካታ ዓመታት ሳነሳ ነበር፡፡ አሁን ይፋ ማውጣት እፈልጋለሁ፡፡ የዘመናት ልዩነትን ጨርሼ ወደ ኦቦሸማኔዎች ዋሻ ለመግባት ተሻገሬያለሁ፡፡ ነውና አዎን ከዳሁ! ጉማሬዎችን (ማለትም ወጣት ያልሆነው መንቀሳቀስ የተሳነው አጅ አግሩ የተሳሰረው የደነዘዘው ትውልድ) ጥያቸው ሄድኩ:: እኔ አሁን ‹‹ኦቦ-ጉማ›› ነኝ:: (ማለትም የጉማሬ ወገብ ከኦቦሸማኔዎች ጋር መወገን የመረጠ)::
ጉዳዩ አንደዚህ ነው፡፡ ኦቦ ሸማኔዎች እየተፈናጠሩ ሲነሱ ክፍ ከፍ ሲሉ ፤ እስከላይኛው ጠርዝ ድረስ ሲምዘገዘጉና ከፍ ሲሉ አየኋቸው፡፡ በቅርቡም መንገዶቹን ሲሞሉ፤ ሳያነገራግሩ ፈራ ተባ ሳይሉ ሲተሙ ጎዳናውን ሞልተው አየኋቸው፡፡‹‹እንዴት ደስ የሚያሰኝ ትዕይንት ነው›› አልኩ፡፡ በጎዳናዎቹ ላይ ሲፈሱ መሰከርኩ፡፡ (ኦቦሸማኔዎች ስለ ሠላም፤ ስለፍትሕ፤ ስለነጻነት፤ እና ስለሰብአዊ  መብት ሲያቀነቅኑ ሲዘምሩ አጋጥሟችሁ ያውቃል?) እንዴት ደስ የሚልና ስሜት ያመቀሰቅስ ድምጽ ነበር! የኔ ዜማ እየዘመሩልኝ ነበር  እኮ!!፡፡›› ከእንግዲህ እኔ ከኦቦሸማኔዎች ጋር ነኝ፡፡ ከፈጣኖቹና ከአስፈሪዎቹ ቆራጥ ኦቦሸማኔዎች ኋላ አየተጎተትኩም ቢሆን እጉኣዛለሁ፡፡
አቤት እስቲ እይዋቸው ኦቦ ሸማኔዎች ሲሮጡ!  እስቲ እንደ ንጋት ጸሃይ ሲወጡና ሲያበሩ ተመልከቷቸው! ‹‹እንደንስር አሞራ አክናፎች እየመጠቁ ፤ እየፈጠኑ፤ ድካም ሳይሞክራቸው፤ እርምጃቸው ሳይቋረጥ፤ ሳይዝለፈለፉ ይራመዳሉ፡፡ ‹‹እስቲ ይታያችሁ እንደ ጉማሬዎች መንገላወድ፤ መዳህ ሳይሆን፤ አቦሸማኔዎች ሲጀግኑ፤ ማየት አያስደሰትም፡፡ ያስገርማል! አይደለም እንዴ?
በዐመቱ የመጀመርያው ጦማሬ ላይ፤2013 ‹‹የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ትውልድ ዘመን›› ብዬ ሰይሜ ነበር፡፡ ያ ያልኩትዓመት ደሞ ይሄው  የአሁኑ ወቅት ነው፡፡ አንዳንድ ጉማሬዎች ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ ‹‹ኦቦሸማኔዎችን ተዋቸው፤ እነሱብልጭታና ምንዛሪ ናቸው›› ብለው ነበር፡፡እኔ ደግሞ እስቲ በመስታወቱ ውስጥ ተመልከቱ አልኩ፡፡
የኢትዮጵያን አቦ ሸማኔዎች ‹‹ስንት ሰአት ነው? ግዜው ምንድነው?›› አልኳቸው፡፡ በነጎድጓዳ ድምጻቸው ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው›› ሲሉ መለሱ፡፡ አልተሰማኝም! ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው!!›› ብለው በድጋምሜ አናጉት:: አስቲ ድምጻችሁን ከፍ፤ ኮራ ብላችሁ በሉት! ‹‹የኦቦሸማኔዎች ሰአት ግዜ ነው!!!››ወደፊት!!!!
በ2013 አመት መጀመርያ የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ከፍ ብለው መጥቀው በአዲስ ከፍታ ላይ ያንጸባርቃሉ ብዬ ነበር፡፡ ከፍ አድርገው ኢትዮጵያችንን ያነሷታል፡፡ ያን እያደረጉ ነው፡፡ እነዚህ ኦቦሸማኔዎች እንማን ናቸው? የኢትዮጵያ የኦቦሸማኔዎች ትውልድ ምሩቃኑና የሰለጠኑ  ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ ‹ብልሆቹንና ብሩሆቹን› ብቻ ሳይሆን፤ የተጨቆኑትን ወጣቶች ለነጻነት ዓየር እንዲበቁ፤ በመደለል፤በማግባባት በሙስና የተታለሉትን፤ ለጭቆና የተዳረጉትን ሰብአዊ መብት በመደፈሩ ድማጻቸውን ስላሰሙ የተወገዙትን፤ ሁሉ ያካትታል፡፡የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔ ትውልድ ማለት፤ የእስክንድር ነጋና የሰርክዓለም ፋሲል ትውልድ ማለት ነው፡፡የአንዱዓለም አራጌ፤ የርዕዮት ዓለሙና የውብሸት ታዬ፤ የበቀለ ገርባ፤የኦልባና ፈይሳ እና የሌሎችም መሰሎቻቸው ትውልድ ነው፡ ኦትዮጵያን ሰቅዞ ከያዛት የብረት አምባገነናዊና ጨቋኝ ገዢ የሚያላቅቃት የኦቦሸማኔ ትውልድ ብቻ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ጊዜው ካለፈበት ከሻገተና ከነቀዘ የበሰበሰ፤ በሃሰትና በቅጥፈት ላይ ከተመሰረተ፤ገዢ መንግስት አላቆ፤ ወደ ሕዝባዊ ስርአት የሚያስገባት የኦቦሸማኔው ትውልድ ብቻ ነው፡፡ በጃንዋሪ 2013 የግሌን ‹‹የኦቦ ጉማ››ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ‹‹በ2013 የኢትዮጵያን ወጣቶች ባለኝ አቅምመና ችሎታ ለማስተማር ለማማከር ለመምከር እሞከራለህ ብዬ ቃል ገብቼ ነበር፡፡ ያን ቃሌን አላፈረስኩም፡፡ ቁጥራቸው ባዘቀዘቀ ወቅትም መረት ላይም ወድቀው 1,2 ,3,… ተነሱ ሲባል የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች እንዲነሳሱ ሲቆጠርም አልተለየሁም፡፡ ተነሱ ኦቦሸማኔዎች! ተነስታችሁ የኢትዮጵያን ብርሃን አሳዩ! በማለት ቃሌን ጠብቄአለሁ::
እቅጩን  መናገር አስፈላጊ ነው፡፡ጉማሬዎች ከኦቦሸማኔዎች ጋር ቃል አፍርሰዋል፡፡ ኦቦሸማኔዎች በጉማሬዎች ክህደት ደርሶብናል ይላሉ፡፡ኦቦሸማኔዎች መገለልና ልዩነት ተሰርቶብናል ይላሉ፡፡ኦቦሸማኔዎች፤ ታማኝነታቸውና አክብሮታቸው እንደ ማንቋሸሽና ብልግና ድፍረት ተወስዶብናል ይላሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎች በርካታ ቅሬታዎችን ባነሱዋቸው ነጥቦች ላይ የጉማሬዎች ቸል ባይነት ያደረሰባቸውን ግድየለሽነት ከዚያም ያስከተለውን ዝግመት በቁጭት ያነሳሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎቹ ጉማሬዎችን ተጠያቂነትን ተቀበሉ ባልን ተገፍተናል፤ ሃሳባችንን በነጻ በመግለጻችን በዘምተኞቹ ጉማሬዎች አርፈን እንድንቀመጥና ትንፍሽ እንዳንል ተደርገናል ይላሉ፡፡
ዛሬ ዛሬ የኢትዮጵያን ኦቦሸማኔዎች ሳይ መላ ሰውነቴ ሰማያዊ ይላበሳል፡፡ አሁን ሰማያዊ የምመርጠውና የምወደውቀለም ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎች ከአፍሪካ ሁሉ የተለዩ ብርቅዬ ኦቦሸማኔዎች ናቸው፡፡ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎችን ሳይ ሰላምና ተሰፋ ይታየኛል፡፡ ሰማያዊ ኦቦሸማኔነት ሲሰማኝ መከፋፈል አይሰማኝም፡፡ አንድ ሕዝብ ነዋ የሚታየኝ፡፡ከምር ሰማያዊን እመርጣለሁ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይን ግን እወደዋለሁ ከዚያ አኳያ ሺህ ጊዜ ከሰማያዊ ይበልጥብኛል፡፡ እስቲ ታዘቡ! አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በውብ ከፈይ ሰማያዊ ተጠቅልሎ! ወድድድድ አደርገዋለሁ፡፡
ሰማያዊውን በአንድነት ሰማያዊውን መስመር እንከተል እላለሁ፡፡ በሰማያዊው ባቡር ላይ ተሳፈሩ፡፡ የመጀመርያው መቆሚያ ጣቢያ፤ ፍትሕ፤ ሁለተኛው ዴሞክራሲ፤ ሶስተኛው መቆሚያ፤ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ/ የፕሬስ ነጻነት፤ አራተኛው የፖለቲካ እስረኞች ነጻ መሆን፤ አምስተኛው መቆሚያ የዕምነት ነጻነት፤ ስድስተኛው …ሰባተኛው……ስምንተኛው…….ከእንግዲህ የሚያቆመን የለም፡፡
እነዚህ ኦቦሸማኔዎች መነሻ መድረሻቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ኦቦሸማኔዎች ዘመናዊው መንገድ መመርያ ጂ ፒ ኤስ ሲኖራቸው እኛ ገና አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ ነው ያለን፡፡ እነሱ የተቀየሰ መንገድ ሲኖራቸው እኛ ግን ዘዋሪ ጎዳና ነው ያለን፡፡ አነጋገራችንም በአዙሪት ነው፡፡ እነሱ ሲራመዱም ሲናገሩም ትክክልና ቀጥ ያለ ነው፡፡ እኛ ደሞ መቀኘትና ተረት ተረት እናበዛለን፡፡ ኦቦሸማኔዎች አንድ ጊዜ ጠፍተው ነበር አሁን ግን ተገኝተዋል፡፡እኛ ደሞ እስከናካቴው ላንገኝ ጠፍተናል፡፡ በቀስተደመናው መጨረሻ በፈዘዙና ባረጁ ዓይኖቻችን የወርቅ ማሰሮ እንፈልጋለን፤ ኦቦሸማኔዎች ግን ሕዝባዊ ቀስተደመናን በብሩህ ዓይኖቻቸው ይመለከታሉ፡፡ ይሁኑበት ጃል! አንተውላቸው!! ሽማግሌዎች፤ያረጀን፤ወቅት ያለፈብን ፤ ባለ አሮጌ ካርታ ባለቤቾች ነን፡፡ አሁን አዲስ ቀን ነው፤ሰማያዊ ቀን ነው፡፡ ውቅቱ ዘመናዊ መመርያ ጂ ፒ ኤስ የያዙት የኦቦሸማኔዎች ነው፡፡ በሰማያዊው ባቡር እንትመም! ሁኑበት ወደፊት በሉለት በሉ ሰማያዊ ኦቦሸማኔዎች፡፡
ተገቢው ዝና እንደአስፈላጊነቱ ሊሰጥ የግድ ነው
በኢትዮጵያ ስላለው ገዢ ፓርቲ ሚዛናዊነት አስተያየት እንደምነሳ ይነገራል፡፡ አምርሬ ስለመንቀፌም ይነገራል፡፡ ገዚውን ፓርቲ
አንዳችም ወቅት ፋታ መተንፈሻ አልሰጠህምም ተብያለሁ፡፡ ለምንም ተግባራቸው መልካም ተናነግረህ አታውቅም ብለውኛል፡፡ያ ሁሉ እውነት ከሆነ እንግዲህ አሁን ለውጥ አለኝ፡፡ (አስተሳሰቡንና ተግባሩን መለወጥ የማይችል ማንም ቢሆን ለለውጥ አይበቃምና) ሲያጠፉ ጥፋቸውን ካጋነንኩ: መልካም ሲያደርጉ ደግሞ ያለምንም እቀባ ድጋፌ አይጓደልባቸውም፡፡ ሰኔ 1 ቀን ሰላማዊ ሰልፍቻውን እንዲደርጉ ሲፈቅዱላቸው መልካም አድርገዋል፡፡ ለሃይለማርያም ደሳለኝና ለቡድኑ፤ የማይቻል ነው ብሎ በርካታ ሰው ያሰበውን የሚቻል በማድረጋቸው ድጋፌ ጨርሶ አይለያቸውም፡፡ያደረጉትና የወሰዱት እርምጃ ቀላል እንዳልበረ እገነዘባለሁ፡፡ ከባድ ጫናም እንደነበረባቸው ይሰማኛል፡፡መልካም እሳቤ የሌላቸውና እኩይ ምግባር ብቻ ሙያቸው የሆኑት ባልደረቦች፤‹‹አታሞክረው፤ በኋላ ታዝናለህ፡፡ አሁን ሰላማዊ ሰልፉን ብንፈቅድ ሰማይ ይደረመሳል፤ ከዋክብትም ወደ ምድር በመውረድ ይከሰከሳሉ… ይልቁንስ በ2005 እንዳደረግነው ሁሉ የማይረሳ ትምህርት እንስጣቸው›› ብለውት እንደነበር ይሰማኛል፡፡ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሠላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ በመፍቀዱ አክብሮቴን እገልጻለሁ፡፡ እሱና የሃሳቡ ደጋፊዎች መልካም አድርገዋል፡፡ ሚዛነዘዊነት አስፈላጊ በመሆኑ ሊመሰገኑ የግድ ነው፡፡(ልዩነት ካለኝ ሰዎች ጋር ትክክል ሲያደርጉ ማመስገን ካልቻልኩ በሚዛናዊነት አላምነም ማለት ነው::) ሃይለማርያምና ደጋፊዎቹ ይህን ውሳኔ ለመወሰን ብዙ ወኔ ጠይቋቸዋል፤ ይህ ነው አመራር ማለት፡፡ የተሳሳተን መንገድ መምረጥ ቀላል ቢሆንም ትክክለኛውን ማደረግ ደግሞ ከባድ ነውና: ከባዱን በመወጣታቸው ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ የበለጠ ጉልበት እንዲያገኙና ትክክለኛውን ለማድረግ እንዲያበቃቸው ምኞቴ ነው፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ የፓርቲው አመራሮች አልበገሬነታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሚፈልጉትን እንደሚያውቁ አረጋግጠዋል፡፡ ምን ማድረግ እንደነበረባቸውም አስመስክረዋል፡፡ መልእክቶቻቸውን ላመስተላለፍ የረጉና የበሰሉ ነበሩ፡፡አንዳችም የቁጣ መንፈስ የእርግማን ቃላት የማውገዝና የጠበኝነት መንፈስ አላሳዩም፡፡ ወደሠላማዊ ሰልፉ ሽርፍራፊ ነገር ተሸክመው አልመጡም፡፡ በትከሻቸው ያነገቡት ዓላማቸውን ብቻ ነበር፡፡ ጠብና ትንኮሳም ዓላማቸው አልነበረም፡፡ መነሻና መድረሻቸው ሁሉ የሰብአዊ መብት መከበር ብቻ ነበር፡፡
የፓርቲው አመራሮች፤ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ሁሉ፤ መልካም አርአያ የነበራቸው ናቸው፡፡ ለስነስርአት የተገዙና የረጉ ነበሩ፡፡ አንድም ሰው ድንጋይ አልወረወረም፡፡ አንድም ጠብ አልታየም፡፡ በማንኛውም መልኩ ሰብአዊ መብታቸውን ማስከበር ብቻ ነበር ዓላማቸውና ያንን ነው የተከተሉት፡፡ ለጥበቃ የተመደቡትም የፖሊስ አባላት ቢሆኑ የተለየ ሁኔታ ስላጋጠማቸው ዳር ዳሩን ከመቆም  ባሻገር ሌላ ምርጫ አልነበራቸውም፡፡ ጥቂቶቹም ግንብ ተደግፈው በማፋሸግ እንቅልፋቸውን ለማባረር ነበር ጥረታቸው፡፡ ሠላማዊው ሰላማዊ ሰልፍ ሠላማዊነቱ ይህን ይመስል ነበር፡፡ ለዓለም ያሳዩትም በሰላማዊ በክብርና በጨዋ ደንብ ተቃወሞን ማሳየት እንደሚቻል ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲና አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ለማመስገን ቃላት ያጥሩኛል፡፡ ምንግዜም ከግጭት የወጣና ሰላማዊ መንገድ ከግጭትና ጠብ ጫሪ መንገድ እንደሚበልጥ ያለኝን ቋሚ እምነቴን አረጋግጠውልኛል፡፡
ስለ (ሰብአዊ መብት) ትክክለኛነት አስብ፤ (ሰብዊ መብትን) በትክክለኛ መንገድ ተግባር ማንም ያድርገው ማንም እኔ ምን ጊዜም በእውነተኛው ወገን በኩል ነኝ፡፡ ትክክለኛ ያልሆነውን መንገድ ማንም ያድርገው ማንም አልደግፈውም፡፡ ስለተግበሪው ሳይሆን፤ ስለትግበራው ነው፡፡ስለሃጢአቱ እንጂ ስለሃጢአተኛውአይደለም፡፡ መልካም ተግባር ሊመሰገንን ሊደፋፈር ይገባል፡፡ መጥፎውም ውግዘትና እርግማን ይገባዋል፡፡ በጁን 1 ሰማያዊ ፓርቲም ገዢው መንግስትም ትክክለኛውን ጉዳይ ተግብረዋል፡፡ ስለሰብአዊ መብት ትክክለኛነት በመተግበር ስህተት አይፈጸምም፡፡
ደህና እስከመሰለኝና  እስካመንኩት ድረስ የተሳሳተ መንገድ ቢመስልም መልካም ነገር ማድረግን እመርጣለሁ፡፡ የዋህነህ የሚሉኝ የኔ አይሆንም ባዮች አሉኝ፡፡ ‹‹እነዚህን ሰዎች አታውቃቸውም ይሉኛል፡፡›› እየቀለዱ ነውይላሉ፡፡ አንድ ነገር ስላደረጉ ልታምናቸው አይገባምና ትንሽ ጠብቃቸው ይሉኛል፡፡ እኔ ግን ጨርሶ አልጠብቅም፡፡ እንደአመጣጡ እቀበለዋለሁ፡፡ቆይተው ጠባያቸው ሲለወጥ ያን ጊዜ ደሞ ሃሳቤን እገልጻለሁ፡፡
‹‹ታዲያ ቢቀልዱስ?›› ከሃሳብ የበለጠ ተግባር፤ድርጊት ይመሰክራል፡፡ ምናልባትም ይህ የአሁኑ ድርጊታቸው ለለውጥ የሚደረገውን ሂደት አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ላይ የሚፈጥረውን ስሜት ለማየት ያደረጉት ሙከራ ሊሆን ይችላል፡፡ ላሞቹ ወደ ጋጣ እስኪገቡ ድረስ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን የፈቀዱበትን ምክንያት ላንሰላሰል ሳወጣ ሳወርድ መዋል እችላለሁ፡፡ ያ ደሞየራሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ በኔ አመለካከት፤በፓርቲው ውስጥ በተሰባሰቡትና በተቃዋሚ ማሃል ያለውን ርቀት ለማጥበብ ለሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን መፍቀዳቸው ጥሩ ጅማሮ ነው፡፡ በተፎካካሪዎች ማሃል ያለመተማመን በበረታ ቁጥር፤ በድንገትም ቢሆን ለመግባባት የሚያስችል ዘር ማቆጥቆጥ ሲጀምር ያንን መንከባከብና ማበረታታት አስፈላጊ ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሰላማዊ ሰልፋቸውን በተሳካ መንገድ ሲያካሂዱ፤ለሰማያዊ ፓርቲና ለገዢው መንግስት፤የዕውነት ወቅት ነበር፡፡ ለሁለቱም የተሰነዘረ የፍተሸ ወቅት ነበርና ሁለቴም ወገኖች ፈተናቸውን በሰማያዊ ቀለም አልፈዋል፡፡
ዕቅድህ ለሰላም ይሁን  እንጂ ክፋትን አታስብ፤ መልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲን በተመለከተ ለስርነቀል ለውጥ
እና ለመሻሻል ጣር
የተሰማኝን በመናገሬና እውነትን በመተንፈሴ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለዚህ ነው የግል ድሀረ ገፅ ‹‹ለሰብአዊ መብትተሟገት፡፡ እውነትን ለሃያላን አስታውቅ›› የሚለውን ጥቅስ የያዘው፡፡ እውነትን እንደማየው፤ እንደምናገረውና እንደሚሰማኝ፡፡ ይህ ደግሞ የኔ ጎራዴና ጋሻዬ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እውነት መራር ፍሬ የሚሆንበት ወቅት አለ፡፡ አስቸጋሪም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያም በተለየ፤ የእውነት ውጤት ጣፋጭ፤ ነጻ አውጪ፤ ብርሃናማና ፍላጎታችንን የሚያሟላ ሊሆን ይችላል፡፡ መለስ ባለፈ ጊዜ፤ ለስንብቱ ለመለስ ወራሾች አንድ የእውነት ሙግት አዘልጥያቄ
አቅርቤ ነበር፡፡
መለስ ስለ ሰብአዊ መብት ረቀቅ ባለ መልኩ በትንሹም ቢሆን ምልከታ እንዳለው ገምቻለሁ፡፡ የጥርጣሬ ማመሳከሪያ ያህል ላምነው እፈልጋለሁ፡፡ መለስ በ2007 ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ፤ ‹‹የኔ ስጦታ (ቅርስ) የተሳካና የተስተካከለ ልማት በማካሄድ ኢትዮጵያን ለዘመናት ከኖረችበት የችግርና የመከራ እስር ነጻ ማውጣትና የተረጋጋ ሃገር እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ መልካም አስተዳደርንና ዴሞክረሲን በተመለከተ መሰራታዊና ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ ነው: እናም እኔ ወደ ጡረታ በምገለልበት ጊዜ ያልኳቸው ጉዳዮች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ› ብሎ ነበር፡፡
‹‹መልካም አስተዳደርንና ዴሞክረሲን በተመለከተ መሰራታዊና ስር ነቀል ለውጥ ማድረጊያው›› ወቅት አሁን ነው፡፡ መሰራታዊ የሆነ የኋልዮሽ ሂደት አምባገነናዊ አስተዳደር፤ማንአለብኝነትና ጭቆናን ተመልክተናል፡፡ ‹‹ያ‹‹ መለስ የወደፊቱ ያለው ጊዜ አሁን ነው›› ሁላችንም በአንድነት ሆነን የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ምኞቱንና ሃሳቡን ተግባራዊ ለማድረግመስራት አለብን፡፡ ወራሾቹ የሆኑት የመለስ ሹመኞች ይህን የመለስን የውርስ ምኞት በመቀበል ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር በጥምረት ለመስራትና የመለስን የምኞት ጥማት መወጣት አለባቸው፡፡
የ “መልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርነቀል መሰረታዊ ለውጥ” የሚጀምረው የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታትና የሽብርተኝነትንና የእርዳታ ሰጪዎችን ድርጅቶች ሕጎች መለወጥና ማስተካከል፤ የሕግን የበላይነትም ባረጋገጠ መልኩ እንዲተገበር መንገዱ ሲጠረግ ነው፡፡ የዘመን መለወጫው እየተቃረበ እንደመሆኑ፤በመሰረታዊው ስር ነቀል ለውጥ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ መሻሻል ሁላችንም በአዲሱ ጎዳና ላይ መራመድ መጀመር ይኖርብናል፡፡
መለስ በቃላት ደረጃም ቢሆን ሲመኝ እንደነበረው፤ ሰማያዊ ፓርቲም ፍላጎቱ የመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ስርነቀል ለውጥ ነው፡፡የመለስም ወራሾች ይህን ስር ነቀል ለውጥ እንደሚፈልጉት አልጠራጠርም፡፡ በተቃዋሚውም ጎራ ያሉት ሌሎችም ይህ ነው ፍላጎታቸው፡፡ሁሉም ከተስማማበት ቀላሉ ጥያቄም፤ ይህን ለውጥ እንዴት ማምጣት ይቻላል የሚለው ነው፡፡
ለውጥ ፈለግነውም ጠላነውም በጊዜ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ ለውጥ በትክክለኛው መንገ ድ አለያም በሌላ መልኩ መምጣቱ የግድ ነው፡፡ስለዚህም ለውጥን በሰላማዊው መንገድ ብንቀበለው እንጂ ካልሆነ በከፋ መልኬ ስለሚመጣብን ቀናውን እንምረጥ፡፡ በኢትዮጵያ ለውጥን ወጣቱ እየተራበውና እየተጠማው እየፈለገው ስለሆነ መምጣቱ አያጠራጥርም፡፡ወጣቱ የራሳቸውን አመለካከትና  ሁኔታ ለውጠዋል፡፡ ከእንግዲህ የሚቀበሉት አይደለም በቅቷቸዋል፡፡ ስለሃገራቸው እጣ ፈንታ ግንባር ቀደም መሆናቸውን ታሪክ ስላስረከባቸው ምንም ሃይል ሊያቆማቸው ከቶ አይችልም፡፡
ለውጥ ለሚፈሩትና ለሚያገሉት በእጅጉ ጨካኝ ነው፡፡ እነዚህ እምቢ ባዮችና ለውጥን ለመቀበል ፍቃድ ሌላቸውየራሳቸውን ጥፋት ቀያሽ መሃንዲሶች ይሆናሉ፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ስለ ለለውጥ ተመክረው ያንን ለመቀበል ፍቃደኛነት አጡ፡፡ መንግስታቸው እራሱ በእራሱ አጠፋ፡፡ የጁንታው መንግሥቱ ኃይለማርያምም ስለለውጥ ተመክሮነበር፡፡ መልሱ ግን እብሪት ነበር፡፡ እሱም የእራሱን መንግስት አጠፋ፡፡ መለስም ስለለውጥ ተመከረ፤እሱም አሻፈረኝ አለ፡፡ ስለዚህ አሁን ያሉት ወራሾቹ ሃሳቡ የነበረውን የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲን ለውጥ በስርነቀል መልኩ የመተግበር ሃላፊነት አለባቸው፤ ያንን የማይቀበሉ ከሆነ ደግሞ የታሪክን ፍርድ መቀበል ነው ምርጫቸው፡፡ ያ ደግሞከፋ ነው:: “ከታሪክ ለመማር ፍቃደኛ ያልሆኑ ሁሉ፤ያለፈውን ሰህተትመድገም ግዴታቸው ይሆናል፡፡”
ለውጥን መፍራት በሰብአዊ ፍጡር ውስጥ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች በአንድ ወቅት ኤሌክትሪክ ሃይልንና በዓየር ላይ የሚበሩትን አውሮፕላኖች ይፈሩ ነበር፡ በጋሪና በፈረስ የሚጠቀሙትም: የሰው ልጅ እንዲበር ቢያስፈልግ ኖሮ ክንፍ ይበጅለት ነበር ብለዋል፡፡ አንድ ጊዜ ግን ከፍርሃታቸው ከተገላገሉ በኋላ ለውጦቹን የህይወታቸው አካላት አድርገዋቸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያሉት ባለስልጣናት በሙሉ ለውጥን በእጅጉ የሚፈሩና ስለለውጥም  መስማት የማይፈረቅዱ ናቸው:: ስልጣናችንን ምቾታችንን አናጣለን ብለው ይፈራሉ፡፡(አንዳንዶችም  ከምራቸው በስልጣን ላይ ለ100 ዓመታት እንቆያለን ብለው ያስባሉ፡፡ የሚያሳዝኑ ሃሳበ ምስኪኖች!) አንዳችም ዕድል ለለውጥ ለመስጠት አይፈቅዱም፡፡ ለውጥን የሚጠይቁትም ቢሆኑ የራሳቸው የሆነ ፍሃትና ጥርጣሬ አላቸው፡፡ለውጡ ምን ሊያስከትል እንደሚችል፤ ምን ይዞ እንደሚመጣ አያውቁትም፤ ሆኖም ግን ለለውጥ ቅድሚያ ሰጥተው ያሻው ይሁን ግን ለውጥ እንፈልጋለን ይላሉ፡፡ ፈላጊዎችም ሆኑ እምቢተኞች የለውጥ የፍርሃት እስረኛ ሊሆኑ አይገባቸውም፡፡ ከፍርሃት እስር ከልባቸው ውስጥ
ከተቋጠረው ድፍረት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ለውጥን ማስተናገድ አለባቸው፡፡
አፍሪካ ሞቶ በተወለደ አለያም በጨነገፈ ለውጥ ቆሽሻለች፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ቀን በቀን ልዩነት ለውጥ እያየንነው፡፡ የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ጭንጋፍ ገዢዎች እንደበጋና ክረምት ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደ ሃይለኛ አውሎ ነፋስ በሚልፉበት ያለውን ሁሉ እያጠፉ ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች እንደበረሃ ንዳድ ይቃጠላሉ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ እነደ ጭጋግ ጉም የጨለሙ ናቸው፡፡ እውነተኛው ለውጥ በአፍሪካ ግን የማይጨበጥ ሆኖ አለ፡፡ እውነተኛ ለውጥ የመሪዎች ብቻ ውጥ አይደለም፡፡ የንዳንዱ ገለ ሰብ ልብና የሕሊና ለውጥ ያስፈልገዋል፡፡
ለውጥን ለመልካምነቱ ልናቅፈውና ልንቀበለው ይገባናል እንጂ ልንፈራው አይገባንም፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ለጥሩና አስፈላጊ ለሆነው ለውጥ ነው የተነሳሱት፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ እያኮበኮበች ያለችው ልዩ ለሆነው ለውጥ ነው፡፡ ከለምለሙ የወጣቶች ሕሊና የሚፈልቀውን ለውጥ ነው፡፡የቀድሞዋ ኢትዮጵያ በዘር በተጠላለፈ፤ የነጋድ መጠቃቀም በቀደመበት፤የጎሳ ውስብስብ ባደራበትና በተረሳ የኋልዮሽ የፖለቲካ ስርአት  መሰረት ላይ እንድትገነባ አይሹም፡፡ የጻታ እኩልነትን ይሻሉ፡፡ የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ የቀረጹበት የራሳቸው ንድፍ አላቸው፡፡ እኛ የራሳችን ነበረን: እነሱስ የራሳቸው ሊኖራቸው አይገባም? ትክክለኛ ፍርድ ነው፡፡
አደረግነውም አላደረግነውም፤የኢትዮጵያ ኦቦሸማኔዎች ትውልድ አሸናፊነት የተረጋገጠ ነው፡፡ ነፋሱ ወደነሱ አድልቷል፡፡ ቁጥሩም የነሱ ነው:: 75 በመቶው የአትዮጵያ ሕዝብ እድሜው ከ35 በታች ነው፡፡ታሪክ ከነሱ ጋር ወግኗል፡፡ ከነሱ በፊት የነበሩት በሚሊዮን የሚቆጠሩት ወጣት ኢትዮጵያዊያን ደማቸውን አፍሰው፤በላብና በደማቸው ፍጹም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጣሩት፡፡ የዓለማችን ሃይሎች የሆኑት ፍትህ፤ነጻነት፤ዴሞክራሲ ከነሱ ጋር ግምባር ፈጥረዋል፡፡ እኛም ከነሱ ጋር መሆን ይገባናል፡፡ ለውጥ በመሳርያን በጉልበት ሊገታ አይችልም፡፡‹‹ጊዜው የደረሰውን ሃሳብ ማንም አያቆመውም::›› የአዳዲስ ሃሳቦች ወቅት፤የትኩስ ወጣቶች ገጽታ በኢትዮጵያ፤ ጊዜው አሁን ነው፡፡
በለውጥ ሂደት የሚተርፉት ባለመሳርያዎቹና ባለገንዘቦቹ አይሆኑም፡፡ ለለውጥ ፈቃደኛነትን ያሳዩ ፤ከለውጡ ጡጫ ጋር አብረው በመንከባለል፤ፈንጂውን የሚከላከሉት ናቸው፡፡ ስሕተት ላይ የሚጥሉትን ነገሮች በማሰላሰል ዘመን ላስቆጥርእችላለሁ? 2005 በ2013 ሊመጣ ይችላል? ስለትክክለኛው ማሰብ ያለብን ቀላል ስለሆነ ሳይሆን፤ አስቸጋሪና ፈታኝስለሆነ ነው፡፡ ስህተትን መፈጸም ምንጊዜም ትክክለኛውን ከማከናወን የበለጠ አስቸጋሪ ነው፡፡
እንደሰብአዊ መብት ተሟግቻነቴ፤ እውነትን በመደገፍ ስህተትን ማውገዝ ተግሬ ነው፡፡ አንድ ሰው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሊሆን ሲወስን ሊወስደው የሚገባው ምርጫም ይሄው ነው፡፡ ስለሰዎች ሰብአዊ መብት እጨነቃለሁ እንጂ ስለፓርቲ  ፖለቲከኞች ስለ ፖለቲካ ዘይቤ ወይም መሰሎች አይደለም፡፡ ሥላጣን ወሳኙ ሳይሆን አመላካች ቅያስነው፡፡ ጥሩም መጥፎም ሊሆን አይችልም፡፡
ከዓመታት በፊት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስከበር የወጣቱት ንጹሃን ዜጎች በመጨፍጨፋቸው ሰበብ ወደሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ስቀላቀል፤ከ8000 ቃላት ያላነሰውንና አድርጌው የማላውቀውን ‹‹ግዙፉ ሲነቃ›› በሚል ርዕስ ረጂሙን ንግግሬን አነበነብኩ፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን አሜሪካኖች በሃገራቸው ጉዳይ ልዩነት ማምጣት ይችላሉ?(እዚህ ይገኛል) ያንንም በአጭሩ ላስረዳ እችላለሁ፡፡ ‹‹የዓላማችንን ትክክለኛነትየምናረጋግጠው በደም በጨቀየና የሙታን በድን በሞላበት በጦር ሜዳ ሳይሆን፤ በወንዶችና ሴቶች ቋሚ ልቦቻችንና በማሰቢያ ሕሊናችን ነው፡፡›› አሁንም መመርያዬ ይህ ቀላል እሳቤ ነው፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ ሕዝባዊ ሰላማዊ ትእይነተ ሕዝብ ብዙ የምንማረው ጉዳይ አለ፡፡ ዋነኛው ነገር ሰላማዊ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚፈራ ሳይሆን የሚደገፍና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ነው፡፡ ምናልባት ከሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጋር በጎዳናው ላይ ልንተም አንችል ይሆናል፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ጋር በጋራ መቆማችንንና መወገናችንን ግን ለማሳወቅ መጠራጠርና ማፈግፈግ የለብንም፡፡በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብቻቸውን ሊያከናውኑት አይችሉም፡፡ ‹‹እኛ›› በሥልጣኑ ላይና ከሥላጣኑ ውጪ ያለነው ሁሉ እንጂ፡
ከሚነሱት ኦቦሸማኔዎች ጋር መነሳት ብቻ ሳይሆን ከጎናቸው መቆምም ይጠበቅብናል፡፡
ኢትዮጵያዊያኖች በመስቀለኛው መንገድ ላይ ናቸው፡፡ አክራሪነታችንን እሹሩሩ እያልን፤በጥላቻ መረቃችንን እየቀቀልን፤ በብጥብጥ፤ ግጭትና አምባጓሮ  በመስቀለኛው መንገድ ላይ ቆመን መቅረትን መምረጥ እንችላለን፡፡ አማራጩ ደግሞ ሰማያዊውን ጎዳና በመምረጥ ሰማያዊውን ስብስብ በመከተል፤ ወደ እርቀ ሰላም መግባባት መወያየት ማምራት እንችላለን፡፡ ሁላችንም ወደ ሰማያዊው ጎዳና መሰባሰብ ይኖርብናል እላለሁ ምክንያቱም እስካሁን በጥቂት የተሄደበት የተጎደነበት በመሆኑ የወደፊቱ መጓዣም ስለሆነ::
‹‹ሠላማዊ ለውጥን የማይቻል የሚያደርጉት: የሁከትን ለውጥ አይቀሬ ያደርጉታል::›› ጆ ኤፍ ኬ
በኔ አስተያየት ደግሞ‹‹ሰማያዊ ለውጥን የማይቻል የሚያደርጉት የሁከትን ለውጥ አይቀሬ ያደርጉታል::››

*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
http://open.salon.com/blog/almariam/2013/06/10/ethiopia_rise_of_the_blue_cheetahs
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::